Saturday, April 13, 2019


በእንተ ዓይነ ጥላ
እጅጉን በዓይነ ጥላ የተቸገራቹ እና በጸሎት ብቻ የሚሆን መፍትሔ ካለ ብላቹ በተደጋጋሚ ላቀረባቹት ጥያቄ እኔሆ አስማተ ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት።
ለፍርሀት :ሽብር :ድንጋጤ: ጥላቻ :መሰናክል :ፈተና:ዓይነጥላ፡ችግርማስዋገጃ ጸሎት
ይህ ጸሎት የሚመለከተው ሰው ብቻ ብንጽህና ይጸልየው።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ ጸሎት በእንተ ዓይነ ጥላ ወዓይነ ቁራኛ ወሌጌዎን ፍልጸት ወቁርጸት መጋኛ ወጉስምት እሎንተ ቃላተ አስማተ ክቡራተ እምኩሉ ጽሑፋት ዲበ ክነፊሁ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ዘፀጋም ኤኮስ :አስሌ :ኤፓ :ኤፓስ: ኤንከም: ምስ: ሌከፎ: ፋሌ: ጥሎኬ :ወአርናኬ: ብላዕ: አባሌዕ: አሜኤ: አዎጽ: አቂ: ፒሎ :ፒክ :ኬብርዩ: የየክ :የኬ: ብርሄል :ያዳ: ያብሲት: ፀፀፀ :ሎሎሎ :የየየ :ለክብማኤል: አበዕ: ቤቃ: ቤቃ: ቤቃ :ጼቃ :ጼቃ :ጼቃ :የውጣ :ቤጣዓብይ ስሙ እግዚአብሔር አነሂ ተአመንኩ በትንብልናሁ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ወበአስተብቁዖታ እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ ወበስእለቱ ቅዱስ ገብርኤል ዜናዊ ትፍስህት (ትስብእት) አድኅነኒ እምኩሉ ኃይለ ጸላኢ ወጸር ወእምኩሉ ኃይለ አጋንንት ወመናፍስት ርኩሳን ወእምኩሉ ኃብተ መሠርያን ለገብርከ (ስም) ገብረሚካኤል ዘየማን እሎንተ ዓብያተ አስማተ ሊካዕ :አሜሌኬ :ኤንካዕ :ካዜዕ :ኤርናኬ: ኬምካዮን :ፔካ :ጌሎ :አስኤሌቅ: ያሬሙ: ያብሲት: ጓጓጓ: እብሲት: ፌኤ :ኤልባ :ኤጣሴ: ብስለኪፍ: እርህሎ: አዎጽእሙንቱ አስማት ይዓብዩ እምኩሉ ቃላት ዘበነገረ እብራይስጥ ጥዩቅ ነገር ወለእመ አጽሓፈ ዘንተ መጽሓፈ ክቡረ ኢይፍልጥ ወኢይዝሩ አላ ይዕቀቦ በመካን ቅዱስ ከመ ይኩኖ ለሕይወት ወለ መድኃኒት ወልታ ወለመግረሬ ጸር ወንስተት ኃይለ ጸላኢ ወጸር እለ ይሓውሩ በሌሊት ወበመዓልት ይርሓቁ ወይጉየዩ በመዓቱ እግዚአብሔር ጸባዖት ዘወረደ በእደ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ወበጸሎቱ ለቅዱስ ገብርኤል ዜናዊ ብስራት ወበ፺ ነገደ መላእክት ወበ ሊቃነ መላእክት ድርገታት ወበጸሎቱ ወ፬ ካህናተ ሰማይ ወበጸሎተ እንስሳ ወበጸሎታ እግዝእትነ ማርያም ምክሀ ኩሉ ፍጥረት ወላዲተ መድኃኒት ይርሓቁ አጋንንት ወሰይጣናት የኩኤል :ለካኤል :ሙዳኤል :ፓፒሮስ: ወፎነስርበዝንቱ አስማት ዘወረደ በእደ ሚካኤል አድኅነኒ እምዕደ አጋንንት ለገብርከ (ስም)ገብረሚካኤል::
