Saturday, December 15, 2018

ክብረ ቅዱሳን

መግቢያ                                                                  
ምዕራፍ አንድ
ቅድስና ምንድን ነው
1.1      የባሕርይና የጸጋ ቅድስና
1.2    የቅዱሳን ሕይወት
1.3    ቅዱሳን የሚባሉት ምን የፈጸሙ ናቸው
1.4    የቅዱሳን ሰዎች አስያየም
1.5    በቤተክርስቲያን ቅዱሳን ተብለው
የሚጠሩት እነማን ናቸው፡፡
1.     እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
2.    ቅዱሳን መላእክት
3.    ቅዱሳን ሰዎች
4.    ቅዱሳን መካናት
5.    ቅዱሳን ዕለታት
6.   ቅዱሳን መጻሕፍት
7.    ቅዱሳን ንዋያት
8.    ቅዱሳን ስዕላት
ምዕራፍ ሁለት                                       ምዕራፍ አራት
የቅዱሳን የገድል ሕይወት                                    የቅዱሳን አማላጅነት
2.1 ቅዱሳን መከራ የሚቀበሉት ከማን ነው          4.1 አማላጅነት
ሀ. ከፈቃደ ሥጋቸው                                 4.2 በአማላጅነት ወቅት የሚሳተፉ አካላት
ለ. ከዓለማዊያን ነገስታት                             4.3 አማላጅነት ለምን አስፈለገ
ሐ. ከመናፍቃን                                       4.4 የቅዱሳን አማላጅነት በሕይወት ሥጋ
መ. ከጠንቋዮች                                       4.5 የቅዱሳን አማላጅነተ በአፀደ ነፍስ
ሠ.ከአሕዛብ                                           4.6 ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል
ረ. ከአጋንንት                                         4.7 ሕያዋን ሙታን
2.2 ምዓርጋተ ቅዱሳን                                4.8 ማጠቃለያ
1. ንጽሐ ሥጋ                                                 ምዕራፍ አምስት
2. ንጽሐ ነፍስ                                                ቅዱሳን መላእክት
3. ንጽሐ ልቡና                                       5.1 የቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮ
ምዕራፍ ሶስት                                         5.2 የመላእክት አለቆችና አሰፈፈራቸው
የቅዱሳን ቃል ኪዳን                                  5.3 የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት
3.1 ቃል ኪዳን                                        5.4 ባሕርያዊ ሥልጣናቸውና ክብራቸው
3.2 የቅዱሳን ክብር                                   5.6 ማጠቃለያ
1. ስማቸው
2. ሥዕላቸው
3. ዐጽማቸው
4. ስግደት
3.3 የቅዱሳን መታሰቢያ
3.4 በዓላተ ቅዱሳን
3.5 የቅዱሳን የገድል መጽሐፍ
3.6 የስንክሳር መጽሐፍ



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ክብረ ቅዱሳን
መግቢያ
ክብረ ቅዱሳን ስንል ቃሉ የግእዝ ሲሆን
            ክብራቸው ስንል የቅዱሳን ግርማ ሞገሳቸው መወደዳቸው .መፈራታቸው. ማለታችን ነው፡፡ ይህም ግርማ ሞገሳቸው በእግዚአብሔር ፊት መወደዳቸው.በምዕመናን መፈራታቸው.ደግሞ በአጋንንት .በመናፍቃን. ዘንድ ነው በባሕርይው ክቡር የሆነው እግዚአብሔር ሲሆን ቅዱሳንን ዳግሞ በጸጋ አክብሮአቸዋል፡፡ ለዚህ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ክብር የተጠቀሰው ‹‹ እናንተ መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ …የክብር ንጉስ ይግባ›› ይህ የክብር ንጉስ ማን ነው፡፡ እግዚአብሔር ይላል መዝ 23፡7-10 ይህ ቃል የተፈጸመው ጌታችን ሲነሳ ነው ሐዋ 1፡9-11 እንደተጠቀሰ ከዓለም በፊት ስለነበረው ክብር ጌታችን ራሱ በወንጌል ተናግሯል ዮሐ 15፡7
የክብር ባለቤት እግዚአብሔር ቅዱሳንን በጸጋ አክብሯቸዋል ‹‹ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው›› እንዲል ሮሜ 8፡30 እንዲሁም ‹‹ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ›› ተብሏል ሮሜ 13፡7 ስለዚህ እግዚአብሔር ያከበረውን ማክበር ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው አለበለዛ ያስቀጣልና፡፡በጥቅሉ ክብረ ቅዱሳን ስንል ቅዱሳንን የማክበር ስርዓት የቅዱሳን ክብር ማለት ነው፡፡
v ክብረ ቅዱሳንን መማር ለምን አስፈለገ?
1.             እግዚአብሔር ለቅዱሳን የሰጠውን ጸጋ እንድናውቅና እርሱን እንድናመሰግን ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹እግዚአብሔር በጻዲቁ እንደተገለጠ ( እንደተመሰገነ) እወቁ›› እንዳለ መዝ 4፡3 ስለዚህ በቅዱሳን አድሮ በሚሰራው ስራ አምላክ ይመሰገናል መዝ 67፡35
2.            የቅዱሳን ፍጹም ተጋድሎና ትሩፋት ተረድቶ ራስን ለገድልና ለትፉፋት ለማነሳሳት (እንድንነሳሳ ስለሚያደርግ)
ቅዱሳኑን አብነት ማድረግ ይገባናል ሐዋርያው ‹‹ የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን ዋኖቻችሁ አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመላከታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው›› ዓለን እዕ 13፡7 በቆሮንቶስ መልእክቱም‹‹ እኔ ክርስቶስ እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ›› 1ኛቆሮ 11፡1 መንፈሳዊ ልጁ ጢሞቴዎስንም ኑሮዮን አብነት ፣ አርአያ አድርግ ብሎታል በትንቢት መጽሐፍም ‹‹ ወደ አባታቸወሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁ ወደ ሳራ ተመልከቱ›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ት.ኢሳ 51፡2 ይህ ማለት አርያአ አድርግዋቸው ምሰልአቸው ማለት ነው፡፡
3.        በቃል ኪዳናቸው እንድንጠቀም
ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ በቃል ኪዳናቸው እንድንድን ሲሆን ሙሴ በአባቶች በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ በተገባላቸው ቃል ኪዳን በመለመን ህዝቡን ከጥፋት አድኗል ዘጸ 32፡10-14 እንደተጻፈ ይህንንም ጉዳይ ዳዊት በመዝሙሩ‹‹ ሙሴ ስለ ህዝቡ ባይቆም (ባይለምን) ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተቆጣ›› አለ መዝ 105፡23 ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ›› ተብሎ ተጽፏል መዝ 88፡3
4.            መንፈሳዊ ግዴታችን ስለሆነ ( የእግዚአብሔርን ነገር ማሰብ ተገቢ ስለሆነ) ይህንን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ዋኖቻችሁን ( የጸኑትን) አስቡ›› ብሏል ዕብ 13፡7
ምዕራፍ አንድ
ቅድስና ምንድን ነው?
ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አመሰገነ ለየ መረጠ አከበረ ማለት ነው ስለዚህ ቅዱስ ማለት ልዩ ክቡር ንጹህ ምስጉን ማለት ነው ቅድስና የባሕሪና የጸጋ በመባል በሁለት ይከፈላል

1.1        የባሕሪና የጸጋ ቅድስና
1.             የባሕርያ ቅድስና ፡- ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ቅድስናው ከእግዚአብሔር የማይለይ ከማንም ያልተቀበለ ማንም ሊወስድበት የማይችል የራሱ ገንዘብ የሆነ ማለት ነው፡፡ በእርሱ ዘንድ ከቅድስና ሌላ ሊታሠብ የማይችል ርኩሰት የሌለበት ነው፡፡ስለዚህ ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ››ይባላል፡፡ ይህን ቅድስናውንም ሡራፌል ‹‹ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ             ቅድሳተ ስብሐቲከ; ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች›› በማለት ምሥጋና የባሕሪ ቅድስናውን ገልጸዋል፡፡ ት.ኢሳ 6፡3 ራዕ 4፡8
ቅድስና ለእግዚአብሔር የባሕሪው ገንዘቡ ስለሆነ ቅድስናን በጊዜ ሂደት ወይንም በትሩፋት ያገኘው አይደለም፡፡እግዚአብሔር መቸም መች ሁል ጊዜም ቅዱስ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ቅድስና ተመሳሳይ ወይም ተወዳዳሪ የለውም፡፡ ይህንንም ራሱ ሲናገር ‹‹እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅዱሱ በማለት ት.ኢሳ 40፡25
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ ከፍ ያለ ልዑል…›› ኢሳ 57፡15 ስሙም ቅዱስ ነው ሉቃ 1፡45
‹‹ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ ሥራህ ታላቅና ጽድቅ ነው አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና›› ራዕ 5፡4 ለእግዚአብሔር ቅድስና ታላቅ ክብርና ምሥጋና ልንሰጥ ይገባናል፡፡ አቻ ተወዳዳሪ የለውም ለሌላው ልንሰጥ አንችልም የባሕርይ ክብሩ ነውና፡፡
2.      የጸጋ ቅድስና፡- ጸጋ ማለት ቸርነት ምህረት በጎነት ያለ ብድራትና ያለ ዋጋ የሚሠጥ ስጦታ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ከእግዚአብሔር የሚገኝ ማንኛውም ስጦታ ሁሉ ጸጋ ይባላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ጥቅሶች መመልከት እንችላለን መዝ 15፡1 መዝ 32፡5 ዘጸ 34፡7 ሮሜ 2፡4 ቲቶ 2፡11
በባሕሪይው ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በረድኤት ያደረባቸው በጸጋ የተወሃዳቸው የሃይማኖት ሰዎች ቅዱሳን ይባላሉ፡፡ ይኸውም ሃይማኖት ለመያዝ ምግባር ለመሥራት ፍቃደ ሥጋቸውን ለፍቃደ ነፍሳቸው በማስገዛት ከክህደት ከጥርጥርና ከክፋት ከርኩሰት በመጠበቃቸው ነው፡፡ ይህንም እግዚአብሔር እራሱ ‹‹እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና  እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› ዘሌ 19፡2 በማለት ሰዎች ቅዱሳን መሆን ስለሚችሉ በቀጥታ ተናግሯል፡፡ ለዚህም ነው ቅድስ ጴጥሮስ ‹‹ ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንት ደግሞ ቅዱሳን ሁኑ›› ያለው 1ጴጥ 1፡13-16 በዳግሚት መልዕክቱም ‹‹ቅዱስ ኑሮም እገዚአብሔርንም በመምሰል እንደምን ልትሁኑ(ልትኖሩ) ይገባችኋል ብሏል 2ጵጥ3፡10-11 አንድም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመሆናችው ቅዱሳን ናቸው 1ኛቆ 3፡16-17 ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም በመልእክቱ ‹‹እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ጻድቅ ነው›› ብሏል 1ዮሐ 3፡7 ከላይ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ስንል ቅድስና የባሕሪይው ገንዘቡ መሆኑን አውቀን ነው፡፡ ቅዱሳንን ቅዱስ ስንል ደግሞ ቅድስናቸው የጸጋ (የስጦታ) መሆኑን አውቀን ነው፡፡ የጸጋ ስጦታ ልዩ ልዩ ነው እግዚአብሔር ግን አንድ ነው፡፡ 1ኛቆ 12፡4
1.2       የቅዱሳን ሕይወት
የቅዱሳን ሕይወት የሚነበብ መጽሐፍ ነው፡፡ይኸውም ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ በመኖራቸው( በህገ ወንጌል በመጽናታቸው) ነው፡፡ ፊልጵ 1፡27 በሕገ ወንጌልም ለመጽናት የቻሉት አስቀድመው ዓለምን በመናቅ ከዓለም በመለየታቸው ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሠቀለበት (ዓለም በእኔ ዘንድ ሙት የሆነበት) እኔም ለዓለም የተሰቀልኩ (እኔም በዓለም ዘንድ ሙት የሆንኩት) ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› ብሏል ገላቲ 6፡14 ዓለምን ስለመናቁም በተጨማሪ ፊልጵ 3፡7-10 ተናግሯል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም በበኩሉ ‹‹ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ ፣ በዓለም ያለው ሁሉ የሥጋ ምኞት የአይን አምሮት ስለ ገንዘብ መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም ዓለሙም ምኞቱም ያልፋል፤ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል›› ብሏል 1ኛ ዮሐ 1፡15-17 ቅዱሳን ሃይማኖት በመያዛቸው ምግባር በመስራታቸው በጾም በጾሎት በስግደት፣ በመወሰናቸው በአጠቃላይ ሰውነታቸው ቅዱስ መስዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር በመስጠታቸው ዓለምን አሸንፈዋል፡፡ ዓለምን አሸንፈዋል ማለትም በዓለም ያለውን ክፉ ነገር በመተዋቸው ዓለምን አሸንፈዋል ማለት ነው፡፡ 1ኛ ዩሐ 2፡13 1ዮሐ 4፡4 የሐ 13፡8 2ቆሮ 11፡23-29
የቅዱሳንን ሕይወት ስንመለከት  በአጠቃላይ በቅድስና በንጽህና ያጌጠ በገድልም የተመላ ነው፡ ንጽህናቸው ‹‹ ከእግዚአብሐር የተወለደ ሁሉ ኃጢያት አያደርግም›› እንደተባለው ከኃጢያት የተለዩ ናቸው 1ኛዮሐ 3፡9 ስራ ገድላቸው ደግሞ ‹‹ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ ሌሎችም መዘበቻ በመሆን በመገረፍ ከዚህም በላይ በወህኒ ፣ በእስራት ተፈተኑ፣ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ሁሉም እንዲህ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ ዓለም አልተገባቻቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻ በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ›› የሚል ተጽፏል ፡፡ ዕብ 11፡35-38 በዚህም ኑ ተከተሉኝ ያላቸውን ፈጣሪ ክርስቶስን መስለውታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 11፡1
ቅዱሳን ክርስቶስን የሚመስሉበትን ሕይወት ያገኙት በጸጋ ከብረው ነው፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሐዋርያው ጳውሎስ‹‹ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ (ወንድሞቼ ብሎ ለሚጠራቸው ቅዱሳን ለበጎ ነገር ሁሉ በኩር አብነት ይሆናቸው ዘንድ) አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኗልና አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው ፤ ያጸደቃቸውን እነዚህን ደግሞ አከበራቸው›› በማለት ገልጦታል ሮሜ 8፡29-30 ቅዱሳን በጸጋ ከብረው ክርስቶስን መሰሉት ስንል ስልጣን ተካከሉት በማለት አይደለም ለምሳሌ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መልክ ፈጣሪውን መስሎ በመፈጠሩ እግዚአብሔርን ተካከለው አያሰኝም ዘፍ 1፡26፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር ቅዱሳንን በጸጋ አክብሮ እንዴት እርሱን ራሱን እንደሰመሰላችው በሚከተሉ ጥቅሶች በማቆራኘት ጥቂቶቹን እንመለከታለን፡፡
ሀ. ኢየሱስ ክርስቶ የጽድቅ ፀሐይ ነው ት.ሚል 4፡2 ማቴ 17፡2 ቅዱሳን ዳግም
 ‹‹በአባታቸው መንግስት እንደ ፀሐይ ይበራሉ››ተብሎላቸዋል ማቴ 13፡43 ይህን የተናገረላቸው ራሱ ጌታችን ነው፡፡
ለ. ለሰው ሁሉ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣል ት.ኢሳ 9፡2 የሐ 1፡9 ‹‹እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ›› ዮሐ 9፡5 ዮሐ 12፡46
‹‹ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ›› ማቴ 5፡16 ‹‹የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ እንደ ብርሃን ትታያላችሁ›› ፊል 2፡15 ‹‹ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም›› የሐ 8፡12
ሐ. ‹‹መልካም እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ስለ በጎቹ ነፍሱን ያኖራል›› ዮሐ 10፡11
1ኛ ጴጥ 2፡20 ዕብ 13፡20 ‹‹ ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጎቼን አሠማራ ዮሐ 21፡15-17 ‹‹ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ… የእረኞቹ አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ›› 1ኛ ጴ 5፡2-4
መ. ‹‹እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉስ ነው በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ›› መዝ 73፡12 ያንንም መገለጥ የነገስታት ንጉስና የጌቶች ጌታ ያሳያል›› 1ኛጢ 6፡16 ራዕ 19፡16 ‹‹ ለዳግመኛ ልደት    የሰው ልጅ በክብር ዙፋኑ በሚቀመጥነት ጊዜ እናንተ ዳግም ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ልትፈርዱ በአሥራ ሁለቱ ዙፋን ትቀመጣላችሁ››
1.3       ቅዱሳን የሚባሉት ምን የፈጸሙ ናቸው?
