ስግደትን በሚመለከት ለመናፍቃን ሀሰተኛ አስተምህሮና ኑፋቄ የተሰጠች አጭር ምላሽ
ስግደትን በሚመለከት መናፍቅ ወገኖች ከሚያስተምሩት የስህተት አስተምህሮ በተጨማሪ ቅድስት ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ፍጹም ሰማያዊ አስተምህሮ በጽኑ ይነቅፋሉ፡፡
ከዚህም ከፍ ሲል ቤተክርስቲያን የምታቀርበው ስግደት ላይ በመሳለቅ የተለያዩ አሳዛኝ ስድቦችን ሲሳደቡና ክፉ ቃላትን ሲናገሩ ማድመጥ እንግዳ ነገር እስካለመሆን እየተቆጠረ መጥቷል፡፡
ይልቁንም ለቅዱሳን፡ ለታቦት፡ ለቤተመቅደስ ክርስቲያኖች የሚያቀርቡትን ስግደት የሚያሳዩ ፎቶዎች ላይ እጅግ ጸያፍ ስድቦችን በመጻፍ በተደጋጋሚ በተለያዩ ግሩፖች ላይ ሲለጥፉ ለመመልከት ይቻላል፡፡ እነዚህ ወገኖች በፍጹም የድፍረት መንፈስ ውስጥ ታስረው በሚፈጽሙት የማይገባ ተግባር የሁላችንም ልብ ቢያዝንም ሀዘናችን ግን ስለ ቅድስቲቱ እምነታችን ስለመነቀፋችንና፡ ስለመሰደባችን ሳይሆን እነዚህ ወገኖቻችን በየጊዜው በሚፈጽሟቸው አስከፊ ሰይጣናዊ ተግባራት የተነሳ በንሰሀ ከማይመለሱበት ፍጹም የአመጻ ተገዢነት በመድረሳቸው ነው፡፡ ስድባቸውማ ለኛ ክብርና ሽልማት የእምነትም ፍሬ ከመሆን በቀር መቼ ጎድቶን ያውቃል፡፡

በእውነቱ እነዚህ ከማስተዋል የራቁ ወገኖች ስለሚፈጽሙትና ስለሚናገሩት ሁሉ ብድራትን የሚከፍለውን አስፈሪውን የእግዚአብሔር ፍርድ ስለምን ሊረሱ እንደወደዱ ባናውቅም ተግባራቸው በሙሉ የሚያስረዳው ግን ከክፋው ወገን መሆናቸውን ነው፡፡
በተለይም እኛ ክርስቲያኖች ለቅዱሳን የምናቀርበውን ስግደት አምርረው ከመቃወማቸውም በላይ ከላይ እንደገለጽነው ጸያፍ ስድቦችን ሲሳደቡ ይስተዋላሉ፡፡
እራሳቸውንም የአምልኮተ እግዚአብሔር ጠበቆች አድርገው በመቁጠር ለእግዚአብሔር አንዴ እንኳ ሲሰግዱ ታይተው የማይታወቁ አጽራረ ቤተክርስቲያን የሆኑ ወገናት የቅዱሳንን ስግደት በመቃወማቸው ለእግዚአብሔር የሰገዱ መስሎ እስኪታያቸው ድረስ በኩራትና በትዕቢት ሲናገሩ ያለ አንዳች ማመንታት ነው፡፡
ለባዶ ትምክህታቸውና ከንቱ ለሆነ ኑፋቄያቸው በሸውራራ አይናቸው ተመልክተው ሁል ጊዜ የሚጠቅሱት ጥቅስ በዘጸአትና በዘዳግም መጽሐፎች ላይ ያለውን ቃል ነው፡፡ቃሉ እንዲህ ይላል፦
"በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፡፡ አትሥገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፡፡.... እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፡፡"/ዘጸ.፳:፪/
በዚህ ሰማይና ምድርን አሳልፎ በሚኖር ዘላለማዊ ቃሉ በህይወት ሊኖሩ ሲገባቸው ብዙዎች ከህይወት ተለይተዋል፡፡ በእውነቱ ከሆነ ይህንን ቃል መናፍቃን ከበፊት እስካሁን የሚጠቀሙበት እንጨት ጠርበው ድንጋይንም አለዝበው፡ ወርቅና ብርንም አንጥረው ጣኦታትን አቁመው የእግዚአብሔርን አምላክነት (አምልኮ) በጣኦታ ለቀየሩ አህዛብና አረማውያን መምለክያነ ጣኦታት አይደለም፡፡ የክፋ መንፈስ ማደሪያ መናፍቃን በዚህ ቃል ሰማይና ምድርን በመላ ፈጥሮ ለሚያስተዳድር ለእግዚአብሔር ብቻ በባህርይ ሊመለክ፡ ልንገዛለት፡ የአምልኮ ስግደትን ለእርሱ ብቻ ሊቀርብለት እንዲገባ ሊያስተምሩ ፈቃደኞች አይደሉም፡፡
እነዚህ አጽራረ ቤተክርስቲያን ወገኖች ቃሉን በብርቱ የሚፈልጉትና የሚጠቀሙበት ለቅዱሳን የሚቀርበውን የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደትን ለመቃወምና ለመሳደብ ነው፡፡