ይህ ጸሎት ጧት ጧት ሁሌም በንጹህ ውኃ ላይ ቢጸለይ እና እራሳችን በመርጨት እንዲሁም በመጠጣት ከተለያዩ የክፉ መናፍስት ወጥመድ የሚታደግ ጸሎት ነው።
ከሴት ዛር ፡ከወንድ ዛር ፡ዓይነጥላ ፡ከድግምት፡ ከሥራይ ከቡዳ ፡ይከላከላል። ይህ ህቡእ ስም ከድርሳነ ሚካኤል መጽሓፍ የሚገኝ ከተለያዩ አድባራት ገዳማት በልዩ ሁኔታ ለተጠማቂዎች የሚጸለይ ጸሎት ነው። አቡነ ዘበሰማያት በል

የመተት አጋንንት ከዓይነ ጥላ የሚለይበት እና አንድ የሚሆንበት
በቀሲስ / ሄኖክ /ማርያም
ተወዳጆች ሆይ ከዚህ በፊት በዓይነ ጥላ መንፈስ መግቢያ ላይ አጋንንት ዓላማቸው አንድ ቢሆንም በሥራ ድርሻቸው እና በተንኮል ተልዕኮአቸው የተለያዩ መሆናቸውን በሰፊው አይተናል፡፡ በዚህ ክፍል የመተት እና የዓይነ ጥላ አጋንንት አስገራሚ አንድነታቸው እና ልዩነታቸውን እናያለን፡፡ ይህን እንድታውቁ የምፈልገው ለግንዛቤ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ በአጋንንት ተንኮል ውስጥ ምን ያህል አጋንንታዊ ሱታፌ እንዳለው እንድትረዱና ሰው መልአክም ሰይጣንም የመሆን ሁለት ተቃራኒ ጠባይ በውስጡ እንዳለው እንድትገነዘቡና የፈተና ስልታቸውን እንድትሉ ነው፡፡
ወዳጆቼ ሰው የቅድስና ጠባይን ከተላበሰ ሥጋ ለበስ መልአክ መሆን ይችላል፡፡ ሰው የርኩሰትን ጠባይ ከተላበሰ ሥጋ ለበስ ሰይጣን መሆን ይችላል፡፡ በተለይ የለበሥነው ሥጋ የዕድቅ አደጋ ስለሆነ ከመልአካዊ ጠባይ ይልቅ ሰይጣናዊ ጠባይ በእኛ ሊታይ ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ሰው ሲከፋ ባለ ሁለት እግር አውሬ ይሆናል›› የሚባለው፡፡
መተት ከዓይነ ጥላ አጋንንት ጋር አንድ የሚያደርገው ሁለቱም የሰውን ልጅ ውድ ሕይወት ማበላሸት፣ውጥኑን፣እቅዱን ማኮላሸት ላይ ስለያተኩሩ ነው፡፡ መተትም ዓይነ ጥላም በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሕይወትን ከማበላሸት እስከ ማጥፋት ይደርሳሉ፡፡ ሁለቱም አለን፣እጄ ገባ፣እርግጠኛ ነኝ በምንላቸው ነገሮቻችን ላይ የሚያደርሱብን ስውር ጥቃት አንድ ነው፡፡