ቅዱሳን እንደየ ገድላቸውና ትሩፋታቸው በተለያየ አከፋፈል ሊከፈሉ ቢችሉም በአጠቃልይ ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የፈጸሙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
1.             ያላቸውን ሁሉ ትተው አምላካቸው የተከተሉ ናቸው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንን ‹‹ እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ ጌታችንም‹‹ እውነት እላችኋለው እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ልትፈርዱ በአሥራ ሁለቱ ዙፋን ትቀመጣላችሁ›› ብሎ በዚህ ዓለም ያስተማሩት ትምህርት የፈረዱት ፍርድ በዚያም የማይከለከልባቸው መሆኑን ከገላጸ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ ምን እናገኝ ይሆን ላለው? ‹‹ብሎ ለጠየቀው ጥያቄም ሲመልስ ‹‹ ስለ ስሜም ሴቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘለዓለምንም ህይወት ይወርሳል›› በማለት ዋጋቸው ፍጹፍ መሆኑን ገልጻል ማቴ 19፡27-30 ማር 10፡29-31 ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን የተከተሉት ሁሉን ሀብት ንብረት ቤተሰብን ሁሉን ትተው ነው ነቢዩ ኤልሳም እንዲሁ ኤልያስን የተከተለው አስራ ሁለት ጥምድ በሬ እያረሰ ሲጠራው በሬዎቹን አርዶ ለህዝቡ አብልቶ ሀሳቡ ከዓለም እንዳይቀርበት ሁሉን ትቶ ነው ስለዚህ ቅዱሳን እግዚእብሔርን ለማገልገል ሁሉን ትተው እሱን ብቻ ተስፋ አድርገው አለምን ከነ ምናምንቴዋ ንቀው ትተው ነው፡
2.            ህይወታቸውን በተጋድሎ ያሳለፉ ናቸው
ጌታችን‹‹ የሠው ጠላቱ ቤተሰቦች ናቸው›› ብሎ ባስተማረው መሠረት የሰው ጠላቱ ከሩቅ አይወጣም መንፈሳዊ ሰው ረቂቅ ጠላት ያለበት ስለሆነ ሁል ጊዜ የተዘጋጀ ሆኖ መኖር አለበት ቅዱሳንም ይህን ጦርነት አውቀው በፈተና የጸኑና እስከ ደም ጠብታ ድረስ የታገሉ ናቸው ያእ 1፡12 ዕብ 12፡4 ስለዚህ ፈተና ከሁሉት አቅጣጫ ይመጣል እነዚህም ውስጣዊና(ውስጣዊ) ውጫዊ (አፍአዊ) ፈተናዎች ናቸው፡፡
  1. ውስጣዊ ፈተና ይህ ፈተና አንድ ሰው ‹‹ሰው›› በመሆኑ የሚፈተነው ፈተና ነው ይከውም ከሰዋዊ ባሕርይ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ከዚህ ፈተና የሚሸሹት ሜዳ የሚሸሸጉበት ጓዳ የለም ሰው የነፍሱና ሥጋ ተዋህዶ ውጤት በመሆኑ በዚህ ዓለም ሕይወት ሲወጣ ናሲወርድ ይኖራል፡፡ ሰው በዚህ ዓለም ሕይወቱ ራሱን ለፈጣሪ ለማስገዛት ከራሱ ጋር ብርቱ ተጋድሎ ማድረግ ግድ ይለዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛል፡፡ እነዚህም እርስ በእርሳቸው ይቀዋወማሉ፡፡ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም›› ገላ 1፡17 ብሎ የገለጸው ይህንን የሰው ሕይወት ያለበትን ብርቱ ጦርነት ለማስገንዘብ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ሰውነቴን እየጎሰምኩ አስገዛዋለህ እንዳለ ሐዋርያው ፍቃደ ሥጋችን ለነፍሳችን በጾም በጾሎት በስግደት ልናስገዛ ይገባናል፡፡ መዝ 68፡10
2.            አፋዊ (ውጫዊ) ፈተና፡- ሰው የሚፈተነው በውስጣዊ ጾር ብቻ ሳይሆን በውጫዊ ጭምር ነው፡፡ይኸውም በቤተሰብ በጓደኛ በዘመድ በአከባብያዊ ወጋ ወጎች ልማድና ባህል ነው፡፡ ሰይጣን ውስጣዊ ጾርን እየተጠጋ እንደሚፈትናችሁ ከላይ የተጠቀስናቸውንም ምክንያት እያደረገ እንዲሁም በህሊናችን የተለያዩ ነገሮችን በማሳሰብ ይፈትነናል፡፡ ለምሳሌ የጢሞቴዎስ ልጅ በርጠሚዎስ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ እያለ ሲጮህ በአከባቢው ያሉት ዝም በል እያሉ ሲያከላክሉት ነበር እንዲሁሙ የኤልያስ ደቀ መዝሙር ኤልሳም ጸጋ እንዳያገኝና በመምህሩ እንዳይባረክ ትቶት እንዲሄድ የነቢያት ልጆች ሲፈትኑት ነበር ማር 10፡46-52 2ኛ ነገ 2፡9 አባ መቃርዮስን አጋንንት ‹‹ መቃርዮስ ሆይ አመለጥከን  መቃርዮስ ሆይ ከእጃችን ›› በማለት መሸነፉቸውን አምነው መስክረዋል፡፡(ገድለ ቅዱስ መቃርስ)
3.            እግዚአብሔርን በራሳቸው( በፍጹም ሰውነታቸው) ያገለገሉ ናቸው፡፡ አምላካችን ምን አለ <<እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› ማቴ 16፡2 በማለት የፍጹምነት መንገድ ተናግሯል፡፡
ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር በህግ ተወስኖ ቤተሰብ መስርቶ ጌታውን እያገለገለ ይኖራል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን በማገልገልና ይህን አለም በማሰብ ልቡ ይከፈልበታል ለዚህ ነው ሐዋርያው ‹‹ ያላገባ ጌታውን እንዴት ደስ እንደሚያሰኝ የአለምን ነገር ያስባል ልቡም ተከፍሏል›› ብሎ በሚገባ ገልፆታል፡፡ 1ቆ 32፡33 በዚህም ነው ወደ ግባዣ የተጠሩት ሰዎች ከግብዣውም ያስቀራቸው ይህ ጉዳይ ነበር ሉቃ 14፡20 መድኃኒዓለም በሚያስተምርነት ጊዜ የዘለዓለም ሕይወት እንዳገኝ ምን ላድርግ ብሎ በጠየቀው ጊዜ ትእዛዛት ጠብቅ ብሎ 10 ትእዛዛት ጠቀሰለት ይህም ሰው እነዚህን ሁሉ ጠብቂያለሁ ቢል ጌታችን ሌላ አይጠበቅብህም አላለውም አንድ ነገር ጎደለህ ፍፁም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ መዝገብም በስማይ ታገኛለህ መጥተህም ተከተለኝ አለው እነጂ  ማቴ 19፡16-22 ማር 10፡17-22 ሰውን ፍፁም የሚያደርገው ትእዛዛትን መጠበቅ ሳይሆን ሁሉን ትቶ ዓለምን በመናቅ እግዚአብሔርን በፍፁም ሰውነትን ራስን በመስጠት ማገልገል ነው፡፡ስለዚህ ቅዱሳንም ዓለምን በመናቅ በምናኔ የኖሩ ናቸው፡፡
4) ሩጫቸውን በድል የተወጡ ናቸው
መንፈሳዊ ተጋድሎ በሩጫ ይመሰላል “ ይህንንም ሐዋርያው በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጠ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ” በማለት መንፈሳዊውን ሰው በሩጫ መስሎ ተናግሯል 1 ቆሮ 9-24-25 የሚሆን እድሜ ሲሆን በሚወዳደረው ከአጋንንት ጋር ነው ዳኛው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ አጋንንትን የቀደመ ክርስትያን አክሊልን (መንግስተ ሠማያትን) ያገኛል ያዕ 1¸2 “በፈተና የሚፀና የተባረከ ነው፡፡ የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና “ ያለው ያዕቆብ በመልዕክቱ መንፈሳዊው ሕይወት በሩጫ ቢመሰልም ከባድ ጉዞ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ምክንያቱም ሩጫው እንደሚካኤደው በርቀት የተገደበ አይደለም ተወዳዳሪዎችም የሚታዩ  አይደሉም ረቂቃን ናቸው አይደክሙም አይበሉም አይጠጡም ዕብ 12¸2 ሐዋርያው “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለም ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ አለም ገዢዎች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካሉ ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር ነው እንጂ” አገልጋዮቻችንን ገልፃችዋል፡፡ ኤፌ6¸12 ዋጋውንም ሲያነጻጽር “ እነዚህ የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው እኛ ግን የማይጠፋውን” በማለት ገልፆአል፡፡ 1ቆ 9¸24-26፡፡
ይህንን ተጋድሎ በትእግስት ያጠናቀቃትም “ሩጫዬን ጨርሻለሁ ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ የሕይወት አክሊል ተዘጋጅቶልኛል” በማለት እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ይናገራሉ በማከልም “ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም” በማለት ተናግሯል 2ጢሞ4¸6-8 ብዙ ሯጮች ሩጫውን አብረ እንደሚጀምሩ ሁሉ ከሐዋርያት ጋር ጀምረው ሩጫውን ያቋረጡም አሉ ለምሳሌ ይሁዳ እንዲሁም ከነሉቃስና ጢሞቴዎስ ጋር ጀመረ ዴማስም ሳያጠናቅቁ አቋርጠዋል ስለዚህ ለገንዘብ ለዓለም ለምድራዊ ነገር ሳይታለሉ የፈጸሙ የሕይወት አክሊልን ያገኛሉ፡፡
5) በፍፁም መንፈሳዊ ጥበብ የኖሩ ናቸው
አምላክችን ቸሩ ጌታችን “እንደ እባብ ልባሞች እንደ እርግብ የዋሆች ላይ አድሮ በመንፈሳዊ ጥበብ መኖር እንዲገባ አስታምሯል ማቴ 10¸6 ምክንያቱም ጠላታችን ረቂቅና አመጣጡም ለማወቅ ጥበብ መንፈሳዊ ያስፈልጋል “ ሠይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እስኪመስክ ድረስ ራሱን ይለውጣልና” 2 ቆሮ 11¸ 14 ላይ እንደተፃፈ “ እኔ ሚካኤል ነኝ እኔ ገብርኤል ነኝ” በማለትም በምትሆኑ ይመጣል 2 ቆ 11¸ 3 እባብ ሄዋንን እንዳሳሳተችው እንዳትለወጥ እፈራለሁ” በማለት ደግሞ ያስገነዝባል ሰይጣን በምትሀቱና በሀሰት ምህረቱ ብዙዎችን ስህተት ውስጥ ጥሏል፡፡ የሀሰት አባት ነውና ዮሐ 8¸ 44፡፡
አንዳንድ ጊዜ በጽድቅ ውስጥ የተደበቀ ኃጢያትም ሰይጣ ሊያሠራ ይችላል፡፡ በሠሩት ስራ መመካት ሌሎችን መናቅ ውዳሴ ከንቱ  ትእቢት እና ሌሎችም እንክርዳዶች ሊበቅሉ ይችላሉ ፡፡ እዝነዚህ ደግሞ ሙሉ ደመወዝ እንዳይቀበል እንቅፋት የሚሆኑ ናቸው፡፡ 2 ዮሐ 8 እንደተፃፈ  “ ከተሠመረ  ኃጢያት አንጻኝ” መዝ 18¸ 2 ጠቢቡ ሰለሞንም በድብቅ ስፍራ ኃጢያት እንዳለ አየሁ” በማለት የተናገሩት ስለዚህ ይህንን ረቂቅ ፈተና በድል ለመወጣት በፍፁም መንፈሳዊ ጥበብ መኖር ይገባል ቅዱሳንም በመንፈሳዊ ጥበብ የኖሩ ናቸው፡፡
በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ትቀመጣላችሁ” ማቴ 19 ¸ 28 በዙፋን ሚቀመጥ ንጉስ ነው “ የእግዚእሔርና የክርስቶስ ካህናት የሆናችሁ ከእርሱም ጋር ሺህ ዓመት (ለዘለዓለም) ይነግሉ” ለእ 2¸ 6፡፡
ሠ) “እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና” መዝ 74¸7 መዝ 93¸ 2 “ ከሙታን ከተነሳ በኃላ … በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተመሠገነ እርሱ እንደሆነ እንመክር ዘንድ አዘዘን” የሐዋ 10  42  ማቴ 16 ¸ 27 ሮሜ 2¸16  ሰብ 10¸ 30 “ ሁላችንም በክርስቶስ ወንበር ፊት እንቆማለንና” ሮማ 14¸ 10 ¸ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ እስራኤል ነገድር እስራኤል ዘሥጋ እስራኤል ዘነፍስ) ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ” ማቴ 19 ¸ 28 ¸ ቅዱሳን በዓለም ላ እንዲፈርዱ አታወቁምን?” 1 ቆሮ 6¸2 “ ይህን እንደዚህ በሠለው ነይ አሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፈርጄበታለሁ፡፡ “ 1ቆ 5¸1-4 የሐዋ 5 ¸ 1-10 ሐዋ 13 ¸ 9-10 ሐዋ 5¸ 1-10 “ቅዱስ ጴጥሮስ በሀናና በከጲላ ፈርዶባቸዋል” 2ህ-132 ነገ 6¸18-19፡፡
ረ) “አማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ” መዝ 49¸ 1 “እርሱ እውነተኛ (የባሕሪያ) አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው” ዮሐ5¸20 ቅዱሳን የደጋ አምላክ ሲሆኑ እግዚአብሔር ደግሞ የባይርያ አምላክ ነው፡፡ የሐ 20 ¸28 “ እግዚአብሔርም ሙሴን አይ እኔ በፈርኦን ላይ አምላክ አድርጌዋለሁ” ዘይ 7¸1 “እኔ ግን አምላክት ናቸሁ” መዝ 81¸6 “ቅዱሳን የደጋ አማልክት መባላቸው ሊሻር አይችልም” ዮሐ 10¸34፡፡
ሰ) “በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን” ዘፍ 18 ¸ 14 “ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም “ ሉቃ 1¸37  እውነት እላችኋለው የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ወደዚህ  እለፍ ብትሉት ያልፋል የሚሳናችሁም ነገር የለም” ማቴ 17 ¸20 “በእኔ የሚንምን እኔ በማደርገውን ሥራ እርሱም ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል” የሐ 14¸12፡፡
ሸ) “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው … ባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ  ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ፡፡” ሉቃ 24 ¸ 34-46 “ ጌታ ሆይ ይህን ኃጢያት አትቁጠርባቸው… ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል፡፡ “የሐዋ 7¸8፡፡
ከዚህ በላይ ለመግለፅ እንደሞከር ነው በደጋ እግዚአብሔር የከበረ በኃይማኖት በምግባር የፀና ንጽህናና ገንዘብ ያደረገ የቅዱሳን ህይወት እንዴት ፈጣሪያቸውን እደ መሰለ ነው፡፡ በዚህ ብቻ ሳይሆን አንካሳ በማርታት አይነስውር በማብረታት ሙታንን በማንሳት መስለውታል፡፡ የሐ 3¸1-10, 9¸32-35¸40፡፡
1.4 የቅዱሳን ሰዎች አሠያየም