መናፍቃን በዚህ ቃል ምርኩዝነት በመጠቀም ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ውጪ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርበውን የአምልኮና የመገዛትን የባህርይ ስግደት ለቅዱሳን ከሚቀርበው የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት ጋር በማምታታትና በማጋጨት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርበው የአምልኮ ስግደት ለቅዱሳንም እንደተሰጠ የዋህ ምዕመናን እንዲቆጥሩ በመግፋት የአምልኮተ እግዚአብሔር ጠበቆች ሆኖ በመቅረብ ነው ብዙዎችን ከህይወት የለዩት፡፡
በእውነቱ ከሆነ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተዘርፈውና በተኩላዎች ተነጥቀው ከተወሰዱት ነብሳት መካከል ባልሳሳት ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆኑት የቀደመች እምነታቸውን የካዱት በዚህ አይነት ሰይጣናዊ የማጭበር ስልት ተታለው ነው፡፡
ወደ ፕሮቴስታንት የሄዱ ወገኖችን በተደጋጋሚ የመጠየቅ እድል በማግኘቴ "ለምን ከቅድስት ቤተክርስቲያን ወጣችሁ?" ብዬ ለጠየኳቸው ጥያቄ የመለሱልኝ ቀዳሚ መልስ፦ "በመጽሐፍ ቅዱስ ለየትኛውም የተቀረጸ ምስል አትስገድ አታምልካቸውም ይላል፡፡ በኦርቶዶክስ ግን ለብዙ ነገሮች ስግደት ይቀርባል፡፡ ይመለካሉ፡፡ ስለዚህ ጌታ ኢየሱስን አገኘነውና ጌታን ተቀበልን፡፡" የሚል ምላሽ ነው፡፡
እንግዲህ ስለዚህ የጠላታችን ክፋት ምን እንላለን፡፡ ስለሆነብን ነገር ፈጽመን እናዝናለን እንጂ፡፡ ዳግመኛም ሌሎች በጎችን ተኩላዎች እንዳይነጥቁብን አሁን መንቃት እንዳለብን በብርቱ እናስተውላለን፡፡
እንግዲህ መናፍቃን በእንዴት ያለ የክፋት ጥበብ በጎችን አድነው እየበሉ እንዳሉ እናስተውል፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን የማታምነውን "ታምናለች"፤ የማታስተምረውን "ታስተምራለች"፡ የማታደርገውን "ታደርጋለች" ተብለው ከበረት የራቁ ብዙ በጎች በአራጆች ታርደው ተበልተውብናል፡፡
የባላጋራዎቻችን የክፋት ጥበብ ይህ ነው፦ ስለምናደርገውና ስለምናምነው ሊጠይቁንና ሊያዳምጡን ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ስለኛ የወደደዱትንና ያሰቡትን ይነግሩናል፤ ቀጥሎ ፈጽመው ስለ ራሳቸው ሀሳባቸው ይከሱናል፡ ቀጥሎ የልቦናቸውን ጩኸት እያስተጋቡ ይፈርዱብናል፡፡ በእኛ ላይ ከፈቃዳችን ውጪ በፈረዱብን ፍርድና በወሰኑብን ውሳኔ ለዘለዓለም ይሰድቡናል፡፡
ይህም የመታወራቸውና የመደንቆራቸው ምክንያት ያመጣባቸው ባዶነትና ክፋት መሆኑን እናስተውላለን፡፡ ስድብን ሁሉ ግን ስለ እውነተኛዋ እምነታችን በደስታ እንቀበላለን፡፡ ለዚህም ነው፦ ...."አረ ስለ እውነት በቅድስት ቤተክርስቲያን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በቀር የአምልኮ ስግደት ለማንም አይቀርብም፡፡ ለቅዱሳን የሚቀርበው ስግደት እግዚአብሔር ያዘዘውና የፈቀደው ስለ ትህትናም የሚወደውና የሚቀበለው የጸጋና የአክብሮት ነው፡፡" ስንል የሞኝ ጩኸት መልሶ መላልሶ እንዲሉ ስለ እኛ እምነት ተናጋሪዎችና ወሳኞችና ፈራጆችም ሆነው በከተንቱ ሲመኩ ይውላሉ፡፡ ነገም ከነገ ወዲያም... እስከ ፍርዷ ሰአት ቀድሞ የታወቁ የተገለጡ ሃሳውያን ፍርድን እስከሚያገኙበት ቅጽበት....፡፡