መተት እና ዓይነ ጥላ በዕድላችን፣በእውቀታችን፣በትምህርታችን፣በእጮኝነት እና በትዳር ሕይወታችን እንዳንጠቀም ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ድግሱ ድረስ የመደንቀር፣የማበላሸት ሥራን ይሠራሉ፡፡ ሁለቱም አሉኝ በምንላቸው ነገሮች እንዳንጠቀም የመጠርቀም ሥራን ይሠራሉ፡፡ ሁለቱም ተስፋ በጣልንባቸው ከመቶ ፐርሰንት በላይ እርግጠኛ በሆንባቸው ነገሮቻችን ላይ፣አጋንንታዊ የበላይ በመሆን በግልጽና በስውር፣የማይታይ ምስማር በመሆን ጠስቀይ ይይዙብናል፡፡ ሲላቸው በራሳቸው ሲላቸው በሰው እያደሩ፣የእኛን ነገር ገና ከጅምሩ እየገረገሩ ያበላሹብናል፡፡ መተት እና ዓይነ ጥላ የሰው ልጅ ዳግም የማያገኝውን፣ተመልሶ የማይኖረውን ውድ ሕይወቱን በማባከን፣የያዘውን በማስጣል ብሎም በመንጠቅ አንድ ናቸው፡፡
መተት እና የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚለያቸው ወይም አንድ የማያደርጋቸው ደግሞ አለ፡፡ ይህም መተት በደጋሚዎች ወይም በጠንቋዮች በመጎተት ሰውን የሚቆራኝ አጋንንት ነው፡፡ መተት በሰው እድል የሚቀና፣በሰው መልካም ሕይወት በብግነት የሚኖር ሰው በሚበላ በሚጠጣ፣በቁስ ወዘተ በማስደገም የሚያቆራኘው አጋንንት ነው፡፡
ዓይነ ጥላ በደጋሚዎች የሚጎተት አጋንንት አይደለም፡፡ እራሱን ችሎ፣ክፋቱን ተንኮሉን ጠቅልሎ ወደ ሰው ሕይወት የሚገባ አጋንንት ነው እንጂ በደጋሚዎች የሚቆራኝ አይደለም፡፡ ዓይነ ጥላ የሰውን ልጅ ከማኅፀን ጀምሮ በጽንስ ጊዜ በመቆራኘት አብሮ የሚያድግ፣የሰውን ሕይወት የሚያጠወልግ አጋንንት ነው፡፡ መተት ግን ድንገት ወደ እኛ ሕይወት በሰው ክፋት የሚመጣ አጋንንት ነው፡፡
ዓይነ ጥላ የማንም አጋንንታዊ ድግምት የማያዘው በራሱ የክፋት መንገድ የሚራመድ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ በእርግጥ መተት ገና በማኅፀን ባለ ጽንስ ላይ ቢደገምም መተትን ወደ ሰው ሕይወት ለማስገባት ገፊ አካላት ያስፈልጋል፡፡ ዓይነ ጥላ ግን ዕድላችን ላይ በመቅናት ሰተት ብሎ የሚገባ ነው፡፡ መተት በሰው ቅናት የሚገባ አጋንንት ሲሆን ዓይነ ጥላ እራሱ መንፈሱ በእኛ በመቅናት የሚገባ ነው፡፡
ዓይነ ጥላ በውስጣችን ከገባ በኃላ እራሱን እየቀያየረ በሕመም እየተመሰለ ይቀመጣል፡፡ መተትም ውስጣችን ከገባ ደዌ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ ልዩነታቸው ዓይነ ጥላ አንዴ ውስጣችን ከገባ እንደ ግል ይዞታው ተደላድሎ ይቀመጣል፡፡ መተት ግን ውስጣችን ከገባ በኃላ እድሳት የሚባል አጋንንታዊ ሥርዓት አለው፡፡