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የቅዱሳን አሰያየም በድምፅ ብልጫ አይደለም፡፡ ቅዱሳንን ቅዱስ የሚያሰኛው ሕይወታቸው ነው ከላይ በዝርዝር እንደተመለከትነው በሁሉ አብነታቸውን ክርስቶስን መምሰላቸው ነውና በውስጥም በአፍአም በቅድብና ወርቅ የታለበጠ(ያጌጡ) መሆናቸው እንደ ካህኑ ዘካርያስና እንደ ቅዱስት ኤልሳቤጥ “ሁለቱም በጌታ ትዕዛዝና ሕግጋት ሁሉ የላነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ፀድቃን ነበሩ፡፡” ተብሎ ይመሰከርላቸዋል፡፡ ሉቃ 1¸ 6 ከሁሉ በላይ ደግሞ የሚሠክርላቸው እግዚአብሔር ነው፡፡ “ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልስራህ አውቄሃለሁ፤ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ ለዘህዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ፡፡ “ 7. ኤር 1¸4-5 “ እውነት አላችሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱ መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም” ማቴ 11¸11 የሚለው የሚናመለክተው ይኸንን ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክትም “ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ ደስታና ተድላም ይንልሀል በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ  አይጠጣም፡፡ ገናም በእናቱ ማፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ተሞልቶበታል” በማለት መስክረዋል፡፡ ሱናማዊቷ ሴትም ስለ ነቢዩ ኤልሳ ለባሏ ስትመሰክር “ ይህ በእኛ ዘንድ ሁል ጊዜ የሚያልፈው ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው እንደሆነ አውቃለሁ” ያለችው ለዚህ ነው፡፡ 2 ነገ4 ¸9 ከኢያሪክ የመጡ የነቢያት ልጆችም “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳ ላይ አርፎአል” በማለት መስክረዋል መቼም ወዳጅ እያለ ጠላትም ስለማይጠፋ በጠላትናት የማገባ ነገር ቢናገሩባቸው መልሱን እግዚአብሔር ይሠጣል፡፡ ለምሳ ሐሰተኞች መምህራን የሶስናን ስም በሐሰት አጎድፈው በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ ሁሉም ሞት ፈርዱባት፡፡ እግዚአብሔር ግን በነቢዩ በዳኤል በኩል መልሶ ሰጥቶ ንጽህናዋን መስክሮላታል፡፡ ውድ ሶስና 2”44 ሌላው ቀርቶ አሮንና እህቱ ማርያም እንኳ በእግዚአብሔር ባለሟል በሙሴ ላይ የሚገባ ነገር በመናገራቸው እግዚአብሔር ሁሉንም ወደ መገናኛው ድንኳን ጠርቶ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ በላይም እገለጥለታለሁ ወይም በህልም አነጋግረዋለሁ፡፡ ባሪያዬ ሙሐ ግን እንዲህ አይደለም እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው፡፡ እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ በምላሴ አይደለም  የእትዚአብሔርንም መልክ ያያል በባሪያዬ በሙሴ  ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አላፈራችሁም፡፡” በማለት ተቆጥቶባቸዋል፡፡ ዘኀ 12¸1-8 በዚህም ምክንያት በሙሴ አማላጅነት እስክትፈወስ ድረስ የሙሴ እህት በልምድ ነድዳለች፡፡
በመሆኑም ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዚህ ላይ ተመስርታ ቅዱሳንን ትሰይማለች፡፡ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፡፡
1.             እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን / ራዕ2 ¸ 10/ እንደተባለ እስከ ሕይወታቸው ፍፃሜ ድረስ በመጽናት ሠማዕት የሆኑትን እስከ እረፍት ዘመናቸው ድረስ በጾም በጸሎት ተወስነው በገድል እየተቀጠቀጡ በአምላኮተ እግዚአብሔር የፀኑትን ነው፡፡
2.             በጌታች በአምላካችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ላይ የተመሰረተችውን ቤተክርስቲያንን እምነትና ሥርዓት ጠብቀው በማስጠበቅ በአገልግሎት የፀኑትንና የታደጉላትን፡፡
3.            የእግዚአብሔርን ቃል ንባብ ትርጓሜና ምስጢር ሳፋልሱ በማስተማር በሃይማኖት ያደጉትን ምዕመናንን ያበዙትን፡፡
4.            በሕይወታቸው ነውር በሀይማኖታቸው ነቀፋ ያልተገኙባቸውን፡፡
5.            ከዓለም ተለይተው በበረሃ ወድቀው ድንጋይ ተንተርሰው ጤዛ ልሰው ዋሻ ዘግተው ጸብአ አጋንንትን ድምፅ አራዊትን እና ግርማ ሌሊትን ሳይሰቀቁ የኖሩትን
6.           ምትሀት የይደላ እውነተኛ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁትን
7.            በአጠቃላይ ከፍፁምነት መዓረግ የደረሱትን እግዘብሔር እንዳከበራቸው ተከብርላቸዋለች፣ ቅዱሳን ብላ በቅድስና ስም ትጠለቸዋለች፡፡ ከእነርሱ በፊት የቅዱስና ማእረግ በተሰጣፈው ሰዎች መዝገብ ስማቸውን በክብር ትጽፋለች፡፡ ሕዝቡም እንዲያውቀው ታደርጋለች፡፡ በጽማቸው ያለበት ቦታ የሚያውቅ እንደሆነ ሰብስባ በክብር ታስቀምጣለች፡፡ ተአምራቸውን ወይም ገድላቸውን ትጽፍላቸዋልች፡፡ ለጸሎት ለልመናና ለምሥጋና የሚሆን መልክእ ትደርስላቸዋለች፡፡ የሚታሰቡበት እለት ትሰጣቸዋለች  የመታሰቢያ ስዕል ትስልባቸዋለች፡፡ ጽላት ትቀርድላቸዋለች ሕንፃ ቤተክርስቲያን ታንጽላቸዋለች፡፡ ስማቸውንም እየረለች ትማፀንባቸዋለች፡፡ ምዕመናንም በስመ ክርስትና ኃይለ ጊዮርጊስ ወለተ ጊዮርጊስ ገብረ ተክለሃይማኖት ወለተ ተክለሃይማኖት… እየተባሉ እንዲጠሩ ታደርጋለች፡፡
1.5 በቤተክርስቲያን ቅዱሳን ተብለው የሚጠሩት እነማን ናቸው
1.             እቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
2.            ቅዱሳን መላእክት
3.            ቅዱሳን ሰዎች
4.            ቅዱሳት መካናት
5.            ቅዱሳት እለታት
6.           ቅዱሳት ንዋያት
7.            ቅዱሳት መፃሕፍት
8.            ቅዱሳት ሥዕላት
1. እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም መልዕልተ ፍጡራን በትሕተ ፈጣሪ (ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች) ትባላለች ምክንያቱም ወለዲተ አምላክ ሰለሆች ለዚህ ነው ሃይማኖቸው የቀናች 318 ሊቃውን በኒቂያ ጉባኤ ባደረጉ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ግብር የተፈጸመውን የአምላክ ልደት ለመተርጎም ሲሉ የቅድስት ማርያምን ክብር ማዕረግ ገልጠው ተናግረዋል እንዲሁም በጉባኤ ኤፌስን የተለየ ሐሳብ ይዞ የተነሳውን ንስጥሮን ባወገዙበት ወቅት እመቤታችን ድንግል ማርያም እመአምላክ መሆኗን ገልጠዋል ለዚህ ትምህርት ውጪ አዲስ ሀሳብ የሚያመጣውንም እነ ቅዱስ ቄርሎስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው አውግዘዋል እኛም ስለ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የምተስተምረውን ትምህረት እንደሚከተለው እንገልጣለን፡፡
ሀ) የቅድስት ማርያም ሕይወት
ቅድስት ማርያም ከቅዱሳን ወላጆቿ ከኢያቄምና ከሐና በሊባኖስ ተራራ ተወለደች፡፡ መኃ4 ¸ 8 መዝ 68 ¸ 1 የስእለትም ልጅ ስለነበረች በቤታቸው ሳይሆን በቤተመቅደስ እንድታድግ ተደረገች ዘወትርም መላእክት ምግቧን የመጡ ነበር መዝ 44 ¸ 10 በሦስት ዓመቷም ቤተመቅደስ ከገባች በኃላ እስከ አስራ አምስት አመት ድረስ ቆየች እግዚአብሔርም ለልጁ እናት እንድትሆን ስለመረጣት መልአኩን ወደ እርሷ ላከ የዚህም ብርሃናዊ መልአክ ስሙ ገብርኤል ነበር ሉቃ 1¸19-27 እመቤታችን ማርያም በሐልዩ በነቢብ በገቢር በሦስት ወገን ድንግል ንፅህይት በመሆኗ አምላክን እንዲያድርባት አደረገችው በድንግልና ጸንሳም በድንግልና ወለደችው ማቴ 2 ¸ 1 ሉቃ 2 ¸1 አምላክም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ከሷ ከተወለደ በኃላ በንጉስ ሄሮስ ቅናት ምክንያት ወደ ግብፅ ልጇን ታቅፋ  ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ተሰዳለች  ኢሳ 19 ¸1 ከስደቷም መልስ ጌታችን እስከሚሰቀል ድረስ ለ33 ዓመት ከጌታችን ጋር ኖራለች ጌታችን በተሰቀለ ጊዜም ለዮሐንስ አደራ ሰጥቷታል ዮሐን 19 ¸ 26 ከዚህም ከዮሐንስ ጋር 15 ዓመት ኖራለች እመቤታችን በጥቅሉ 64 ዓመት በዚህ ዓለም ከኖረች በኃላ እንደ ሰው ሁሉ አርፋለች ሐዋርያትም በነሐሴ 14 ቀን ተቀብራለች በ3ተኛው ቀን እንደ ልጃ ነሐሴ 16 ሞትን ድል አድረጋ በልጃ ስልጣን ተነሳች አረገች ህያው ሆናም በልጃ ቀኝ በክብር ቆመች መዝ 44¸9፡፡
ለ) የድንግል ማርያም የቅድስና ጠባያት
1)    የንጽህናና የትህትና ህይወት
እመቤታችን ድንግል ማርያም ንጽህት ቅድስት ናት እመቤታችን ከጥንት እስከ ከውርስ ኃጢያት  ንጽህይት ነች ይህንንም ነቢዩ እይያስ “ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን ገሞራንም በመሠልን ነበር” እንዳለ ት.ኢሳ 1¸ 9 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረ የእመቤታችን የማርያም ንፅህና ከመላእክትም ይበልጣል ብሏል በዚህም ምክንያት አምላክ ከእርሷ እንዲወለድ መረጣት ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሳ ነፍስም ነስቶ ሰው ሆነ የፀሀይ መገኛም ስለሆነች መስራቅ ተባለች፡፡
ትህትና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ  በድንግሊቱ ሕይወት ውስጥ ተገልጧል መልአኩ ወደ እርሷ በመጣ ባበሠራት ጊዜ “ እነሆን የጌታ ባሪያ …” ነበር ያለችው ሉቀ 1 ¸ 38 በእርግጥም እርሷ ይህንን ያለችው እናቱም አገልጋዩም ስለሆነች ነው፡፡ አምላክንም ከጸነሰች በኃላ ወደ ኤልሳቤጥ ዘንድ ሄደች መንፈስ ቅዱስም ለኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ክብር በገለፀላት ጊዜ በትህትና “ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆነኛል?” ብላለች ሉቃ 1¸ 43 እመቤታችን ወደ ኤልሳቤጥ የኄደችው አምላክ ከጸነስች በኃላ ነው በጣም አድካሚ ወደ ሆነው ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ የመጣቸው ፡፡ ከዚህ በኃላ ኤልሳቤጥም እስክተወልድ ድረስ ለሦስት ወራት ያህል በዚህ ተቀምጣለች፡፡ ሉቃ 1 ¸ 39-56፡፡
ለእርሷ የተሰጣት ድንቅ የሆነ ክብር ትህትናዋ ፈጽሞ አልቀነሰውም በፀሎቷም ጊዜ “ የባሪያውን ትህትና ተመልክቶአልና… ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራትን አምላክን መድረሻዋን በክብር የተሞላ የሥጋዌን ምስጢር ለማንም አለመናገሯ ደግሞ ሌላው ድንቅ የትህትናዋ መገለጫ ነው፡፡
እመቤታችን ቅድስት ማርያም በቤተ መቅደስ የኖረች በቅስስናና በንፅህና ነው፡፡ አይሁድ ግን ከቤተ መቅደስ እንድትወጣ በጠየቁ ጊዜ አልተቃወመችም እንደዚህም በአንድ ሰው ጠባቂነት ስር እንድትኖር በተደረገ ጊዜም አንዳችም የተቋውሞ አሳብ አላቀረበችም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አሰራር በድንግልና እናት እንድትሆን እግዚአብሔር ሲፈቅድ ሉቃ 1 ¸ 35 ሰፊ የውይይት አጀንዳ እንዲከፈት አልፈቀደችም ይልቁንም ባልተቀየረ ቃሏ እንዲህ አለች እንጂ “ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ…” ሉቃ 1 ¸ 38 ይህን በማለቷ በመታዘዟም የእግዚአብሔር እናት ሆነች፡፡
እሜታችን ቅድስት ማርያም ወደ ግብጽ እንድትሰደድ በመልአኩ በኩል በታዘዘች ጊዜ በዝምታ ነበር የወረደችው፡፡ ከግብጽ ወደ ቅድስት ሀገር እንድትመለስ ይኸው ትእዛዝ ሲደርሳት በዝምታ ነበር የፈፀመችው፡፡ ከቤተልሄም ወጥታ ወደ ናዝሬት በመሄድ በዚያ እንድትኖር በታዘዘች ጊዜም ጋር የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን ብላ የታዘዘችው፡፡ እናታችን ያለ ምንም ውይይት በመታዘዝ ሕወት ውስጥ ያለፈች የሰው ዘር ናት፡፡
3)  የትዕግስት የጽናት ሕይወት
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆቿ በሞት የተለዩአት ገና የስምንት አመት ብላቴና ሳለች ስለሆነ ያደገችው ያለ ወላጅ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም ያለ ወላጅ የማደግን ችግር በጽናት ተቋቁማለች በቤተ መቅደስ መኖርንም የጀመረችው ገና በሕፃንነት እድሜዋ በመሆኑ ብቸኝነትንም ተጋፍጣለች፡፡ በአንድ ጠባቂ ሰው ጥላ ስር ለመኖር ከቤተ መቅደስ ከወጣች በኃላም የድህነትን ህይወት ተቋቁማለች፡፡ “ በዚህም  የመውለጃዋ ወራት ደረሰ የበኩር ልጅዋንም ወለደች በመጠቅለያም ጠቀለለችው በእንግዶችም ማረፊያ ስፍራ ስላልነበረቸው በግርም አስተኛችው” ሉቃ 2 ¸ 7 ተብሎ እንደተጻፈ አንድን ልጅን ክርስቶስንም ከወለደች በኃላ መከራን በጽናት ተቀብላለች በጠባቂዋ በዮሴፍ ቤት በነበረች ጊዜም የኃላፊነትን ቀንበር ተሸክማለች፡፡
ድንግል ማርያም ገና በ15 አመቷ ብላቴና ሳለች የግብጽን የደርሶ መልስ አድካሚ ጉዞ በጽናት ተወጥታለች፡፡ በዚያ ከልጇ ጋር ለሦስት አመት ከስድስት ወር በስስት ስትቀመጥ የግብፅ ጠኦታት በልጀዋ ፊት እየተሰበሩ ይወድቁ ስለነበር በትንቢተ ኢሳያስ እንደተፃፈ ጣኦት አምላኪዎች ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ ያሳድዷቸው ስለነበር ይህንንም በትዕግስት በጽናት ተቋቁማለች፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ በልጇ ላይ የወረደውን ስድብ እንግልት ግርፋትና ህማማት መስቀል እየተመለከተች ከመሪር እንባ ጋር በጽናት ቆይታለች፡፡