እንግዲህ መናፍቃን ከላይ በገለጽነው መንገድ በሀሰት እየከሰሱ በሀሰትም እየፈረዱ ማስተዋል ባልቻሉ ነብሳት አዳራሾቻቸውን ሞልተዋል፡፡ በጩኸትም ብዛት ሰገነቶቻቸው አቁመዋል፡፡ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ሲነገርበት ያከማቹት ይበተናል፡፡ ሰገነታቸውም እንደ እንባይ ካብ ይፈርሳል፡፡ አፈርና ትቢያ ይሆናል፡፡ በአለትም ይቀጠቀጣል፡፡ ፈጽሞም ይደቃል፡፡ ትምክህታቸውም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ይሆናል፡፡ እውነትን ማሸነፍ ለዘላለም አይቻልም፡፡ ተዋህዶ የእውነት አምድ የእውነት መሰረት ናትና፡፡
እውነቱ ሲገለጥ!.
አሁን የቤተክርስቲያን የተቀደሰ እግዚአብሔራዊ አስተምህሮና የመናፍቃን ሀሰተኛ የሆነ ሰይጣናዊ አስተምህሮ በጥቂቱ ብቻ ይመዘናል፡፡
ወሳኝ ነጥቦች
፩.መናፍቃን ለእግዚአብሔር ቃል ያላቸው ክብር እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ የለምም ማለት እንችላለን፡፡ ይህ ግን ጭፍን ፍርድ አይደለም በተግባር በነሱ ህይወት ውስጥ ስለምናይ ነው እንጂ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ቅዱስና እውነተኛ ለዘላለምም የሚኖር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጠው ክብር እኩልና ሊበላለጥ ከቶ የማይችል ነው፡፡ "ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሀንስ ለመልአኩ ሰገደለት" የሚለው ቃልና "መልአኩም አትስገድልኝ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ አለው" የሚሉት ሁለት ቃላት እኩል ናቸው፡፡ ለፈቃዳችንንና ለስሜታችን የሚቀርበንን ብቻ የምንመርጥ ከሆነ ወደ እውነተኛው ምስጢር እንዳንደርስ በርን በላያችን ላይ እንዘጋለን፡፡ እንደዚህ የተለያዩ የሚመስሉ ቃላትን ምስጢር ደግሞ ሊተረጉሙ ስልጣንና ቅድስና ካላቸው አባቶች እግር ስር እንቀመጣለን እንጂ ቀስሜትና በሞራል ተወጥረን በከንቱ መፈክር ከተማውን መረበሽ አይገባም፡፡
በርግጥ ከአስር በማይበልጡ ቁንጽል ጥቅሶች ላይ አዳራሿን ለሰራች ፕሮቴስታንት ይህ ጭንቅ ነው፡፡
ለክህደትና ለኑፋቄ የተመቹ የመሰሏትን ጥቅሶች አንጠልጥላ በቅዱሳን ርስት ላይ የምትቅበዘበዝ ጋለሞታ ጉልበቷ የሚበረታው ባልጸኑትና ማስተዋል በሌላቸው ነብሳት ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ክብር በአንደበታቸው ብቻ ሊናገሩ የሚወዱት ፕሮቴስታንት መናፍቃን በተግባር ግን እንዲህ በሚመዘኑ ቀን እውነተኛ አቋማቸው ይገለጣል፡፡
እነዚህ ወገኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ሃይለ ቃል ከመተማመን ይልቅ በራሳቸው አእምሮ የማሰብ እና የመረዳት ችሎታ ላይ ይተማመናሉ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ግን፦
"በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፡፡" ይላል፡፡/ምሳ.፫:፭/ እንዲሁም፦
"ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው" የሚል ማስጠንቀቂያ በድጋሜ ተሰጥቷል፡፡ /ምሳ.፲፬:፲፪/