እድሳት ማለት አንድ ሰው ላይ በመልካም ነገሩ መተት ሲመተትበት፣የሚያስመትተው ሰው በደጋሚው ወይም በመታቹ በኩል ለአጋንንቱ ግብር ያቀርብለታል፡፡ ለምሳሌ ገንዘብ፣በግ፣ደም ወዘተ ያቀርባል፡፡ ይህንን ያስደገመ ቀን ያቀረበውን ግብር በየ ዓመቱ ሊያቀርብ አጋንንታዊ ውል ይገባል፡፡ ይህንን የሚያደርገው የሰውን እድል ስለወሰደ በዛም ስለሚጠቀምበት ከሰው የወሰደው ዕድል፣እውቀት፣የትዳር፣የሥራ እድል ወዘተ በአጋንንት ተጠብቆ እንዲቆይለት እንዲጠቀምበት የሚያደርገው ነው፡፡
ብዙ ጊዜ መተት የተመተተባው ሰዎች ከአጋንንቱ በቀላሉ መላቀቅ የሚያቅታቸው በአጋንንቱ እና በሚደገምበት ሰው መሃል ያለው አስደጋሚው ሰው በየዓመቱ ወይም በየወራቶቹ በተደገመበት ሰው ስም ለአጋንንቱ ስለሚገበር የተመተተበት ሰው ሲታደስበት አጋንንቱ እንደ አዲስ ወደ ውስጡ ይገባል፣ጤና ያጣል፣የጀመራቸው ነገሮች በአስገራሚና ለማመን በማያስችል ሁኔታ ይበላሻል ወዘተ፡፡
አንድ ሰው በተለይ መተት የተመተተበት ሰው መተቱ ሲታደስበት የሚያሳየው ጠባይ አለ፡፡ ይህም በድንገት ጭው የሚል ስሜት መሰማት፣ያለ ምክንያት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባት፣መረበሽ፣መጨናነቅ፣ፍርሃት መሰማት፣የሆነ የማናውቀው ነገር ውስጣችን ሲገባ መሰማት፣እራስን ስቶ መውደቅ/ይህ መንፈሱ ውስጣችን ሲገባ ነው/ በጠራራ ፀሐይ ብርድ ብርድ ማለት፣ውልብ ብሎ ሰውነታችንን የሚከብድ ስሜት መሰማት፣በድንገት የልብ ምት መጨመርና ዝብርቅረቅ የሚል ስሜት መሰማት፣ከፍተኛ ድንገተኛ የሰውነት ድካምና የመክበድ ስሜት መሰማት፣ሰላም ማጣት፣ድንገተኛ የባሕርይ ለውጥ ማሳየት፣ያለ ምክንያት ብስጭት ብስጭት ማለት፣ማዞር መቅለሽለሽ፣ጭንቅላት እና ልብ ላይ ጭንቅ የሚል ስሜት መሰማት፣ጩኽ ጩኽ የሚል ስሜት ከውስጥ መግፋት፤እጮኛሞች እና ባለ ትዳሮች ከሆኑ ድንገት የማስጠላት እና የመጥላት ስሜት ውስጥ መግባት፣መሳደብ፣እንለያይ ማለት፣የትዳር አጋርንና ልጆችን መጥላት፣ያለ ጥፋት መምታት ወዘተ ሊከሰቱብን ይችላል፡፡ ስለዚህ የተመተተበት ሰው መተቱ ሲታደስበት እንኳን ለሰው ለራሱም የማያውቃቸው የሚይጨበጡ የባሕርይ ለውጦችን ያሳያል፡፡
ለምሳሌ በመጠጥ የተመተተበት ሰው በስንት ጸሎት እና ጸበል መጠጡን ከተወ የታደሰበት ቀን ንጉልያው እስኪዞር ድረስ ጠጥቶ ይሰክራል፡፡ በእጮኛውና በትዳሩ ላይ በመቅናት የተመተተበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን ከእጮኛውና ከትዳር አጋሩ እና ከልጆቹ ጋር ያለ ምክንያት ከፍተኛ ጠብ ውስጥ ይገባል፡፡ በእውቀቱ የተመተተበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን በዛን ሰሞን ደንዝዞ ፈዞ ይከርማል፡፡ በገንዘቡ የተመተተበት ሰው ገንዘቡ ከኪሱ ለመውጣት የሚያጨበጭቡ ይመስል ያለ ምክንያት ይወጣል፡፡ ግን በምን እንዳወጣው፣ገንዘቡን የት እንዳሰረሰው፣ምን ቁም ነገር ላይ እንዳዋለው አይውቅም፡፡ ሌላም ሌላ …. በአጠቃላይ እድሳት ማለት ከአጋንንቱ ጋር በሰው ሕይወት እና እድል ላይ ውል ማራዘም ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በሰው ሕይወት ላይ በአጋንንት ስውር ምስጢር መቆመር ማለት ነው፡፡