ድንግሊቱ እነዚሁ ሁሉ መከራዎች ቢገጥማትም በልጇ የሚሆን ደስታዋን ስላላጣቸውወ በምሥጋና ፀሎቷ ውስጥ እንዲህ ብላለች “… መንፈሴም በአምላኬ በመድኋኒቴ ሐሴት ታደርጋለች” ብላለች ሉቃ 1 ¸ 47፡፡
4) የእምነትና የመቀበል ሕይወት
እርሷ ስለተቀበለቻቸው መከራዎች አንድ ጊዜ እንኳን ይህ ለምን ሆነ አላለችም፡፡ ሄሮድስ ልጃን ለመግደል አውሬ ሆኖ በተነሳበት ጊዜና ወደ ግብጽ ስትሰደድ እንሁ አይሁድ ግን ሁሉ መከራ ሥቃይ ሲያደርሱባት በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ይነግሳል ለመንግስቱም ፍፃሜ የለውም ብሎ መልአኩ የነገረኝ ቃል ወዴት ደረሰ? ብላ አልተናገረችም ሉቃ 1 ¸32-33፡፡
እናታችን ቅዱስት ማርያም ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግልና እንደምትወልደው አምናለች ይህም ተከናውኖላታል፡፡ ምንም እንኳን ልጃ ኢየሱስ ክርስቶስ በበረት ቢወለድም ስለ እርሱ “… ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዘብሔር ልጅ ይባላል” ሉቃ 1¸ 35 ተብሎ በተነገራት የምስራች ቃል አምናለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ልጇ ሕማማተ መስቀል እንደሚገጥመውና በመስቀል ተሰቅሎ እንደሚሞትና ሞትን ድል አድርጎ እንደሚነሳ ስላመነች ይህንን በአይኗ ተመልክታለች፡፡ ማቴ 28
5) ዝምታ ፀሎትና ተመስጦ
እናታችን በእግዚአብሔር ፈቃድ ቤተመቅደስ ውስጥ ስላደገች የብቸኝነትን የዝምታን በፀሎትና ተመስጦ ራሷን ጽሙድ በማድረግ በዚህ ተምራለች፡፡ እርሷ በልጅነቷ የወላጆቿን ፍቅርና እንክብካቤ ብታጣም ፍቅሯን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር በማድረግ አድጋለች በዚህም በብቸኝነት ለሚኖሩ ለባህታውያን ትልቅ ምሳሌ ነች፡፡

እርሷ ድንቅ ልጇን በወለደች ጊዜ ገና ብላቴና ነች ከእድሜዋ ጋር ሲነፃፀር ከህሊና በላይ የሆነ ድንቅ ተአምራት ተከባ ነበር እርሷ የመላእክትን የእረኞች የስብሰባ ስገልን (ከሩቅ ምስራቅ ሐገር የመጡ የጥበበኞች ሰዎችን ድንቅ ቃላት ምሥጋና ሰምታለች ቢሆንም ግን አንድም ጊዜ በኩራት አልተናገረችም በወንጌል የተፀፈው “… ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር”፡፡ ሉቃ 2¸19 እና 52
ይህ  ይሁን እንጂ እናታችን መናገር በሚገባት ጊዜ ስትናገር የተናገረቻቸው ንግግሮች ለትውፊታዊ ስብከቶ ምንጮች ነበሩ፡፡ ሐዋርያትንና ወንጌላውያን ባቀረቧቸው ዜናዎቻቸው ላይ ከእርሷ ብዙ እንደተማሩ ገልጠዋል በተለይ ፍቅሩ እግዚ ዮሐንስ ከፃፈው ወንጌልም  እንደምንረዳው ከእርሷ ስለ ምስጢረ ስላሴ ጥልቅ ነገር እንደተማረ ያስታውቃል፡፡
ድንግል ማርያም ብቸኝነትን ፀጥታን ከይሎት ከዜማ ከመዝሙራት መፃሕፍትን ከማንበብ ያነበባቸውን ጥቅሶች በተለይም መዝሙረ ዳዊትን በተመስጦ ውስጥ ሆና በቃሏ በመውጣት ሙሉ ጊዜዋን በዚህ ታሳልፍ ነበር፡፡ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘንድ ያለው ዝምታ ለእኛ ትምህርት ሰጪ ነው እናም እባካችሁ እርስዋን ጥቂት በመናገርና ብዙ በመጸለይ በተመስጦ ውስጥ በመቆየት እንምሰላት፡፡
6) ሌሎች የቅድስና ጠባዮቿ
እግዚአብሔር ወላጆቿን በሕጻንነቷ እድሜ ያጣችውን ድሀ ድንግል እናት አደርጎ የመረጠው በሕልውናዋ (በአኗኗርዋ) ከሴቶች ሁሉ የምትልቅ እናት ሊያደርጋት ስለ ወደደ ነው እርሷ በጠባዮቿ ከገንዘብ ብልጽግና የሚልቁ ልዩ ጠባያት አሏት፡፡
ቅድስና ንፅሕና ድንግልና መንፈሳዊ ዕውቀት ሌሎችን ማገልገልና ለሐዋርያት አባቶች ያሳየቻቸው መንፈሳዊ እናትነት ከዋና ዋና ጠባዮቿ መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ሐ. ድንግል ማርያም በቤተክርስቲያን እምነት ውስጥ
ኦርቶኮክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የቅድስት ድንግል ማርያም የሚገባትን ክብር ማዕረጓን አትቀንስም፡፡
1.                እንደ ኦርቶኮክሳዊት ቤተክርስቲያን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናት ናት፡፡ ንስጥሮሳውያን ድንግል ማርያም “የሰው ናት እንጂ የአምላክ እናት አይደልችም” ብለው በካዱ ጊዜ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ በኤፌስን ጉባኤ  ላይ ከተቃወማቸው በኃላ በወግዘት ተለይተዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ እንደሆነች ብዙ ቦታ ላይ ተጽፏል ለአብነት ያክል “ ሕፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫታው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” ት.ኢሳ9 ¸6-7  ይህ ትንቢታዊ ቃል ሲሆን በፍፃሜው በሀዲስ ኪዳን ደግሞ “ በመጀመሪያ ቃል ነበር ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃም እግዘብሔር ነበረ፡፡… ቃልም ሥጋ ሆነ “ ዮሐንስ 1 ¸1 እና 14 ይላል፡፡ በተጨማሪ እነዚህን ጥቅሶች መመልከት ይቻላል፡፡  ት.ኢሳ7¸ 14 ማቲ 1 ¸ 22፣ 7 ማክ 5 ¸ 2 ማቲ 2 ¸5 ዮሐን 1¸34 ማቲ 3¸17 ማቲ 17¸5
2.               ቤተክርስቲያንን በእመቤታችን ቅድስናና ንጽህና ታምናለች በዚህም በእግዚአብሔር ህሊና ስትታሰብ ስለቆየች ኢየሱስ ክርስቶስን ጸንሳ ወልዳለች፡፡ “ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን ገሞራንም በመስልን ነበር” ት.ኢሳ 1¸9 ይህ ማለት እመቤታችን ጥንተአብሶ የውርስ ኃጢያት የሌለባት በአዳም ባህሪ ውስጥ እንደ እንቁ የምታበራ መሆኗን የሚያመለክት ነው፡፡ መልአኩ ይህን አስመልክቶ”… መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጸልልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” ብሏል ሉቃ 1 ¸47 እመቤታችን ንፅህይት ባትሆን ኖሮ በባህሪው ንፁህ ለሆነው ለእግዚአብሔር እናት ነች አትመረጥም ነበር ምክንያቱም ፍፁም እግዚአብሔር ኃጢአት በባህሪው አይስማማውምና፡፡
3.               ቤተ ክርስቲያን በድንግል ማርያም አማላጅነት ታምናለች እርሷ የንጉስ እናት ስለሆነች ከንጉሱ ቀኝ የምትቆም ንግስት ነች ስለዚህም አማላጅነቷ ሚቀርበው ከሊቃነመላእክት ሁሉ በፊት ነው፡፡ መዝ 44¸9
4.              ቤተ ክርስቲያን እመቤታችን ምልእተ ጸጋ (በጸጋ የተሞላች) እንደሆነች ታምናለች ሰዎች ሁሉ ሊባረኩ ደግ ሊሰጣቸው ይችላል የእመቤታችን ጸጋ ግን የተለየ ነው በእግዚአብሔርም ፀጋ የተሞላች ነች የፀጋ ተከፍሎ የለባትም፡፡ ሉቃ  1¸
5.              ቤተክርስቲያን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና ታምናለች፡፡ እመቤታችን ከመጸነሳከመውለዷ በፊት ድንግ በጸነሰች በወለደች ጊዜ ድንግል ከጸነሰች ከወለደች በኃላ ለዘለዓለሙ ድንግል ነች፡፡ 2 አሳ 7¸ 14 ማቲ 1 ¸20-24 7 ህዝ 44¸1 ሉቃ 1¸ 34
ተረፈ ንስጥሮሳውያን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከክርስቶስ ሌላ ልጆች ወልዳለች ይላሉ ይህ ግን ፍፁም ስህተትና የመጻሕፍትን ምስጢር አለመረዳት ነው፡፡
መጽሐፍ ለዮሴፍ ታጨች ቢል ዘመድ ስለሆነ እንዲጠብቃት ነው ለዚህ መልአኩ በህልሙ ለዮሴፍ ከሷ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነው ያለው ማቲ 1¸28 እና 20 የጌታ ወንድሞች ስለሚባሉት ደግሞ ያዕቆብ ዮሳ ስምኦንና ይሁዳ የተባሉት ሰዎች የዮሴፍ ልጆች ናቸው፡፡ ከሞተችው ሚስቱ የወለዳቸው የጌታ ወንደሞች የተባሉትም ከጌታችን ጋር አብረው ስለደጉ ነው ምክንያቱም አብሮ አደግ የሆኑ ሰዎች ወንድሞች ብሎ መጥራት የተለመደ ስለሆነ ነው የሚገርመው ነገር መናፍቃን በሚያነሱት ጥቅስ መልሰው እራሳቸው መታነቃቸው ነው ቃል እንዲህ ነው የሚለው  ይህ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ  አይደል ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዩሳ ስምኦንም ይሁ አይደሉ እህቶቹ በእኛ ዘንድ አይደሉምን ይህንንስ ጥበብ ከየት አመጣው ብላው ተሰነካከሉበት ይላል ማቲ 13  54-57 አይሁድ ጌታችንን የዮሴፍ ልጅ የነስምዖን ወንድም በማለት አምላክነቱን በመካዳቸው ተሰነካከሉት ነው የሚለው ፕሮቴስታንቶችም የአይሁድን አላፋ ይዘው መነሳታቸው በጣም የሚገርም ነው ልብ ይስጣቸው ነው የምንለው ስለዚህ ቤተክርስቲያን ምን የእመቤታችንን ድንግልና የሚክዱትን ዘለዓለማዊ ንስጥሮስንና ተከታዮቹን ፕሮቴስታንትን ከነ ጀሌዎቻቸው ታወግዛለች፡፡
6. ቤተ ክርስያን እመቤታችን ከሞት መነቷንና ወደ ሰማይ ማረጓን ታምናለች ይኸንንም ክቡር ዳዊት በትንቢቱ “ አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም” በማለት ተናግሯል መዝ 131 ¸ 8 ታቦት የተባለች እመቤታችን ነች የእግዚአብሔር ማደሪያ ነችና ጠቢቡ ሰለሞንም “ ወዳጄ ሆይ ተነሽ ብሏል” መኃ2 ¸10
ማጠቃለያ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር እንዲገባት አስቀድሞ አምላክ አከበራት ከሌሎች ሴቶች ለይቶ መረጣት መዝ 131 ¸13-14 አምላክን ትውልድ ዘንድ አንዳላትም ነቢያት ትንቢት ተናገሩላት ት ኢሳ 7¸14 7 ኢዮ 5¸2 መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል   ሊያበስራት በተላከ ጊዜ “ምልዕተ ፀጋ ቡርክት አንቲ አም አንስት” እያለ አመሰግኗታል ክብሯንም ገልጧል ሉቃ 1¸28-29 ቅድስት ኤልሳቤጥም “ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ መለላባት በታላቅ ድምጽም ጩኸት እንዲህም አለች አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ የማኀፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንደምን ይሆንልኛል …” ስትል ገልጣ ተናግራለች ሉቃ 1¸41-43 ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ እናቱን ሳይረሳ ከመከራው ይልቅ የእሷ የእናቱ ነገር ግድ ብሎት ዮሐንስን እንዲንከባከባት አደራ ሲል ክብሯን ገልጦል ዮሐ 19 ¸26-27 አንዲት ሴት አስምታ ጮክ ብላ የተሸከመች ማህፀን ያጠባኻቸው ጦቶች ብጹአን (የተመሰገኑ) ናቸው” ስትል ትናግራለች ሉቃ 11¸26 ይህም  መልከ ማርያም ነው የእመቤታችን ሁለንተናዊ የተቀደሰ ነውና ራሷ እመቤታችንም እነኆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል ብላለች ሉቃ 1¸ 48 እንዲሁም በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ ስምሽን ለልጅ ልጅ ያዘክራሉ እንዲል ቅድስት ቤተክርስቲያንን እመቤታችንን ከአምላክ በታች ከፍጡራንም በላይ የሆነ ክብር ሰጥታ ታከብራታለች እንዲሁም ወላዲተ አምላክ ብላ ትጠራታለች በስሜ ቤተክርስቲያንን ታንፀለች ጽላት ትቀርጻለች በስሟ አንድ ቅዳሴ ትቀድሳለች በስሟ የአዋጅ ጾም ደንግጋ በየአመቱ ትፆማለች በጥመ ዜማዎች በማኃሌቶች ለእግዚአብሔር እናት በሚቀርቡ ምሥጋናዎች ውዳሴዎች በአጽዋማት ቀናቶቿና በበዓላቶቿ እንዲሁም ዘወትር በሚቀርቡ ምሥጋናዎቿ በፀሎት መጻሕፍቶቹ ውስጥ ተካተው ይገኛሉ፡፡ የመላእክትን የነቢያትን የሐዋርያትን የሰማዕታትን የሌሎችንም የቅዱሳንን ስም ከመጥራታችንና ከጠራን በኃላ የእመቤታችንን ስም እንጠራለን እንደ ቤተክርስቲያን ትምህርት እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ቤዛዊት አለም ዘላለማዊት ድንግል ወላዲ አምላክ እመብርሃን እየተባለች እንድትጠራ እንድትመሰገን ታስተምራለች በእውነት በረከቷ ይደርብን አሜን፡፡
v ለቅዱሳን መላዕክት
ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለተልእኮ የሚፈጠሩ  ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትን እና አርነትን ለሰው ልጆች ያሰጣሉ፡፡ “ዳንኤል ሆይ ጥበብንና ማስታዋልን አስጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ” የሚለው የቅዱስ ገብርኤል ቃል የሚረጋግጥልን ይህንኑ ነው፡፡ የሰዎችን ጸሎት ልመና መብት ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡ ፀሎትህን መስዋትህ በእግዚአብሔር ፊት አረገ” የሚለው ቃል ምስጢር ነው የሀይ¸ 4 ትልቁ አገልግሎታቸው እግዚአብሔርን ማመስገን ነው፡፡  “ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጌታ እግዚአብሔር” እያ በአንድነትና በሦስትነት ፀንቶ ሚኖር እግዘብሔርን ያመሰግኑታል፡፡ 2 አሣ 7
v ቅዱሳን መላዕክት
ተፈጥሮአቸው ሕይወታቸውም በቅድስና የተመላ በመሆኑ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡ ቅዱስ የሆነውን የእግዘብሔርን ስም ስለሚያመሰግኑ ቅዱሳን ይባላሉ እንዲሁም ከእርኩስት የተለዩ በመሆናቸው ቅዱሳን ይባላል፡፡ መላእክት ተፈጥሮአቸው በሐልዮ( በሐሳብ) ከምንም ነገር በአምላክ ኪነጥበብ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ቁጥራቸውም አይታወቅም ማለትም ከፈጠራቸው አምላክ በስተቀር ቁጣራቸውን የሚያውቅ የለም እልፍ አእላፍት ወት እልፊት ብዙ የብዙ ናቸው፡፡ራዕ5÷1  በመንፈሳዊ አለም እየኖሩ በሠማይም በምደርም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መንፈሳዊ ሥራ ይሰራሉ፡፡ በዚህም ተፈጥሯቸው ከእግዚአብሔርና ከቅዱሳን ሰዎች ጋር  አንድነት አላቸው፡፡ ከተፈጠሩበት ዕለትና ሰዓት ጀምሮም ከቅዳሴና በምሳሌ አልተለዩም፡፡ ኢሳ 6¸3 ለእ 48፡፡ ምሥጋናቸው ዕረፍታቸው ዕረፍታቸውም ምሥጋናቸው ነው፡፡ ከዚህም ጋር የእግዚአብሔርን ጸጋ ምህረት ወደ ሰው የሰውን  ጸሎትና መስዋዕት ወደ እግዚአብሔር ያደረሳሉ፡፡ 7 ዳ 9¸22 የሐ 10¸4፡፡