በመሆኑም የትኛውም ሰው ከራሱ አእምሮ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን ማክበር ይገባዋል፡፡በቅዱሳኑ አድሮ የነገረንን ቃል እና ዳግመኛም በእነርሱ አድሮ የሚነግረንን የቃሉን የተቀደሰ የምስጢር መፍቻ ትርጓሜ በእውነት ልናምን ይገባናል፡፡ ሰው ያለ አንዳች ጥርጥር በእግዚአብሔር ቃል ሊታመንና ሊመካም ይገባዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር መኖሩን ማስተዋል የሚችለው ቃሉን በሙሉ በእምነት ከተቀደሰ ትርጓሜው ጋር መቀበል ሲችል ነው፡፡
ይህንን ያነሳነው ያለ ምክንያት አይደለም መናፍቃን ወገኖች ከስሜታቸውን ከልባቸው ሀሳብ ጋር የማይሄድ የመሰላቸውን ቃል ሲያጣጥሉ ሲያናንቁና ላለማመን በብርቱ ሲሸሹ በተደጋጋሚ በግላጭ ስለታዩ ነው፡፡ በነዚህ ወገኖች ዘንድ እንደ መለያ አርማ ተለይተው በከተማው መፈክር የሚሰማባቸው በጣት የሚቆጠሩ ጥቅሶች ለዛውም በስህተት መንፈስ የተቃኙ ናቸው፡፡ ሌሎቹ የመጽሀፍ ቅዱስ የህይወትና የእውነት ቃሎች ግን እንዳይነገሩና እንዳይታወቁ ለማድረግ መናፍቃኑ በክፋው ጉባኤያቸው መካከል ወስነዋል፡፡ አሁን ግን ያንን አንፈቅድም፡፡ ለዚህ ርዕሳችን የጠቀስናቸው መናፍቃኑ በእጃቸው ከያዙት የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ብቻ መሆኑን ቀድመን እናሳውቃለን፡፡ ይህም ለሽሽት ምክንያት ለማሳጣት መሆኑ ግልፅ ሊሆን ይገባዋል፡፡
፪.ሁለተኛው ወሳኝ ነጥብ ደግሞ ስግደትን በሚመለከት ለሚነሳው የመናፍቃን የስህተት አስተምህሮና ኑፋቄ በመጽሀፍ ቅዱስ አስተምህሮ ለመመዘን ይቻል ዘንድ በመጀመሪያ የነሱን ኑፋቄ በግልጽ ማስቀመጥ ይገባል
ኑፋቄ አንድ
"ለቅዱሳን የሚቀርብ ስግደት በመጽሀፍ ቅዱስ የተከለከለና እግዚአብሔር በትእዛዙ በማናቸውም ምሳሌ ለተቀረጸ ምስል አትስገድ ካለው ትእዛዝ ጋር የሚደመር በመሆኑ ለቅዱሳን መሰገድ ጣኦት አምልኮ ነው፡፡ ይህንንም በራዕይ መጽሐፍ መልአኩ እንዳይሰግድ ለዮሀንስ አስጠንቅቆታል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ለቅዱሳን የሚደረገውን ስግደት ፈጽሞ እንደማይቀበል ያስረዳል" ይህ የመጀመሪያው ኑፋቄ ነው፡፡ እዚህ ላይ የራዕይ መፅሐፍን ጠቅሰው እንደ ማስረጃ ሲያቀርቡ የሚታወሰን አህዛብ በጌታችን የባህርይ አምላክነት ዙሪያ ለሚያነሱት የክህደት ጥያቄ ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቡት የወንጌል ቃል ነው፡፡ አንድ ህግ አዋቂ ጌታችንን ሊፈትን በቀረበ ጊዜ "ቸር መምህር ሆይ፦" በሚል የሽንገላ ቃል ማጀቢያነት የጠየቀውን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ክብር ስግደት፡ አምልኮ ለእርሱ ይሁንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ "ስለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር የለም፡፡" ብሎ የመለሳትን መልስ ፊደል ብቻ በመያዝ ክርስቶስ "ቸር አትበሉኝ እያለ ለምን ቸር ትሉታላችሁ?" እያሉ በከንቱ እንደሚጠይቁ አህዛብ አይነት ጥያቄ ናት፡፡
ኑፋቄ ሁለት