ተወዳጆች ሆይ መተት ከዓይነ ጥላ አንዱ የሚለይበት መተት በምንበላው ምግብ፣ በምንጠጣው መጠጥ፣በምንለብሰው የውስጥ እና ውጭ ልብስ/በላብ በወዝ/ በምንይዘው ቁስ ወዘተ ስለሚደገም በቀላሉ ሕይወታችን ሊደረመስ፣ጤናችን ሊቃወስ ይችላል፡፡ ሌላው መተት ከዓይነ ጥላ የሚለይበት ምክንያት መተት አደገኛና ገዳይ መሆኑ ነው፡፡ ምንክያቱም መተት በመርዝ መልክ ሊሠራ ስለሚችል የተመተተበትን ምግብ የበላ ወይም መጠጥ የጠጣ ሰው በድንገት ሊሞት ይችላል፡፡ በተለይ ወደ ሆድ በሚገቡ ነገሮች አጋንንቱ በሰውነታችን ሕዋሶች በመሰራጨት፣ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል፡፡
መተት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ በልዩነታቸው መተት የሚከብድበት አንዱ መተት አጋንንት እራሱን መቀየር መቻሉ ነው፡፡ መተት በሆድ ውስጥ አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሻይ፣በጠላ፣በሚሪንዳ መተት ተመትቶ ቢሰጠው ያንንም ቢጠጣ ወደ ሆዱ ከገባበት ቀን ጀምሮ ጤና ማጣት፣ህመም መሰማት ይጀምረዋል፡፡ ይህ በሚጠጣ ነገር ወደ ሆዱ የገባው መተት ሰውዬው ሳያውቀው ከቆየ፣ሥጋዊ በሽታም ከመሰለው በጊዜ ሂደት ሆዱ ውስጥ የገባው መተት እራሱን በመቀየር እባብ፣እንቁራሪት፣አይጥ ወዘተ ሆኖ ውስጡ ተቀምጦ ሥጋውን በመብላት ደሙን በመጠጣት ለከፍተኛ ጤና መታወክና ጉዳት ይዳርገዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሊገድለውም ይችላል፡፡
ዛሬ ሆዳችንን እያመመን፣የሆድ ህመማችን ትልቅ ጭንቀት ፈጥሮብን በየ ሆስፒታሉ ሄደን መፍትሔ የምናጣው መተት ቢሆንስ? ምክንያቱም በመተት ወደ ሆድ ገብቶ ደዌና አውሬ ሆኖ የተቀመጠው ነገር በሕክምና ምርመራና መሣሪያዎች አይታይም ይሠወራቸዋል፡፡ ሴቶችም በመተት ማኅፀናቸው ላይ ደዌና አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ እንደ ጽንስ ይገላበጣል፣እንደ አውሬ ይጮኻል፡፡ በሕመም ያሰቃያቸዋል ግን በሕክምና የሕመማቸው ምክንያት አይታወቅም መፍትሔም አይገኝም፡፡ እህቶቼ መተት ቢሆን ማን ያውቃል?