v ቅዱሳን ሰዎች
ቅዱሳን ሰዎች ለተለያዩ ግባር ነገር ግን ለአንድ አላማ የተጠሩ ሰዎች ናቸው መጠራት ብቻ ሳይሆን የተመረጡ ናቸው፡፡ “ የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቆች ናቸው”፡፡ የተገለው ዚህ ነው ማቴ 22¸10 ስለሆነም ከብዙዎች መካከል ለይቶ የመረጣቸው ቅዱሳንን መልሶ ከብዙኃኑ ጋር መቀላቀል አይገባም፡፡ ይኽንን በተመለከተ ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ እናንተም የክርስቶስ አካላት ናችሁ፡፡ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ፡፡ እግዚአብሔርም በቤተክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን ሁለተኛም ነቢያትን ሦስተኛም አስተማሪዎችን ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ እርዳታንም አገዛዝንም፡፡ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል፡፡ ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ ተአምራት ይሰራሉን? ነገር ግን ሚበልጠውን የፀጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ፡፡” ብሏል 1 ቆሮ 12 ¸ 47 በመሆኑም እግዚአብሔር የልጁን መልክ እንዲመስሉ ወስኖ የጠራቸው የመረጣቸው የጸደቃቸውና ያከበረላቸው ነቢያት፣ ሐዋርያት ዳድቃን ሰማዕታት ነገስታት ካህናት አበው አርድእት ጳጳሳት መነኮሳት ሊቃውንት ደናግል ቅዱሳት አንስት ምዕመናን ቅዱሳን ናቸው፡፡ እነሱንም በአጭር በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታቸዋን፡፡
1) ቅዱሳን ነቢያት
ሃብተ ትንቢት ከእግዚአብሔር ተሰጥቷቸው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ በእርግጠኝነት የሚናገሩ ናቸው፡፡ የሚናገሩትም “ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” እያሉ ነው 1 ሳሙ 9¸6,7  አሞ 1¸3¸6¸9, 7 ሚክ 3¸8፡፡ ሚገለጥላቸውም በራእይ መህልምና በመልአክ ነበር፡፡ ዘን 12¸6,7 ዳ10¸11፡፡ ለዚህም ስራ ከእናታቸው  ማህፀን ጀምሮ ጠርቶ መርጧቸዋል 7 ኤር 1¸4-10 ቅዱስ  ጴጥሮስ ስለ ነቢያት “ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩግን ቅዱሳን ሰዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ተነድተው ተናገሩ” ብሎላቸዋል 2 ጴ 1¸2፡፡ ጌታችንም በወንጌል “በነብይ ስም  የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል” በማት ተናግሮላቸዋል ማቴ 10¸4-1፡፡

2) ቅዱሳን ሐዋርያት
በነቢያት የተነገረው ቃለ ትንቢት መድረሱንና በዘመናቸው መፈጸሙን ለዓለም እንዴንስ ታምሩ ጌታችን ራሱ “ኑ ተከተሉኝ” ብሎ የጠራቸውና የመረጣው ናቸው፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ “ ለእናንተ የመንግስተ ሰማያት ምስጢር የማወቅ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡” ብሏቸዋል ማቴ 13¸10 አጋንንትም እንዲያወጡ ደዌን እና ህሙማንን እንዲፈወሱ ሙት እንዲያስገሱ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ማቴ 1¸9 ማር 16¸16 በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ካስረከባችው በኃላ “ በምድር የምታስሩት በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድር የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል”  በማለት ከምድር እስከ ሰማይ የሚሰራ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል ማቴ 16¸19 ከትንሳኤው በኃላም “ ኃጢያታቸውን ይቅር ይላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል የያዛችሁባቸውም ተይዞባቸዋል፡፡” በማለት አጽንቶላቸዋል ዮሐ 20¸23 በመጨረሻም “ ግልጋሎቼን አሰማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጎቼን አሰማራ” በሚል ቃለ ትዕዛዝ የምእመናንን ህይወት አስረክቧቸዋል፡፡ ዮሐ 21¸15 ይህም ስልጣን ከእነርሱ ጋር ሳያልፍ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ እንደሚኖር ሲገልጥላቸውም “ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ” ሚል ተስፋ አስጨብጧቸዋል ሜቴ 28¸20 ከዚህ ሁሉ ጸጋ ጋር ትልቁ ስራቸው ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ መስበክ ነበር፡፡ ማር 16¸15
3) ቅዱሳን ጻድቃን
ቅዱሳን  ጻድቃን የሚባሉት መላ ዘመናቸውን ከጣዕመ ዓለምና ከተድላ ዓለም ተለይተው ቤት ልሰራ ዘር ልዝራ ሳይሉ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው በፆም በፀሎት በስግደት በምናኔ ፀንተው የኖሩ ናቸው አኗኗራቸውም ድምጸ አራዊትና ጸብአ አጋንንትን ግርማ ሌሊትን ሳይሰቀቁ ዳዋ ጥሰው ደንጊያ ተንተርሰው ጤዛ ልሰው ነው፡፡ ይኸንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ ሁሉን እያጡ መከራ እየተቀበሉ እየተጨነቁ የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ ዓለም አልተገባቸውምና በመድረበዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ” ያለው ዕብ 11 ¸37 ¸38 ቅዱስ ዮሐንስም  “ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ፃድቅ ነው” ብሏል ዮሐ 3¸ 7 ጌታችንም በወንጌል  “ ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል ማንም ከእነዚህ ለታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዝመሩ ስም የማይጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋናው አይጠፋበትም” ብሏል፡፡ ማቴ 10 ¸41
4) ቅዱሳን ሰማዕታት
ቅዱሳን ሰማዕታት የሚባሉት “እግዚአብሔርን ካዱ ለጣኦት ሰገዱ ሲባሉ “እግዚአብሔርን አንክድም ለጣዖትም አንሰግድም” በማለት በዓላውያን ነገስታት ፊት ቀርበው ሳያፍሩና  ሳይፈሩ ስለ ፈጣሪያቸው የመሰከሩ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ተዘረዝረው የማያልቅ መከራ ተቀበለዋል ህይወታቸውንም ስለ ፈጣሪያቸው አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ይሕንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እስከ ሞት ተደበደቡ በሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፉ ከዚህም በላይ  በእስራትና በወህኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ በመጋዝ ተሰነጠቁ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ በማለት ገልጦታል፡፡ ዕብ 11¸35-36 ስለራሱም መከራ 2 ቆሮ 11 ¸ 23-28 ላይ ተናግሯል፡፡
ይህ ሁሉ መከራ ከእምነታቸው እንዳላናወጣቸው ሲናገር “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ራብ ወይስ ራቁትነት ወይስ ፍርሃት ወይስ ሰይፍ ነው? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደተፃፈ ነው” ብሏል ሮሜ 8 ¸35-36 መዝ 43 ¸22፡፡
5) ቅዱሳን አበው
መጻህፍት ሳይፃፍላቸው መምህራን ሳይላኩላቸው በሕገ ልቡና ብቻ በቃል የተላለፈላቸውን ይዘው እንዲሁም በሥነ ፍየጥረት በመመራመር ፈጣሪያቸውን አምነው እርሱ የሚወደውን ሥራ የሰሩና በአካባያቸው በነበረው የጣኦት አምልኮ ራሳቸውን ያላረከሱ ሰዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ አባ ብዙኃን አብርሀምን መጥቀስ እንችላልን መጽሐፈ ኩፋሌ 10  ¸42-44 እና 11  ¸1 ላ እንደተጠቀሰ አባቱንና ጣኦት ዓመልኩ የነበሩ ሰዎችን ከጣኦታት ምንም የምናገኘው ጥቅም የለንም ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን አምልኩል በማለት ይክራቸው ነበር አብርሀምን መሰሉ ሕገ ኦሪት እክትሰጥ የነበሩ ሁሉ ይጠሩበታል፡፡
6) ቅዳሳን ነገሰታት
እንደ አህዛብ ነገስታት በሰልጣናቸው በሀብታቸውና በሠራዊታቸው ሰይመኩ ሃይማኖት ይዘው ምግባር ሰርተው የተገኙ ናቸው፡፡ የሚመሩትንም ህዝብ ፍርድ ሳያጓድሉ ደሀ ሳይበድሉ ጉቦ ሳይቀበሉ ለሰው ፊት ሳያዳሉ አስተዳድረዋል፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ዳዊት አንዳንዶቹም አለምን በመናቅ በምናኔ ኖረዋል ለምሳሌ በሀገራችን እኔ አፄ ካሌብ እነ አብርሃና አጽብአ እና አዳ ላሊበላ እነ ይመርሐነ ክርስቶስ ወዘተ…
7) ቅዱሳን ሊቃውንት
ቅዱሳን መጻሕፍትን በእግዚአብሔር መንፈስ ገላጭነት በመተርጎም ምእመናንን በሃይማኖት ያጸሉ ናቸውው፡ መናፍቃን የተሳሳተ ትምህርት ታዘው ሲነሱም መጽሐፍ አልባው ኃይለ ቃል አስበው ተከራክረው የረቱ ናቸው፡፡ ሃይማኖት እንዳይጠፋ ትምህርቱም እንደይፋለስ ሌት ቀን በማስተማር ብዙ ደቀ መዛሙርትን የፈሩ ናቸው፡፡ ይህንንም ተግባር ሲፈጽሙ መንገዱ ሁሉ አልጋ ባልጋ ሆኖላቸው ሳይሆን በችግር ላይ እየተረማመዱ ነበር፡፡ እሳቱም ስለቱም እስራቱም ግርፈቱም አልቀረላቸውም እነዚህም እነ ቅዱስ አትናቄዎስ ቅዱስ ቄርሎስ ስና ቅዱስ  ዮሐንስ አፈወርቅን የመሳሰሉ ናቸው፡፡
8) ቅዱሳን ጳጳሳት
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዘብሔርን ቤተ ክርስቲያን ይጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ከሄድሁ በኃላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ ደቀመዛሙርትንም ወደ ኃላቸው ያስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሱ እኔ አውቃለሁ” ሐዋ 20 ¸29-31 በተባለው መሠረት የካህናትና የምዕመናን የሰማያውያንና ምድራውያን አንድነት የሆነችውን ቤተክርስቲያን በሃይማኖት መርታዋል፡፡ ቤተክርስቲያን ጠላቶች ከአህዛብና ከመናፍቃን ጋር ታግለዋል፡፡ በአጠቃላይ ጳጳሳቱ መነኮሳቱ ቀሳውስቱ ዲያቆናቱና ምዕመና በቤተክርስቲያኗ ላይ የነደደው እሳት ሁሉ ነድዶባቸዋል፡፡ ቅዱሳን የተወለድት ከዚህ መከራ ከበዛበት አገልግሎት ውስጥ ነው፡፡
9) ቅዱሳን መነኮሳት (ደናግል)
“ያላገበው ጌታን እንዴት ደስ እንደሚያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፣ የገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲየሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል ልቡም ተከፍሏል ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም የአንዲቀዶሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፣ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች” /1ቆሮ 7 ¸ 32 ¸34/ እንደተባለ የዓለምን ነገር ትተው መንፈሳዊውን ነገር ብቻ የመረጡ ናቸው፡፡ ከሕገ እንስሳ ሕገ መላእክት ይበልጣ ብለው ራሳቸውን ለክርስቶስ አጭተው ከሴት ወይም ከወንድ ርቀው ንጹ ጠብቀው ስለ መንግስተ ሰማያት ብለው ራሳቸውን ጃንደረቦች ያደረጉ ናቸው፡፡ ሜታ 19  ¸ 12 እነዚህም ፈቲው እንስሳዊትን ድል የነሱ ከቀድሞ ሰዎች የነቢዩ የኤልንስን ከኃላ ሰዎች ደግሞ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን መንገድ የተከተሉ ደናግል በመሆናቸው ቅዱሳን መነኮሳት ይባላሉ፡፡
10) ቅዱሳት እንስት
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መርጦ ካስከተላቸው መቶ ሃያ ቤተሰቦች መካከል ሠላሳ ስድስቱ ቅዱስት አንስቷ ነበሩ፡፡ እነዚህም ተጠርተው ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የተከተሉና ያገለገሉ ናቸው፡፡ በተሰቀለበት እለትም አልሸሹም በመቃብሩ ዙሪያ ተገኝተዋል የትንሳኤው ምስክሮችም ሆነዋል፡፡ ከዚህም በኃላ ከቅዱሳን ሐዋርያት ሳይለዩ  ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት ታላቅ  ድርሻ አበርክተዋል፡፡ በየጊዜውም ንፅሕናንና ቅድስናን ገንዘብ አድርገው እነዚህን አርአያ አድርገው መከራ በበዛበትና በጸናበት የክርስትና ጎዳና የተጓዙ እናቶችና እህቶች ሁሉ ቅዱሳት አንሳት ይባላሉ፡፡ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ከእሲተ አብርሀም ሳለን በሃይማኖትና በምግባር የሚመስሏትን ሴቶች ሁሉ “ ቅዱሳት አንስት” ብሏቸዋል፡፡ 1ጴጥ 3 ¸3
v ቅዱሳት መካናት