"ምግባር፡ 'የጽድቅ' ሥራ፡ ትሩፋት ስለማያድን ለእግዚአብሔርም ቢሆን መስገድ ከንቱ ድካም ነው፡፡ ሰው ካለ ስራ በጸጋው ብቻ ስለሚድን፡፡" ይህ ደግሞ ሁለተኛው ኑፋቄ ነው፡፡ አንድ አስገራሚ ነገርን ግን መታዘብ የቻልን ይመስለኛል፡፡ የቅዱሳንን የጸጋ ስግት ለመቃወም ሲሉ አጣመው "ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡" ሲሉ የነበሩ መናፍቃን ቀጥሎ ደግሞ "በስራ በትሩፋት ድህነት የለም መዳን በእምነት ብቻ ነው፡፡" በሚለው ሌላኛው ገዳይ መርዝ እንዴት ወደ ሰይጣን አገዛዝ የሰው ልጅን እንደሚከቱ በብርቱ እናስተውላለን፡፡
ኑፋቄ ሦስት
"ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን የሚያቀርቡት ስግደት የአምልኮ ነው፡፡ በዚህም ጣኦት አምልኮን ይፈቅዳሉ፡፡" በሚሉ ዋና ዋና ኑፋቄዎች ቅድስት ቤተክርስቲያንን ሲወነጅሉ ሲነቅፉ እንደሚውሉ እናስተውላለን፡፡
ሥግደት በቅድስት ቤተክርስቲያን ሰማያዊ
በቅድስት ቤተክርስቲያን ስግደት ደግሞ ሁለት ዓይነት ነው፡፡
፩.የአምልኮ ስግደት
፪.የጸጋ (የአክብሮት) ስግደት
አሁን አጠር አጠር አድርገን እንመልከታቸው፡፡
፩. የአምልኮ ስግደት፦
ይህ ስግደት የሚቀርበው የባህርይ ጌትነትና የባህርይ ገዢነት ለብቻው የባህርይ ገንዘቡ ለሆኑለት ለእግዚአብሔር ብቻ፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን የአምልኮ ስግደት ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም አይቀርብም፡፡ ከእግዚአብሔር በቀር የባህርይ አምላክ ሰማይና ምድርን ፈጥሮ የሚገዘና የሚያሰተዳድር ሌላ አምላክ ከቶ የለምና፡፡ ከእግዚአብሔር አምላካችን በቀር ሌላ አምላክ ማነው? እርሱን የሚመስለውና የሚተካከለውስ ከቶ ማነው?
"ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፡፡ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ፡፡
በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፡፡ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም...እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፡፡" /ዘጸ.፳:፪/
እንግዲህ ከእምነታችን ውጪ ሌላ አምላክን እንድናምን ሊያስገድደን የሚችል ማነው? ከአሚነ ሥላሴ ሊነጥለን የሚችል ማነው? መናፍቃን በልባቸው ሃሳብ እየተቃጠሉ በከንቱ የሚከሱን ክስ ሁሉ ከሰይጣን የሚመነጭ የሃሰትና የማሳሳቻ ክስ ነው ብለን በአጭሩ እንለፍ፡፡ ነገር ግን ሲመረመሩ ለእግዚአብሔር እንኳ ሊሰግዱ የማይፈቅዱ መናፍቃን በቤቱ ጸንተው በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት ፡ በአጽዋማትና ፡ በሰሞነ ህማማት ወዛቸው እስኪነጥፍ ለእግዚአብሔር አምላክ የሚሰግዱ ኦርቶዶክሳውያንን ለመንቀፍ ሲነሱ ያለ አንዳች እፍረት መሆኑ ህሊና ቢስነታቸውንና የሰይጣን ማደሪያዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
፪. የጸጋ ስግደት
ከላይ እንደገለጽነው መናፍቃኑ የዚህ አይነት ስግደት በመጽሐፍ ቅዱስ ከቶ የሌለና እግዚአብሔርም ከቶ የማይፈቅደው መሆኑን በድፍረት በመናገር በሀሰተኛ ትምህርት ብዙ ምዕመናንን ከበረት ቤተክርስቲያን አስወጥተውበታል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተክርስቲያንን የሚነቅፉትና በአጸያፊ ቃላት የሚሰድቡት የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደትን ለመቃወምና በዚህም የኑፋቄ አስተምህሮ ነብሳትን ለመንጠቅ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡
አምላክ የባሕርይ ጌትነትና፡ የባሕርይ ገዢነት ለብቻው የባህርይ ገንዘቡ መሆናቸውን ከላይ ገልጸናል፡፡ የጸጋ ገዢነትንና የጸጋ ጌትነትን ለሰው እንደሰጠው እንዲሁ፡፡ ከመመለክ ጋር የሚሆን የአምልኮ ሰጊድ የባህርይ ገንዘቡ ሲኾን በጸጋ ከመግዛትና በጸጋ ከሚሰጠው አክብሮት ጋር የሚደረግ የጸጋ ሰጊድም ለቅዱሳን ይደረግ ዘንድ እግዚአብሔር ወዷል፡ ፈቅዷል፡ አዟልም፡፡
ከዚህ ቀጥለን መናፍቃኑ ለፍርድ ተሸክመውት እየዞሩ ለኑፋቄ እያጣመሙ ስተው ከሚያስቱበት መፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እናስቀምጥ፡፡
የጸጋ ስግደት በቅዱስ መጽሐፍ
"ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውምን አምላክ አግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሱ ሰገዱ፡፡" /፩ዜና.፳፱:፳/
መናፍቃን እግዚአብሔር እንደ ልቤ ያለው ቅዱስ ዳዊት በነገሰበት ዘመን እስራኤላውያን ለቅዱስ እግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት፤ ለንጉሳቸው ክቡር ዳዊት የጸጋ ስግደትን ማቅረባቸውን ይህም ከትሁታን የእግዚአብሔር ልጆች የሚጠበቅና እግዚአብሔርም የሚወደውና የሚፈቅደው እንደሆነ እንዴት አታስተውሉም? እኛ ቅዱሱን መጽሀፍ በእውነት ስናምን እናንተ ደግሞ ከቃሉ ጋር ስትለያዩ እንዲህ እናስተውላለን፡፡
"ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር፡፡ ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፡፡" /ዘፍ.፲፱:፩/
ቃሉ ላይ ለማመጽና በማስተዋላችሁና በትዕቢት ላይ ለመመካት ያስመረጣችሁ እንዴት ያለ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ ትዕቢት የማን ባህሪ ናት? ትዕቢተኛስ ማነው? እንግዲህስ ልትነቅፉት የምትወዱት ማንን ነው? ሎጥን ወይንስ ሁለቱን መላእክት? ወይንስ እግዚአብሔርን?
"እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ ሰገደም በግምባሩም ወደቀ፡፡"
/ዘኁ.፳፪:፵፩/
የበለዓም የታወሩ አይኖችን አግዚአብሔር እስኪከፍታቸው ድረስ መልአኩን ማየት አልተቻለውም፡፡ አይኖቹ እስኪከፈት ድረስ በማስተዋል አህያው ትበልጠው ነበር፡፡ ማየት ያልቻለ ውሳጤያዊ አይኑን እግዚአብሔር በቸርነቱ ባበራለት ግዜ ግን ብርሃናዊውን ግሩም የእግዚአብሔርን መልአክ ከፊቱ ተመለከተው፡፡ ያኔ ለመልአኩ የጸጋ ስግደትን ሰገደ፡፡ አሁንስ ማንን ትከሳላችሁ? የዕውሩን አይኖች አብርቶ መልአኩን እንዲመለከትና የአክብሮት ስግደት ይሰግድ ዘንድ የፈቀደለትን እግዚአብሔርን? ወይስ የጸጋ ስግደት ሲቀርብለት ሳይቃወም የተገባውን አክብሮት የተቀበለውን ቅዱሱን መልአክ? ወይንስ ከእውርነትና ከቁጣ መንፈስ ተመልሶ ትህትናን በእግዚአብሔር ፊት የፈጸመውን በልአምን? ወይንስ ዘኁልቅን እንሰርዘው? ወይስ የተረት መጽሐፍ እንበለው? በእናንተ ዘንድ አህያ እንደተናገረች የሚናገር መጽሐፍ እንደምን ቅዱስ ተባለ? ከማስተዋላችሁና ከጥበባችሁስ የተነሳ ይህንን የደብተራውን የሙሴን መጽሐፍ እንደምን ተቀበላችሁት? ይህስ ቃል ከሮሜ ምዕራፍ ስምንት ከሰላሳ አራተኛዋ ቁጥር ጋር እንደምን ቅዱስ ተባለ?
"እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው? አለው፡፡" /ኢያ.፭:፲፬/
ፀሀይን በገባዖን ያቆመው አባታችን ኢያሱ በማስተዋል ጠየቀ፡፡ "እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን፡፡ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ፡፡" ብሎ በቅንአት አሰምቶ የተናገረ ኢያሱ ግን ለሰራዊት አለቃ ለቅዱሱ መልአክ የጸጋ ስግደትን ሰገደ፡፡ የትህትናና የፍቅርንም ስራ ሰራ፡፡ መናፍቃን ሆይ ኢያሱ ለጣኦት እየሰገደ ይሆን? ወይንስ "ከኔ በቀር አማልክት አይሁንላችሁ ለማንም አትስገዱ አትገዙ፡፡" ያለውን አምላካዊ ትዕዛዝ እየሻረ ይሆን? ወይንስ የመላእክት አለቃ ሃያሉ መልአክ ለባለ ራዕዩ ዮሀንስ ከተገለጠው መልአክ ተለይቶ ያልተፈቀደ ስግደትን የሚፈቅድና በዝምታ የሚያልፍ ይሆን? እባካችሁ ወገኖች ቃሉን ማሸነፍ ከፍጥረታት ወገን ለማንም የሚቻል አይደለም፡፡
መልአኩ ግን የጸጋ ሰጊድ እንጂ የአምልኮ ሰጊድአለመሆኑን ስላወቀ ጫማህን አውልቅ ብሎ በክብር ላይ ክብር ከመጨመር በቀር ለምህን ለኔ ትሰግዳለህ? እንዳታደርገው ተጠንቀቅ የሚልን ቃል ከቶ አልተናገረም፡፡ ወይንስ መጽሐፈ ኢያሱንም እንቀንሰው?
"እርሱም በፊታቸው አለፈ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ፡፡" /ዘፍ.፴፫:፫/
በእውነት ከህያውና ከመለኮታዊ ቃሉ ብዙ ጥቅሶችን መጥቀስ እንችላለን፡፡ በእግዚአብሔር የሚታመን ቃሉንም ለሚሰማና በእውነትም ለሚመካ አንዲት ቃል በቂ ናት፡፡ መናፍቃን ሆይ በዚህች ሰዓት ምን ታስቡ እንደሆነ እኛ አንዳች አናውቅም፡፡ በእውነቱ ቃሉ ካላሸነፋችሁ በምን አቅማችን እኛ እናንተን ልናሸንፍ ይቻለናል? ቃሉ ግን ይፈርዳል፡፡ አንዲት ፊደል እንኳ ያለ ምክንያት አልተፃፈምና፡፡ እኛ እግዚአብሔርን እናምነዋለን፡፡ ትምክህታችንም እርሱ ነው፡፡ ከማስተዋላችንንና ከእውቀታችን ሁሉ በላይ ትሁታን አባቶቻችን የነገሩንን ዘላለማዊ ቃል ካለ አንዳች ጥርጥር እናምናለን፡፡ በዚህም እጅግ ሀሴትን እናደርጋለን፡፡
ቀጥሎ ያለውን ነገር ስነግራችሁ እያዘንኩ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ የተሃድሶ ተላላኪ በዚህ ርዕስ ከወጣቶች ጋር ይከራከር ነበር፡፡ ቀናኢ የነበሩ ወጣቶች የነ ኢያሱን፡ የነዳንኤልን፡ የነ ቅዱስ ዳዊትን፡ የነሎጥንና የሌሎችንም ደጋግና ቅዱሳን አባቶች የተቀደሰ የትህትና ህይወትና ሃይማኖት እየጠቀሱ አላፈናፍን ይሉታል፡፡ የክፉ መንፈስ ማደሪያ የሆነው ይህ ሰው በመጨረሻ ሁሉንም ሰው ያስደነገጠ ቃልን ተናገረ፦ "ለመላእክት፡ ለሰዎች፡ ለታቦትና ለቤተ መቅደስ እንደሰገዱ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉ ሁሉ ተሳስተዋል፡፡ እኔ የምሰማው አስቀድሞ በዘጸአት ላይ ራሱ እግዚአብሔር በቃሉ "አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም" ካለው ውጪ አልቀበልም፡፡" አለ እሱ የጠቀሰውን ጥቅስ ትርጓሜና አገባብ ስቀድመው ገልጸውለት የነበሩ ቢሆንም ለማመን ፈፅሞ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ተሰነባብተው ተለያይተዋል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትን፡ ነቢዩ ዳንኤልን፡ ኢያሱንና ቅዱስ ዮሀንስን "ተሳስታችሁዋል" ብሎ ለመናገር የደፈረ ትውልድ መምጣቱ ጊዜው ወደ ማምሻ መቃረቡን ይጠቁማል፡፡