ስለዚህ የመተት አጋንንት ውስጣችን ከገባ እራሱን እየቀያየረ የተለያየ በሽታ ይሆናል፡፡ በሚበላና በሚጠጣ ወደ ሆዳችን የገባው፣በቁሳቁስ ወደ እኛ የሰረጸው መተት ሆዳችንን ሊያሳምመን፣ለአእምሮ ሕመም/እብደት/ ሊዳርገን፣እጅ እግራችንን ሽባ ሊያደርገን፣ለወገብ ለልብ ወዘተ ሕመም ሊዳርገን ይችላል፡፡ መተትም አደገኛ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡
ዓይነ ጥላ ሕይወታችንን የማጎሳቆል ሥራ የሚሠራው በስውር ነው፡፡ መተት ግን በግልጥ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ በውስጣችን አሸምቆ ተደብቆ ከእኛው ጠባይ ጋር ተስማምቶ አድብቶ ነው የሚኖረው፡፡ መተት ግን ጥቃቱ የሚታይና ግልጥ ነው፡፡ የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚጎዳን በጊዜ ሂደት ነው፡፡ መተት ግን በድንገት ነው፡፡
መተት ብዙ ጊዜ የተንኮለኞች የቅናት እና የክፋት እጅ ስለሆነ ተጠንቅቀን የምናመልጠው ሳይሆን በጸሎት የምንከላከለው ነው፡፡ አንድ አባት አንድ ወጣኒን ‹‹ልጄ ጀርባህ ላይ ግንድ ከሚጫንህና ሰው ከሚጫንህ የቱ ይሻልሃል›› አሉት፡፡ ወጣኒውም ብልህ ኖሮ ‹‹አባቴ ጀርባዬ ላይ ግንድ ቢጫነኝ ሰው ያወርድልኛል፤ሰው ከተጫነኝ ማን ያወርድልኛል›› አላቸው፡፡ ዛሬም በመተት ሰዎች ሕይወታቸውን ተጭነዋቸው የሚያወርድላቸው አጥተው ከቤሰተብ፣ከትዳር፣ከሥራ ተለይተው በየ ጸበሉና በየ ገዳሙ የሚንከራተቱትን ፈጣሪ ይቁጠራቸው፡፡
ወዳጆቼ ሰውና አጋንንት በማበር በመተት በዚህ ደረጃ የሚፈትኑን፣ሕይወታችንን የሚያበላሹት አንድም ለፈተና፣ለጸጋ፤ለክብር፤አንድም በእኛ የእውነተኛ አምልኮት ድክመት ነው፡፡ ሰማያዊ አምልኮት፣ጾም፣ጸሎት ስግደት በሌለበት ሕይወታችን በመተት አጋንንት ብዙ ነገር በማጣት ብንኖር ፈጣሪን ከመውቀስ እራስን መለስ ብሎ መፈተሹ አይከፋም፡፡
አስደናቂው ነገር የመተት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ ሁለቱም ውስጣችን ካሉ ይተባበራሉ፡፡ አጋንንት ለክፉ ተግባራት እርስ በእርሳቸው ሲተባበሩ እኛ ግን ለመልካም ነገር እርስ በእርሳችን አንተባበርም፡፡ በተቃራኒው በምቀኝነት ጎራ ተሰልፈን አንዳችን ለአንዳችን ሕይወት መበላሸት ምክንያት እንሆናለን፡፡ የመተትም የዓይነ ጥላውም ሥራቸው፣ዓላማቸው ሕይወታችንን ማበላሸት ስለሆነ እራሳቸውን ላለማጋላጥ ተደብቀው ይኖራሉ፡፡ ደግነቱ ዓይነ ጥላው ከተጋለጠ፣መተቱም ይጋለጣል፡፡ አንዱ ሲያዝ አንዱም ይያዛል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ትዕግስተኛው ኢዮብ ‹‹በምድር ላይ የሰው ሕይወቱ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን›› ብሎናል፡፡ ስለዚህ በምድር እሰከ ኖርን ድረስ በሕይወታችን በአጋንንት ብርቱ ሰልፍ ሊገጥመን ስለሚችል አምልኮታችን በማጠንከር፣በጾም በጸሎት በስግደት በመበርታት ልንዋጋ ይገባል፡፡ /ኢዮ 7÷1/
‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› .ሆሴ 4÷6
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› .ኢሳ 53÷8
‹‹ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው›› ምሳ 21÷31