እግዚአብሔር በመዝሙር በቅዳሴ በመዝሙር በቅዳሴ በማኀሌት ይገለገልባቸው ዘንድ የመረጣቸው ቦታዎች ገዳማትና አድባራት ቅዱሳት ናቸው፡፡ ከቦታ ሁሉ ተለይተው የከበረ ናቸው እግዚአብሔር ታላላቅ ስራዎች የሠራባቸው ለምሳሌ የእግዘብሔር ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ የሚፈትባት ፀሎት የሚሰረይበት ቦታ ቤተክርስተያን ቅድስት ናት እንዲሁም እግዚአብሔር በቀጥታም ሆነ በወዳጆቹ እያደረ ልዩ ልዩ ስራ የሰራባቸው ቦታዎች የተቀደሱ ናቸው ቅዱሳት መካናት ይባላሉ፡፡
እግዚአብሔር የሚገለጽበት ስፍራ ቅዱስ መሆኑን ለሙሴ እንዲህ ሲል ነግሮታት “ ሙሴ ሙሴ ሆይ አለ… ወደዚህ አትቅረብ አንተ የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ” ዘይ 3 ¸5 እንዲሁም ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ደብረ ታቦር ተራራ “ በቅዱስ ተራራ ይህን ድምጽ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን” በማለት ቦታው የተቀደሰ መሆኑን ገልጧል ፡፡2ጴጥ1 ¸16-18
የእግዚአብሔር ማደሪያው ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስለመሆኑ በቅዱስ መጽሐፍ በከፊል ተገልጿል፡፡ ለአብነትም የሚከተሉት ጥቅሶች ይህን ያስረዳሉ
·                   “ኬታ መቅደሱ ቅዱስ ነው በእውነትም ድንቅ ነው” መዝ 64 ¸5
·                   “አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚህ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ያይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ” 2 ዜና 7  ¸16
“ከእግአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሀሉ ቤቱም እውነት አምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ነው”፡፡ 1 ጢሞ 3 ¸15
v ቅዱሳት ዕለታት
እግዚአብሔር አበይት ሥራዎችን የሠራባቸው ዕለታት የተቀደሱ ናቸው፡፡ “ተዝካረ ገብረ ለስብሐቲሁ ፡- ለተዓመራቱ መታስቢያ አደረገ” እንዲል መዝ 110  ¸ 4 ይኸውም እግዚአብሔር ድንቅ ስራ የሠራበትን ቀን በዕለቱ ያደረገልንን ድንቅ ሥራ እያሰብን የእግዚአብሔርን ከሃሊነቱን ገናናነቱን እንዲሁም ቸርነቱን እንድናስተውልና እንድናዘክር ነው፡፡ ለምሳሌም እግዚአብሔር ፍጥረታችን ተፈጥሮ የፈፀመበትን ሰባተኛውን ቀን ቀድሶታል፡፡ “ እግዚአብሔር የስራውን ስለ በሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፡፡” ዘፍ 2 ¸ 2-3
ስለዚህ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ሰው ሆኖ የተወለደበትን ዕለት ልደቱን ተሰቀለበት ዕለት ስቅለቱ ሞትና የመቃብርን ይዞ የማስቀረት ኃይል አጥፍቶ የተነሳበት ዕለት ትንሣኤው ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ጥናት አኗኗሩ ያረገበት ዕለት ዕርገቱ እና መንፈስ ቅዱሳን ለሐዋርያት የላከበት ዕለት የተቀደሱ ዕለታት ናቸው፡፡
v ቅዱሳት ነዋያት /ንዋያተ ቅዱሳት/
ለእግዚአብሔር ሆነ ሁሉ ቅዱስ ነውና በቤተ መቅደስ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ ነዋያተ  በሙሉ የተቀደሱ (የተለዩ) ናቸው፡፡ እነዚህም ወደ ቤተመቅደስ ከመግባታቸውና ለአገልግሎት ከመዋላቸው በፊት በካህናት ተገቢው ጸሎት የተደረጉባቸው በቅብአ ሜሮን ከከበሩ በኃላ ለአገልግሎት ይውላሉ፡፡ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳቱ ታቦት ያድርበትና መስዋዕት ይቀርብበት የነበሩትን ነገሮች ሁሉ እንዴት እንደሚያከብራቸውና እንደሚቀድሳቸው ለሙሴ እንዲህ ሲል ልዑል እግዚአብሔር ነግሮታል፡፡ “ በዙሪያውም  አደባባዩን ትተክላለህ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ትዘረጋለህ፡፡ የቅብአቱንም ዘይት ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ ትቀባለህ እርሱንም ዕቃውንም ሁሉ ትቅድሳለህ ቅዱስም ይሆናል፡ ለሚቃጠል መስዋዕት ሚሆነውም ሁሉ መስዊውን ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፡፡ መሰዊያውም ትቀድሳለህ መሰዊያውም ቅድስተ ቅዱሳን ይሆናል፡፡” ዘይ 40  ¸6-10 እንዲሁም በዚዳግም  ላይ “ የመገናኛውንም  ድንኳን የምስክሩንም ታቦታ ገበታውንም ዕቃውም ሁሉ መቀረዙንም ዕቃውንም የዕጣን መስዊያውንም ለሚቀጠል መስዋዕት የሚሆነውን መሰዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ የመታጠቢያ ሳህንና መቀመጫውንም ትቀባበታለህ፡፡ ሁሉንም ትቀድሳቸዋለህ ቅድስተ ቅዱሳንም ይሆናሉ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል፡፡” ብሎታል ዘዳ 30 ¸ 22-29 እንግዲህ በብሎይ ኪዳን ቤተ መቅደስ የነበሩ ነዋያት ይህንን የህል ቅዱሳን ከሆኑ በክርስቶስ ደም ላይ የተመሰረተችው በአዲስ ኪዳን ቤተ መቅደስ የሚገለገልባቸው ንዋያት ይበልጥ የተቀደሱ በሚገባም ሚነካቸውም ይበልጥ እንደሚቀደስ ልናስታውል ይገባናል፡፡
v ቅዱሳት መጻሕፍት
በመሠረቱ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚባሉት ብሎያት ሀዲት መፃህፍተ መነኮሳት ሊቃውንት እንዲሁም አዋልድ መጻሕፍት ናቸው፡፡ እኛ ግን አሁን ትኩረት ሰጥተን የምንመለከተው 81 ሰማንያ አንዱን 46 ብሉያትና 35  ሀዲሳት በጥቅሉ መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ ሚጠራውን ነው ቅዱሳን ነቢያትና ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው በተለያየ ዘመንና በልዩ ልዩ ቋንቋ የጻፋቸው ከሐሰት ከኑፋቄ የተለያዩ ሰውን ለንፅህናና ለቅድስና ሚያበቁ መጻሕፍት በመሆናቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ለመባል በቅተዋል፡፡

ሦስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቃውንት በፀሎተ ሃይማኖት ወይም በአንቀጸ ሃይማኖት ላይ “ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፍ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ከማለት የብሉይና ሀዲስ ኪዳን መጻህፍት በጥቅሉ ቅዱሳት መጻሕፍት እደሚባሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ሐዋርያው  ቅዱስ ጳውሎስም ስለ መፃህፍቱ ቅዱስነትና ስለ አገልግሎቸው “ ቅዱስ መጽሐፍን ከህፃንነትህ ጀምሮ ከማን እንደተማርክ ታውቃለህ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ሊያድንህ ሚችለውን በእግዚአብሔር መንፈስ ምክር ደግሞ ይጠቅማል” በማለት ገልፆልናል፡፡ 2ኛ ጢሞ 3¸15-17 2ኛ ጴጥ 1¸21 መፃህፍቱን ቅዱሳት ያሰኛቸው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ስለጻፋቸው ነው፡፡ ቃሉም የእግዚአብሔር ነው፡፡ እንዲሁም ሰውን በመምከር ከክፋት ከክህደት ወደ መልካም ስነ ምግባርና ወደ እምነት  ስለሚያመጡ ነው ይኸንን በተመለከተ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ ባዕድ ቃል (ልብ ወለድ ፈጠራ) ወደ ልባችን እንዳይገባ ቃላተ መለኮትን ማድመጥ ይገባናል” ብሏል፡፡ ቅዱስ ስዊሮስ ዘእስጨናይ” ማሕፍት አምላካውያት የእግዚአብሔር እስትንፋስ ናቸው፡፡ እንዲሁም ደግሞ መጽሀፍ ቅዱስ ሁሉን የፈጠረ የእግዚአበብሔር ቃል ነውና፡፡ እርሱም ክቡር ከፍጡር አሳብም ከፍ ያለ ነውና” ብሏል ቅዱስ ቄርሎስ ደግሞ በግዳዌ ድርሳኑ ላይ “ የቅዱሳትም መጻሀፍትን ትምህርት ማናቸውም ደግሞ ቢሆን የሚጠግበው የልም ይልቁንም ደግሞ ቢሆን የሚጠግበው የልም፡፡ ጥይልቁንም ጥበብን ለሚሹ በልባቸው ማኃይየሚ አእምሮን ለተገነዘቡ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በምትወጣ ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ እንዳይድን ተጽፎአልና፡፡ የልቡና ምግብ ሰውንም የሚያበረታ መንፈሳዊ ኃብስት የእግዚአብሔር ቃል ነው” ብሏል ከዚህ በላይ የጠቀስባቸው የሊቃውንቱ ምስጢርራት አነጋገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ተገኝተው መጽሐፍ ቅዱስን የሚተረጉሙ ናቸው፡፡ ዮሐንስ 19¸19 ዕበ 4 ¸12 ኤር 23¸29 መዝ 118 ¸94-97 ማቴ 4¸4ሉ 10¸42 1ጢ 4¸13 ሉቃ 11¸28፡፡
v ቅዱሳት ስዕላት
በቤተክርስቲያናችን እግዚአብሔርን እመቤታችንን፣ ነቢያትን ሐዋርያትን ጻድቃን ሰማዕታትን እና ሊቃውንትን የሚያመለክቱ አያሌ ቅዱሳት ስዕላት አሉ ቅዱሳት መባላቸውም፡፡
·                   ሥጋዊውን ዓለም ከማንደባርቁ ዓለማውያን ሥዕላት ፈፅመው የተለዩ በመሆናቸው ነው፡፡
·                   የቅዱሳኑ ቅድስና ሥዕላቱም ቅዱሳት ያሠኛቸዋል፡፡
·                   ሥዕላቱ በራሳቸው የሚያደርጉት ገቢረ ታአምራት ቅዱሰት አስኝቷቸዋል፡፡
ቅዱሳት ስዕላት የተሳሉት በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን ሥዕለ ኪሩብን እንዲያአጋጅ ለሙሴ እግዚአብሔር አዞታል፡፡ ስዕሉንም ከታቦቱ አጠገብ እንዲያስቀምጥ ነግሮታል፡፡ በመጨረሻም “ከዚያም ከአንተ ጋር እገኛለሁ የእስራኤልንም ልጆች ታዘዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ በምስክሩ ታቦት ላይባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ አነጋግርሀለሁ” ብሎታል ዘይ 25¸21-22 በዚያም በስዕለ ኪሩብ እየተጋለጠ እንደሚያነጋግረው ቃል ገብቶለታል አነጋግሮታልም፡፡ “ ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን እርሱን ለመነጋገር ከገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ በኪሩቤልም መካከል ድምጽ ሲናገረው ይሰማ ነበር” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ዘኃ7¸8-9 ከዚህም በሥዕል ፊት ቆሞ መሳለም እንደሚገባ ያስተምሩናል፡፡ ዳግመኛም በአስሩም የቤተ መቅደስ መጋረጃዎች ላይ ሥዕለ ከሩብን እንዲስል ለሙሴ የታሰጠው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ይኸንኑ ማያጠናክር ነው፡፡ ዘይ 21¸1 በዚህ አይነት ለሙሴ በተጠው የሥዕል መነሻና መሠረት ሆኖ ለሥርተ አምልኮ መፈፀሚያ ይሆናል፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር በሰጠው ነገር መጠቀም  ለማንኛውም ሰው ሃማኖታዊ ግዴታው ነው፡፡ እንዲሁ ንጉስ ሰለሞንም ቤተ መቅደሱን በጨረሰ ጊዜ ስዕለ ኪሩብን በቅድስት ቅደዱሳኑ ውስጥ አስቀምጧል፡፡ በቤተ መቅደሱም ግንብ በውጭና በውስጥ የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳ አበባ ሥዕሎችን ሰርቷል፡፡ 1ነገ 6¸23-24 እግዚአብሔርም ይህንን ስራውን ሁሉ ወድዶና ፈቅዶ ተቀብሎለታል 2ዜና 7¸11-12 እንዲዘሁም በሀዲስ ኪን ብዙ ስዕላት ይሳላሉ የብሉይ ኪዳን ስዕላት ለሀዲስ ኪዳን መሠረቱ ነውና ጌችን ብዙ ጊዜ በሰሎሞን  በሠራው መቅደስ እየተገኘ ያስተምር ነበር፡፡ ድውዮችንም ይፈውስ ነበር በቤተመቅደስ እርግብ        ሻጮችና ለዋጮች የንግድ ቤት ባደረጉት ጊዜ ሁሉንም ጠራርጎ አስወጥቷል በቤተ መቅደስ ስዕል ቢያስፈልግ ኖሮ ሥዕሉንም ከቤተ መቅደስ ባወጣ ነበር ማቴ 21 ¸1-13 2 ኢሳ 56¸7 የአዲስ ኪዳን ሥዕላት በስፋት ይሳሉ የነበረው በዋሻ ውስጥ (ካታ ኮምፕ) ግበበ ምድር ነበር ምክንያቱም የመጀመሪያዎቹ ምዕመናን እምነታቸውን በነፃነት ለመግለጽ ይቸገሩ ስለነበር ነው፡፡ በዚያም በዋሻ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያአክሩ ስዕላት ይሳ ነበር ለምሳሌ እረኛ በጎን እንደተሸከመ “ አር እረኛ መልካም እረኛ እኔ ነኝ” ዮሐን 10 ¸11 የቅዱስ ገብርኤል ብስራት የመዳነ መዳን የጌታ ልደት በቤተልሔም የጌታ ስቅለት የጌታ ትንሳኤ እርገት ደግሞ መምጣቱን የሚገልጹ ስዕላት ይሳሉ ነበር፡፡ ሐዋርያውም ስለ ስዕላት “ እናንተ የማታስታውሉ የገላቲያ ሰዎች ሆይ ጌታ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሰቅሎ ነበር” ብሏል፡፡ ገላቴ 3¸1፡፡
ምዕራፍ ሁለት
የቅዱሳን የገድል ሕይወት
አስቀድመን ለመግለጥ እንደሞከርነው የቅዱሳን ሕይወት በገድል የተሞላ ነው ጌታችን በወንጌል “ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ” ዮሐ 16÷33 በማት እንደተናገረው ቅዱሳንም በፍፁም ትዕግስት በመከራ መካከል አልፈዋል፡፡ በሰይፍ ተመትረዋል በመጋዝ ተተርትረዋል በእሳት ተቃጥለዋል ተርበዋል ተጠምተዋል ታርዘዋል ሆኖም ግን “ ወንድሞች ሆይ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲበዛባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት “ ያዕ 1÷2-3 እንደተባለው መከራውን ሁሉ በደስታ ተቀብለዋል፡፡ የተጋደሉትም እስከ ሞት ድረስ ነው፡፡ “ እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን የሕይወት አክሊል (መንግስተ ሰማያትን) እሰጥሀለሁ፡፡ ” ተብሏል ራዕ2÷10 በዚህም ጉዞ ፈተና ከተለያየ አቅጣጫ አጋጥሟቸዋል፡፡
2.1 ቅዱሳን መከራ የሚቀበሉት ከማን ነው?