እንግዲህ በዚህች አነስተኛ ጽሁፍ የመናፍቃን ሀሰተኛ የኑፋቄ አስተምህሮንና የቅድስት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠኑ በማንሳት የነጣቂዎችን ማንነት የበለጠ ለማሳየት ሞክረናል፡፡
መጽሀፍ ቅዱስንም መናፍቃኑ ተሸክመው የሚዞሩት ሰዎችንን በማሳት የድህነት መገኛ የጸጋውም ዙፋን ከሆነች ከቅድስት ቤተክርስቲያን መለየት መሆኑን ለማሳየት ሞክረናል፡፡
እስካሁን ከተጠቀሱት የመጽሀፍ ቅዱስ እውነቶች መካከል ለሚያምን ክርስቲያን አንዷ በቂ ብትሆንም መናፍቃን ወገኖች ወደ ዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ አስራ ዘጠኝ ጥቅስ መልአኩ ለኔ አትስገድልኝ ብሎታል ወደሚል ክርክር እንደሚሄዱ ምንም አያሻማም፡፡ የቃሉ ደጅ ተዘግቶባቸው ከምስጢርም ተለይተው ነው እንጂ የመልአኩ ንግግር የትህትና መሆኑን በሌላ ጽሁፍ ይዘን እንቀርባለን፡፡ ስለ ሌሎቹ መላእክት ለመናገር አቅም ባይኖራቸውም የትህትናውን ነገር ጌታ የሚወደው ሃዋርያ ቅዱስ ዮሃንስ ለሁለተኛ ጊዜ ሰግዶ አሳይቷቸዋል፡፡
ሊከራከሩት የማይቻላቸው እውነት
እስካሁን የእግዚአብሔር ቅዱሳን ያቀረቡትን የጸጋ ስግደት አስመልክቶ ከቅዱስ መጽሃፍ የተለያዩ ጥቅሶችን ስናነሳ ቆይተናል፡፡ መጽሀፍ ቅዱስን እናምናለን የሚሉት መናፍቃን ላለማመን ወደ ሌሎች የክህደት ሃሳቦች ሊሄዱ እንደሚችሉ ለማወቅ ብዙ መመራመርን የሚጠይቅ አይደለም፡፡ በመጨረሻ ጽሁፋችንን የምናበቃው እራሱ አምላካችን ህግን አስቀድሞ የሸራው አምላክ ለቅዱሳን የሚቀርበውን የጸጋና የአክብሮት ስግደትን እንደሚወድ፡ እንደሚፈቅድና እንደሚቀበል የተናገረውን ቅዱስና እውነተኛ የሆነው ቃሉን በመጥቀስ እናብቃ፦
"እግዚአብሔርም አለ፡ ይሁዳ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሀል እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ፡፡" /ዘፍ.፵፱:፰/
"አህዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ ለወንድምችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፡፡" /ዘፍ.፳፯:፳፱/
"እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፡፡ የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውንም ታስረው ይከተሉሃል በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፡፡ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል፡፡" /ኢሳ.፵፭:፲፬/
"በፊላድልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ (አለቃ)፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማህበር አንዳንዶችን እከጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አጀርጋቸዋለሁ፡፡" /ራእ.፫:፱
በእውነት ከአሚነ ሥላሴ፡ ከወልድ ዋህድ ክርስቶስ ፍቅር፡ ከድንግል ማርያም እቅፍ፡ ከቅዱሳን፡ ከጻድቃን፡ ከሰማዕታት የብርሃን ከተማ ከፍፅምት ተዋህዶ እምነት እግዚአብሔር አይለየን፡፡ በውጭ ላሉ ወገኖችም ልቦነ ሰጥቶ በንስሀ ወደ ቤቱ ይመልስልን፡፡ አሜን፡፡
"እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት፡ መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያልና የሚታየው ሁሉ በብርሃን ነውና፡፡" /ኤፌ.፭:፩/.
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡አሜን ይቆየን