ቅዱሳን መከራ የሚቀበሉት ከተለያየ አቅጣጫ ነው፡፡ ይህንንም እንደሚከተለው ዘርዘር አድርገን እናየዋለን፡፡
ሀ) ከፈቃደ ሥጋቸው
     በመንፈሳዊ ህይወት ትልቁ ከፈቃደ ሥጋ ጋር የሚደረገው ትግል ነው ይኸውም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ለማስገዛት የሚፈፀመው ገድል ነው፡፤ ሐዋርው ቅዱስ ጳውሎስ ይኸንን በተመለከተ “ ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ (ፈቃደ ነፍሳችሁን ስሩ) የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈፅሙ፡፡ ሥጋ በመንፈስ ላይ (በነፍስ) ላይ መንፈስም (ነፍስም) በሥጋ ላይ ይመኛልና እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቃዋወማሉ ” ብሏል ገላ 5÷16-17 ከዚህም በማያያዝ “ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር ፣ ደስታ ፣ ሰላም ፣ ትዕግስት ፣ ቸርነት በጎነት ፣ እምነት ፣ የውሃት ፣ ራስን መግዛት ነው እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ህግ የለም፡፡ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑት ሥጋን ከክፉ መሻቱ ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ ” በማለት በብዙ ተጋድሎ ፈቃደ ሥጋቸውን እንዳሸነፉ ተነግሯል፡፡ ገላ 5÷22-24 በሮሜ መልክቱም “እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በመሞት ሥጋችሁ ኃጢያት አያንግስ ብልቶቻችሁንም የአመፃ የጦር እቃ አድርጋችሁ ለኃጢያት አታቅርቡ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ ኃጢያት አይገዛችሁምና ” በማለት መክሯል፡፡ ሮሜ 6÷12-14 አብርሃም ከሀገሩ የወጣው ከዘመዶቹ የተለየው ፈቃደ ሥጋውን አሸንፎ ነው፡፡ ዘፍ 12÷1 ያዕቆብ የብኩርና ምርቃትና በረከት ያገኘው ፈቃደ ሥጋውን አሸንፎ ነው፡፡ ዘፍ 25÷1 ዮሴፍ የጌታው (የጵጥፋራ) ሚስት ያቀረበችለትን የዝሙት ግብዣ ሳይቀበል ፈተናውን ያለፈው ፈቃደ ሥጋውን በማሸነፉ ነው፡፤ ዘፍ 34÷7 ሙሴ ሥልጣንን ሀብትን ንብረትን የፈርኦን የልጅ ልጅ መባልን ንቆ ከቤተ መንግስት ወጥቶ የመነነው ፈቃደ ሥጋው በማሸነፉ ነው፡፤ ዕብ 11÷24-26 ዘፀ 2÷10፡፡
     በአጠቃላይ ቅደሳን ሁሉ ዓለምን ጠልተው እግዚአብሔርን ወድደው እስከ መጨረሻው ያገለገሉት ውስጣዊ/ውጫዊ/ ፈተናን ወይም ፈቃደ ሥጋቸው አሸንፈው ነው፡፡ ምክንያቱም ለፈቃደ ሥጋ ተሸንፎ ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ነውና፡፡ ያዕ 4÷4 በመሆኑም መክፈል የሚገባቸውን መሥዋዕትነት ከፍለው ፈቃደ ሥጋቸውን በመግደል ከዓለም ተለዩ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት (ዓለም በእኔ ዘንድ ሙት የሆነበት) እኔም ለዓለም የተሰቀልኩበት (እኔም በዓለም ዘንድ ሙት የሆንኩበት) ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ ያለው ለዚህ ነው ” ገላ 6÷14
ለ) ከዓላውያን ነገሥታት
     ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት “ በነገሥታት ፊት ቃልህን እናገራለሁ አላፍርም ” መዝ 118÷46 እንዳለ ቅዱሳን ከማያምኑ ነገስታትና መኳንንት ጋር ታግለዋል፡፡ ጌታችንም በወንጌል “ ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡዋችኋል በምኩራቦቻቸውም ይገርፏችኋል ከሰዎች ተጠበቁ ለእነርሱና ለአህዛብም ምስክር እንዲሆን ስለ እኔ ወደ ገዢዎች ወደ ነገስታትም ትወሰዳላችሁ ” ብሏል ማቴ 10÷17-18 ነቢዩ ኤልያስ ከአክአብና ከንግስቲቱ ከኤልዛቤል ያጋጠመው ችግር ቀላል አልነበረም፡፡ ፈተናው የከበደው ሞቱን እስኪመኝ ድረስ ነበር፡፡ 1ኛ ነገ 19÷4 ንጉሱ አካዝያስም ታግሎታል፡፡ 2ኛ ነገ 1÷9 የሶርያው ንጉስ ፈረሶችንና ሰረገሎችን በመላክ ነቢዩ ኤልሳዕን ታግሎታል፡፡ 2ኛ ነገ 6÷14 ናቡከደነፆር ሰለስቱ ደቂቅን ወደ እሳት ነቢዩ ዳንኤልን ደግሞ ወደ አናብስት ጉድጓድ ጥሏቸዋል፡፡ ዳን 3÷22 ት.ዳን 6÷16፡፡ የአራተናው ክፍል ገዢ ሄሮድስ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን አንገት አስቆርጧል፡፡ ማቴ 14÷10 ንጉስ ሄሮድስ ቅዱስ ያዕቆብን በሰይፍ ገድሎታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስን በሰንሰለት አስሮ ወደ ወህኒ ቤት ወርውሮታል፡፡ የሐዋ.ስራ 12÷1 ቅዱስ ጴጥሮስን ቁልቁል ሰቅለው ቅዱስ ጳውሎስን ደግሞ በሰይፉ አንገቱን ቆርጠው የገደሉት ዓላውያን የሮማ ነገሥታት ናቸው፡፡
ሐ) ከመናፍቃን
      ቅዱሳን በመናፍቃን የደረሰባቸው መከራ በዓላውያን ነገስታት ከደረሰባቸው መከራ የሚተናነስ አይደለም፡፤ በየጊዜው ከተነሱ የሃይማኖት ለዋጮች ጋር እስከ ደም ጠብታ ድረስ ተጋድለዋል፡፡ ጌታችን ስለመናፍቃን አስቀድሞ በወንጌል “ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣችው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሀሰተኞች ነቢያት (መምህራን) ተጠንቀቁ፡፡ ” ብሏል ማቴ 7÷15 ስለዓለም መጨረሻ(ምዕራፍ በተናገረበት) ምልክት በተናገረበት ምዕራፍም “ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ … ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሳሉ ብዙዎችንም ያስታሉ … በዚያ ጊዜ ማንም እነሆ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢሏችሁ አትመኑ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሳሉና ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” በማለት ተናግሯል ማቴ 24 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንደገቡባችሁ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሱ እኔ አውቃለሁ፡፡”  የሐዋ.ስራ 20÷29-30 ቅዱስ ጳውሎስ የማይራሩ ጨካኞች ያላቸው በቅዱሳን ላይ መከራ ስለሚያደርጉ ነው፡፡ በሁለተኛው የቆሮንቶስ መልዕክቱ ደግሞ “ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ ” ብሏል 2ቆሮ 11÷26 ሐዋርያዊው አትናትዮስም አርዮሳውያንን በሰሩት ደባ ብዙ ጊዜ ከመንበሩ እንደተሰደደ የቤተክርስቲያን ታሪክ ዘጋቢዎች መዝግበውታል፡፡ (ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ ገጽ 124)
መ) ከጠንቋዮች
      ጥንቆላ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ተግባር መሆኑን ነቢዩ ሙሴ ሲናገር ለህዝቡ እንዲህ ነው ያለው “ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አህዛብ የሚያደርጉትን ርኩሰትን ታደርግ ዘንድ አትማር ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የማሰልፍ ምዋርተኛም ሞራ ገላጭም አስማተኛም በድግምት የሚጠነቁል መናፍስትንም የሚጠራ ጠንቋይም ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ ይህም ሁሉ የሚያደርግ  በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው ” ዘዳግ 18÷11 የግብፅ ጠንቋዮች ቅዱሳኑን ሙሴንና አሮንን ተቃውመዋቸው ነበር፡፡ ዘጸ 7÷8 በርዳሱስ የተባለው ጠንቋይ እውነተኛውን ወንጌል እያጣመመ እና ቅዱስ ጳውሎስን አውኳቸው ነበር፡፡ የሐዋ.ስራ 13÷10 በሟርተኝነት መንፈስ እየጠነቆለች ለጌቶችዋ ብዙ ገንዘብ ታመጣ የነበረችውን ሴት ሐዋርያት በፈወሷት ጊዜ መከራ ደርሶባቸዋል፡፡ ከሲላስ ጋር ወደ ወህኒ ቤት ወርውረዋቸዋል ከግንድ ጋር አጣብቀው አስረዋቸዋል፡፡ የሐዋ.ስራ 16÷16-24
ሠ) ከአህዛብ
       እንጨት ጠርበው ደንጊያ አለዝበው ጣዖት የሚያመልኩ አህዛብ ቅዱሳንን ታግለዋቸዋል፡፡ በእሳት አቃትለው በስለት ቆራርጠው ገድለዋቸዋል፡፡ ነቢዩ ኤርሚያስ ለአህዛብ መምህርነት እግዚአብሔር በመረጠው ጊዜ “ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር እነሆ ብላቴና ነኝና እና እናገር ዘንድ አላውቅም ” ያለው አህዛብ የሚያደርጉበትን መከራ አስቦ በመፍራት ነበር እግዚአብሔር ግን “ ብላቴና ነን አትበል፡፡ እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና ከፊታቸው አትፍራ፡፡ ” አለው ት.ኤር 1÷4 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም አህዛብ መከራ አጽንተውበት እንደነበር በመልእክቱ ላይ ገልጧል፡፡ 2ኛ ቆሮ 11÷26
ረ) ከአጋንንት
     ጥንቱንም ቢሆን በዓላውያን ነገስታት በመናፍቃን በጠንቋዮችና በአህዛብ እንዲፈሩ የሚዋጉአቸው መከራም የሚያጸኑባቸው አጋንንት ናቸው፡፤ ከዚህም አልፈው ረቂቃኑ ገዝፈው በመታየት በገሃድ ይዋጋቸዋል፡፤ ቅዱሳንን በደንጊያ በመቀጥቀጥ ወደ ገደል በመጣል ወደ ባሕር በመጨመር ጉሮሮአቸውን በማነቅ ፊት ለፊት ይተናነቋቸዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና ” በማለት እንደተናገረው አጋንንት ለክፋት እረፍት የላቸውም፡፤ ቅዱሳን ዋሻ ዘግተው ቢቀመጡ ከጋራ ቢወጡ ከባሕር ቢገቡ ወደ ምድረበዳ ቢወርዱ እየተከታተሉ መከራ ያጸኑባቸዋል፡፤ 1 ጴጥ 5÷8 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ ፡፡ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ፡፡ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና (ከሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት) ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ አለም ገዥዎች ጋር በሰማያዊ ስፍራም ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር ነው እንጂ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቃወም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሱ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላፃዎች ሁሉ ልታጠፋ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሱ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ፀልዩ ” ያለው ለዚህ ነው፡፡ ኤፌ 6÷10-18
2.2 መዓረጋተ ቅዱሳን
     መንፈሳዊ ህይወት የቅድስና ኑሮ እንደመሆኑ መጠን ከልደት (በጥምቀት ዳግም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስና ከማህፀነ ዮርዳኖስ በመወለድ) የሚጀምርና ደረጃውን የጠበቀ እድገት ያለበት ሕይወት ነው፡፡ “ … ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደተወለዱ ህፃናት ተንኮል የሌበትን የቃሉን ወተት ተመኙ፡፡ ” 1ጴጥ 2÷3 ላይ ብሏል ስለዚህ የእግዚአብሔር ወዳጆች የሆኑ ቅዱሳን በአንድ ጊዜ የፍፁምነትና የቅድስና ደረጃ ላይ አይደርሱም ለምሳሌ የተወለደ ሕፃን ቀስ በቀስ ከመዳህ ወደ መቆም ከመቆም ወደ መራመድ ከመራመድ ወደ መሮጥና መዝለል እንደሚጀምር ሁሉ ቅዱሳንም ከወጣኒነት ጀምሮው ወደ ማዕከላዊነት ከዛንም በእግዚአብሔር ፀጋ እየታገዙ ወደ ፍፁምነት ይደርሳሉ ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት “ እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከት ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣል ከኃይል ወደ ኃይል ከብቃት ወደ ብቃት ከቅጽብና ወደ ፍፁም ቅድስና ይሸጋገራል ይሄዳል ያድጋል ” ሲል በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ የተናገረላቸው፡፤ መዝ 83÷7 ለዚህ ኃይል ቅድስናና ብቃት የሚያደርሳቸውም ራሱ ባለቤቱ እንደሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ “ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍፁማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታታችሁማል ” በማለት ተናግሯል፡፡1ጴጥ 5÷11
    በወጣኒነት ጀምረው ፈተናውን እያሸነፉ ወደ ማዕከላዊነት ሲጓዙ ከዚያም በመጨረሻ ወደ ፍፁምነት ብቃት ይደርሳሉ እነዚህም ሶስቱ የመንፈሳዊያን ደረጃዎች ወጣኒነት ማዕከላዊነትና ፍጹምነት የሚባሉት ሲሆኑ ጌታችንም በወንጌል ባለ ሰላሳ ባለ ስልሳና ባለመቶ ፍሬ ብሎ ሲጠቅሳቸው ቅዱስ ጳውሎስም ከዋክብት በጨረቃና በፀሐይ መስሏቸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ንጽሕ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ እና ንጽሐ ልቡና በመባልም ይታወቃሉ፡፡
     ቅዱሳን ደረጃ በደረጃ የሚደርሱባቸው አስር ማዕረጋት አሉ ሶስቱ ንጽሐ ሥጋ አራቱ በንጽሐ ነፍስ ሶስቱ ደግሞ በንጽሐ ልቡና ይገኛሉ፡፡
 በንጽሐ ሥጋ የሚገኙት ሶስቱ መዓረጋት፡-
1.)           ጽማዌ
2.)          ልባዊ እና
3.)         ጣዕመ ዝማሬ ናቸው
በንጽሐ ነፍስ የሚገኙት አራቱ መዓረጋት፡-
1.             አንብዕ
2.            ኩነኔ
3.            ፍቅር እና
4.            ሁሰት ናቸው፡፤
በንጽሐ ልቡና የሚገኙት ሶስቱ መዓረጋት፡-
1.             ንጸሬ መላእክት
2.            ተሰጥሞ ብርሃን እና
3.            ከዊነ እሳት ናቸው፡፡
እነዚህ መዓረጋት የሚገኙትና የሚደረስባቸው በቅደም ተከተላቸው ነው፡፡ ከላይ ያለውን መዓረግ የሚይዝ ታችኛው መዓረግ እንደያዘ በዚያው ላይ እየተጨመረለት ይሄዳል፡፡
     ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን መዓረጋት በሁለተኛው መልእክቱ በም.1 ቁ.5-9 ገልጾአቸዋል፡፡ “ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ በበጎነትም እውቀትን በእውቀትም ራስን መግዛትን ራስን በመግዛትም መጽናትን በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰልን እግዚአብሔርን በመምሰልም የወንድማማችን መዋደድ በወንድማማች መዋደድም ፍቅርን ጨምሩ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጓችኋልና፡፡ ”
     በዘሪው ምሳሌ ትምህርትም በመልካም መሬት ላይ ያረፈው ዘር ሰላሳ ስልሳ እና መቶ ፍሬ አፍርቷል፡፡ በዚህም ትምህርት ሰላሳ ያፈራው የወጣንያን ስልሳ ያፈራው የማዕከላውያን እና መቶ ያፈራው ደግሞ የፍጹማን ምሳሌ ነው፡፡ ማቴ
     ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ “ እነሆ የእግዚአብሔር በግ ” ብሎ ክርስቶስን ሲያመለክት የሰሙት ሁለት ደቀመዛሙርት ክርስቶስን ሲከተሉት “ እርሱም ምን ትፈልጋላችሁ? ” አላቸው፡፡ እነርሱም “ መምህር ሆይ ወዴት ትኖራለህ? ” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም “የማድርበትን ኑ እዩ” አላቸው፡፡ ሁለቱም የዮሐንስ ደቀመዛሙርትም “ ሄደው የሚኖርበትን አዩ በዚያም ቀን እስከ አስር ሰዓት ድረስ ዋሉ ” ይላል፡፡ ዮሐ 1÷35/41
     ወንጌላዊው እነዚህ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ወደ ክርስቶስ ሄደው ከእርሱ ጋር እስከ አስር ሰዓት ዋሉ ማለቱ ምስጢራዊ መልእክትን ያዘለ ነው፡፡ ይኸውም ወደ ክርስቶስ በሃይማኖት የሚሄዱ ከእርሱ ጋር ከኖሩ አስሩን መዓረጋት እንደሚያገኙ የሚያመለክት ነው፡፡
     አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሐዋርያት ፀጋ መንፈስ ቅዱስን ባረገ በአስረኛው ቀን /ዝቅ ብሎ በዘጠኝ ወይም ከፍ ብሎ በአሥራ አንድ ቀን ሳይሆን መሰደዱ (መላኩ) ምስጢር ያለው ነው፡፤ በእርሱ ዘንድ ሁሉ በጥበብ ይደረጋልና፡፡ መዝ 103(104)÷24 ይህም የሚያስረዳው እርሱን ለተከተሉና ትዕዛዙን ለፈፀሙ አስሩን መዓረጋት እንደሚያገኙ ነው፡፡
v ከዚህ ቀጥሎ ሶስቱን አበይት መዓረጋትና በውስጣቸው ያሉትን አስሩን ንዑስ መዓረጋት ትንታኔ እንመለከታለን፡፡
1.          ንጽሐ ሥጋ
ንጽሐ ሥጋ ከትሩፋት ስፋ (ጾም ፣ ጸሎትና ስግድት…) የሚገኝ ሆኖ ወጣንያን የሚደክሙላት መዓረግ ነው፡፡ በዚህ ጊዜም ሰይጣን ወጣንያኑን ለመጣልና ጣዕመ መንፈስ ቅዱሳን እንዳይቀምሱ ከማዕረግ እንዳይደርሱ ለማድረግ ክፉ ሀሳብና የተለያየ ፈተና እያዘጋጀ ይፈትናቸዋል እነርሱ ግን በተጋደሎ ድል ያደርጉታል ከላይ እንደተገለፀው ንጽሐ ሥጋ ሶስተ መዓረጋትን የያዘ ነው፡፤
Ø ጽማዌ
ጽማዌ ማለት ዝም ጸጥ ማለት መናገርና መቀባጠርን መተው ማለት ነው፡፡ በጥቅሉ ጽማዌ (አርምሞ) ማለት ዝምታ ፀጥታ ማለት ነው፡፡ ሕሊናቸውን ወደ እግዚአብሔር ለመስቀልና የእርሱን ስራ ለመዘከር ይችሉ ዘንድ ሕዋሳታቸውን የሚታየውን የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ ከማሰብና ከማውራት ይከለክሉታል፡፡
    ይኸውም ዝምታ አውቆ ፈቅዶ በመናገርና በመቀባጠር ከሚመጣው ኃጢያት መቆጠብ ነው፡፡ “ በቃል ብዛት ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው ” ተብሏልና ምሳ 10÷19 አንደበት ምንም እንኳን ትንሽ አካል ቢሆን ሰውነትን በኃጢአት እንደሚያሳድፍ ያዕቆብ በመልእክቱ “ አንደበት እሳት ነው አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመጸኛ ዓለም ሆኖአል ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና የፍጥረትንም ሁሉ ሩጫ ያቃጥላል በገሃነም ያቃጠላል፡፡ ” በማለት ተናግሯል ያዕ 3÷6-12 ቅዱስ ዳዊት የፈቃድ ዝምታ ለብቃትና ለተጋድሎ እንደሚያስፈልግ “ በአንደበት እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ አልሁ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ እንደማትሰማ ደንቆሮ በአፉ መናገር እንደማይችል ድዳ ሆንኩ ” በማለት ተናግሯል፡፡ መዝ 38÷2
     በዚህም መዓረግ መላእክትን ሲወጡና ሲወርዱ ያያሉ ነገር ግን ለምን እንደሚወጡና እንደሚወርዱ አያውቁም፡፡ ለምሳሌ ዮሐንስ ሐፂር ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም ሌሎች መላእክት በየመዓረጋቸው ሲወጡና ሲወርዱ አይቷል፡፡
Ø ልባዌ
ልባዌ፡- ልባዌ ማለት ልብ ማድረግ ማስተዋል ማለት ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል “መስማትን ትሰማላችሁ ነገር ግን አታስተውሉም ” በሚለው የኢሳይያስ ትንቢት የገሰፃቸው ማስተዋል (ልባዌ) ታላቅ መዓረግ በመሆኑ ነው፡፤ ማቴ 13÷10 ት.ኢሳ ጌታችን ደቀመዛሙርቱንም ብዙ ጊዜ “ ለበውክሙኑ? አስተዋላችሁን? ” ኋላቸው የነበረው ታላቅ መዓረግ በመሆኑ ነው፡፡ ማቴ 13÷5 ማቴ 8÷17 ከዚህ መዓረግ ሲደርሱ መላእክትን ከነስማቸው ከነግባራቸው ለምን እንደሚወጡ እንደሚወርዱ ሁሉ የሚያውቁበት ነው ከጽማዌ በኋላ የሚሰጥ መዓረግ ነውና እንዲሁም እርኩሳን አጋንንትንም ለይተው ያውቃሉ የሚያሰሩትንም ኃጢያት ያውቃሉ፡፡
Ø ጣዕመ ዝማሬ
ጣዕመ ዝማሬ ይህ መዓረግ ደግሞ ሳትሰለቹና ሳይቸኩሉ ምስጢሩንና ትርጓሜውን እየወጡ እየወረዱ በንቁህ ህሊና ማመስገንና መጸለይ ማለት ነው፡፡ ከዚህ መዓረግ የደረሱ ቅዱሳን ሲጸልዩና ሲያመሰግኑ ቢውሊ ቢያድሩ የማታሰለቻቸውም የማታደክማቸውም ምክንያቱም ምስጢሩ እየገባቸው በማስተዋል ስለሚያደርጉት ነው፡፡ “ እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉስ ነውና በማስተዋል ዘምሩ ” እንዲል መዝ 46÷7 አንድ ሰው የሚፀልየውን ጸሎትና የሚያቀርበውን ምሥጋና በትርጓሜና በምስጢር በውስጣዊ ልቡናው እንዳመጣ የሚያደርሰው ከሆነ ተመስጦን ገንዘብ ማድረግ ይቻለዋል ጸጋ መንፈስ ቅዱስንም እየተጎናጸፈ ከዚህ ከሥጋዊ ነገር በሙሉ ያመልጣል፡፡ ለዚህም ነው ንጽሐ ሥጋን እስከዚህ ባት ሶስት መዓረጋት ገንዘብ ማድረግ የሚቻለው በአገራችንም ስለቅዱስ ያሬድ የሚነግረው ታሪክ ይኸንን ነው የሚያስታውሰን ቅዱስ ያሬድ እግዚአብሔርን የገለጠለትን ሰማያዊ በሚዘምርበትና መቋሚያውን በሚዘምምበት ጊዜ ንጉስ አፄ ገብረ መስቀል የፃድቁ ረድኤት አድሮባቸው በተመስጦ ይሰሙት ነበረ፡፡ ሳያውቁትም እንደዘንግ በሚያዙት በርተ መስቀላቸው ከእግሩ ላይ ወግተውታል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ደሙም ሲፈስ ለቅዱስ ያሬድ አልተሰማውም፡፡ እንዲሁ ከጣዕመ ዝማሬ የደረሰ ኤንድ ባህታዊ ለብዙ ዘመናት ያህል “ አቡነ ዘበሰማያት አባታችን ሆይ ” ብቻ እያለ ያንኑ ብቻ እየመላለሰ “ ይትቀደስ ስምክ ስምህ ይቀደስ ” ሳይል ኖረ፡፡ መልአክ መጥቶ “ ይትቀደስ ስምከ ” በል እንጂ ቢለው፡፡ “ ኧረ ጌታዬ እኔስ “አባታችን ሆይ” የሚለው ኃይለ ቃል ምስጢሩና ጣዕመ በአፌ እንደ ስኳር እየሟሟ አልጠገበኝ ብሏል እንዴት አድርጌ ወደፊት ልሂድ ” አለው ይባላል፡፡
     ለመጸለይ የምን ስንፍና አንድ ጊዜ የጸለይነውን ጸሎት ለመድገም የምንሰለች ወይም ደግሞ ቶሎ ቶሎ ንባቡን ጨርሰን ለመቀመጥ የምቸኩል ከሆነ ምን ያህል ከጸጋ በታች የራቅን መሆናችንን ልናውቅ ይገባል፡፡ ቅዱሳንን ለዚህ ጸጋ ያደረሰ አምላክ እኛንም ሳንሰለች ለመጸለይ ለማመስገን እንድንችል ይርዳን፡፡
2.         ንጽሐ ነፍስ
ንጽሐ ሥጋ ከትሩፋት ሥጋ እንደሚገኝ ሁሉ ንጽሐ ነፍስም ከትሩፋተ ነፍስ ይገኛል ንጽሐ ሥጋ ማዕረግን ሲያልፉ ንጽሐ ነፍስ ማዕረግ ይደርሳሉ በንጽሐ ነፍስ ከረቂቅ ኃጢያት የሚናድበትና ልዩ ልዩ የሆነ የሰይጣን ጾር (ውጊያ) ድል የሚነሱበት ነው፡፡ በንጽሐ ነፍስ የሚገኙት አራቱ መዓረጋት የሚከተሉት ናቸው፡፡
Ø አንብዕ
አንብዕ፡- እንባ ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ የሚኖረው እንባ ከሌላው ይለያል፡፡ የሐዘን እንባ ሰው በደረሰበት ሐዘን ልቡ ተወግቶ ፊቱን አስከፍቶ የሚያለቅሰው ሲሆን የደስታው እንባ ደግሞ ልቡናው በሐሴት ተሞልቶ ሰውነቱ ስሜቱን መቆጣጠር ባቃተው ጊዜ የሚያለቅሰው ነው፡፡ “ አንብዕ ” ግን ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ ይኸውም ቅዱሳን ሰውነታቸው በሐዘን ሳይከፋ በሥጋዊ ሐሴትም ሳይሞላ ሳይሰቀቁ ከዓይናቸው እንባ እንደ ሰን ውኃ እንደ ነሐሴ ምንጭ የሚፈልቅ ነው፡፤ ይህም እንባ ቅዱስ ዳዊት “ ወባአንብዕየ አርሐስኩ ምስካብየ፡- በእንባዬም መኝታዬን አራስኩ ” እዳለው የቆመበትን ቦታ የዘረጉትን ምንጣፍ እስከማራስ የሚደርስ ነው፡፡ መዝ 6÷6 ለምሳሌ ቅዱስ አርሳንዮስ ሁልጊዜ ከማልቀሱ የተነሳ እንባው የሚወርድበት በደረቱ ላይ የጎደጎደ ልዩ ሰንበር አውጥቶ ነበር፡፡ ሌሎች የሚሰፉትን ስፌት ከፊቱ ሲያስቀምጡለት ዕንባው ያርስላቸው ነበር፡፡ ይህንንም በማድረጋቸው የተመሰገኑ (ብፁአን) ተብለው በጌታቸው ተመስግነዋል ይመሰገናሉም፡፡ “ የሚያዝኑ (የሚያለቅሱ) ብፁዓን ናቸው መጽናናትን ይገኛሉና (መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉና) ተብሎላቸዋል፡፡ ” ማቴ 5÷4
Ø ኩነኔ
ኩነኔ ማለት በአጭር ቃል ሥጋን ለነፍስ ማስገዛት ማለት ነው፡፡ ከዚህ አስቀድሞ በቅዱሳን የተጋድሎ ሕይወት እንደተመለከትነው የቅዱሳን ሕይወት በተጋድሎ (በጦርነት የተሞላ ነው ለዚህ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ) “ ጢሞቲዎስ ልጄ ሆይ አስቀድሞ ስለአንተ እንደተነገረው ትንቢት በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትዕዛዝ  አደራ እሰጥሃለሁ ” ያለው 1ኛ ጢሞ 2÷18 ስለዚህ ከሚፈፅሙት ተጋድሎ አንዱ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው ለማስገዛት የሚያደርጉት ትግል ነው፡፡ ገዚህ ተግድሎም ፈቃደ ሥጋቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማስገዛት የበቁት “ ለመዓረገ ኩነኔ ” በቁ ይባላል፡፤ ሥጋ ለነፍስ ተገዛ ማለትም እንስሳዊ ባህርያቸው ፍፁም ደክሞ መልአካዊ ባህርያቸው ሰልጥኖ ይታያል በገላትያ መልእክት ላይ እንደተጠቀሰው ሙሉ ለሙሉ የሥጋ ፍሬ ጠፍቶላቸው በአንፃሩ የመንፈስ ፍሬ የሚያፈሩበት ነው ገላ 5÷16 እንደዚሁም በዚህ ዓለም ለሥጋዊ ደማዊ ፍጥረት  ሁሉ መስራት ይችላሉ ሰው ሳሉ መልአካዊ ሆነዋልና፡፡ ይህም በትንሽ ምግብ (ለምሳሌ በቅጠላ ቅጠል ብቻ) ለብዙ ጊዜ መኖር ከእንቅልፍ መጥፋት የተነሳ በትጋሃ ሌሊት ማደር በየቀኑ ብዙ ሺህ ስግደት መስገድ ከስግደትና ከጸሎት ውጪ በሚሆኑባት ሰዓትም ከቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ አለመለየትን የመሰሉትን ነገሮች የሚያካታት ነው፡፡ ለምሳሌ በቅዱሳን ዜና ህይወት እንደተጠቀሰው አባ ብሶይ የተባለ አባት የእንቅልፍን ጾር ለማጥፋት ሌሊት ሲጸልይ ፀጉሩን ከዛፍ ላይ ያስር ነበር ኢትዮጵያውን አባ ተክለሃይማኖት 8 ጦር እናት ክርስቶስ ሰምራ 12 ጦር በጎናቸው ተክለው (አድርገው) ይጸልዩ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ እዚህ ማእረግ የደረሱት ፈቃደ ሥጋ ጠቅላላ ስለጠፋ የሚዋጉት ከሰይጣን ጋር ብቻ ነው፡፡
Ø ፍቅር
ፍቅር ማለት እግዚአብሔር ከመፍጠር ያልናቀውን ፍጥረት ሁሉንም አስተካክሎ መውደድ ማለት ነው፡፡ ኃጥእና ጻድቅ አማኒና መናፍቅ ሴት ወንድ ቀይ ጥቁር ረጅም አጭር እንዲሁም ወዳጅና ጠላት ብሎ መለየት ሳይኖር ማንኛውንም ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል በክብር የተፈጠረ ስለሆነ ብቻ መውደድ ነው የሚወዱትን ብቻ መውደድ ክርስቲያናዊ ፍቅር አይደለም ምክንያቱም በቅዱስ ወንጌል “ …. በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሙአችሁንም መርቁ  ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና በጻድቃንና በኃጥዓንም ላይ ዝናብን ያዘንባልና፡፡ የሚወድአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችንስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ” ተብሎ ተጽፎአልና ማቴ 5÷45-47 ስለዚህም በእውነተኛ ፍቅር ጌታችንን የመሰሉት ብዙዎች ናቸው፡፡ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ “ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ” ብሎ ለአብነት ስለፀለየ ቅቡ ቅዱሳንም የጌታችንን ፍኖት (መንገድ) በመከተል ስለሚያሰቃዩአቸው ሰዎች ምህረትን ይለምናሉ፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ለሚወግሩት ሰዎች “ ጌታዬ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው ” ነው ያለው፡፡ የሐ.ስራ 7÷60 ሌሎችም ቅዱሳን ሁሉ ይህንን ተግባር በመፈፀም ፈጣሪያቸውን የሚመስሉበት መዓረግ ነው፡፡
Ø ሑሰት
ሑሰት ማለት ካሉበት ቦታ ሆኖ ካሰቡበት መድረስ ነው፡፡ እንደ እግረ ፀሐይ ማለት ነው፡፡ ፀሐይ ካለችበት ቦታ ሆና ወደምድር ሳትወርድ ብርሃኗን በመላክ ከምድር ትደርሳለች እንዲሁም ቅዱሳንም እዚህ ደረጃ ላይ ሲደርሱ ካሉበት ቦታ ሆነው ካሰቡት ቦታ ይደርሳሉ በሌላው ቦታ የሚሰራውን ያውቃሉ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤልሳዕ በኢየሩሳሌም ሆኖ የሶርያው ንጉስ ወልደ አጼር እልፍኙን ዘግቶ ከባለሟሎቹ ጋር የመከረውን ምክር ምንም ሰው ሳይነግረው ያውቅበት ነበር፡፡ 2ነገ 6÷8-12 እንዲሁ አገልጋዩ ንእማን በስውር የሰራውን አውቆበታል 2ነገ 5÷1-23 በነቢዩ ኤልያስም ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በደመና ተጭኖ ይሄድ ነበር፡፡ 1ነገ 18÷12 በአዲስ ኪዳንም ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለቱ ባልና ሚስት ሐናንያና ሰጲራ የመከሩትን ምክር በማወቅ ቀጥቷቸዋል የሐ.ስራ 5÷12 ላይ ተመልከት አባ ጴሜን የተባለ አባት የሰዎችን ልብ ያውቅ ነበር የተሰጣቸውን ጸጋ ያለባቸውን ጾር ሁሉ ያውቅ ነበር፡፡ የባህረ ሀሳብ ቀማሪው አባ ድሜጥሮስ ለንስሐ ለቁርባን የበቁትን ያልበቁትን ኃጢያታቸው ተገልጾለት ያውቅ ነበር፡፡ ለዚህ ነው በቁርባን ሰዓት አንተ በቅተሀል ቁረብ አንተ ግን አልበቃህም ንስሀ ግባ ይላቸው ነበር በጥቅሉ ከዚህ መዓረግ የደረሱ ቅዱሳን የሰው ሐሳብ አይሰወርባቸውም ያውቃሉ ጠፈር ሰፈረ ግድግዳ የማይገድባቸው በተዘጋ ቤት የሚገቡ ጨለማ የማያግዳቸው  የሚሆኑበት ነው፡፤ ለዚህ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ በፃፈው የመጀመሪያ መልእክቱ “ መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ” ያለው 2ቆሮ 2÷15
3.        ንጽሐ ልቡና
ከንጽሐ ነፍስ መዓረግ የደረሱትን ወደ ፍጹምነት ደረጃ ሊደርሱበት ስለሆነ ጠላት ዲያብሎስ ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ ይዋጋቸዋል፡፡ ዘንዶና እባብ አንበሳና ነብር ሌሎችንም ሰውን የሚያስደነግጡና የሚያስፈሩ አራዊትን እየተመሰለ ለማስፈራራት ቢሞክርም ያልደነገጡትን ሰይጣን ራሱ በገሀድ ሽፍታ ወታደር እየመሰለ እየመጣ ይደበድባቸዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ እንደፃፈው “ በሰማይ የምታድሩ ሆይ እልል በሉ (ንጽሐ ልቡና የደረሳችሁ) ለምድርና ለባህር ግን ወዮላቸው ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ” ራዕይ 12÷2 ምስጢሩ ምድርና ባህር የተባሉ በንጽሐ ሥጋና በንጽሐ ነፍስ ያሉትን ነው፡፡ ይህን ሁሉ መከራ በጽናት በእግዚአብሔር እርዳታ በርትቶ የተጋፈጠና ያሸነፈ ወደ ፍፁምነት ይደርሳል፡፡ “ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያድናችሁማል ያበረታችሁማል”  ተብሎ  ተጽፏልና፡፡ 1ኛ ጴጥ 5÷10  በመዝሙር  ዳዊት  ላይም “ የፃድቃንም መከራቸው ብዙ ነው እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል ” እንዲል መዝ 33÷19  ንጽሐ ልቡና ልቡናን ከኃጥያት በማንባት (ከሐልዮ ኃጢያት በመንጻት) የሚገኝ ማዕረግ ነው በዚህም ቅዱሳን እንደ መላእክት የሚሆኑበት በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩበት ፍጹም የሚሆኑበት ደረጃ ነው፡፤ በንጽሐ ልቡና የሚገኙት ሶስቱ መዓረጋት የሚከተሉት ናቸው፡፡
Ø ንጻሬ መላእክት
ንጻሬ መላእክት ማለት መላእክትን መመልከት ማለት ነው፡፡ ለዚህ መዓረግ ሲበቁ ቅዱሳን በዓፀደ ሥጋ ሆነው መላእክትን በየከተማቸው በየቦታቸው ያያሉ፡፡ በሶስቱ አለመ መላእክት በኢዮር በራማ በኤረር ያሉ ቅዱሳን መላእክትን በየነገዳቸውና በየአለቃቸው እንዲሁም  በየክፍለ ቦታቸው ሆነው “ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪአቸውን ሲያመሰግኑ ያያሉ፡፡ ይህንን ከማለታቸው የተነሳ ሥጋዊ አኗኗር እየተረሳቸው ስለሚሄድ በዚህ ዓለም እያሉ ከዚህም ዓለም የሚደረገውን ድርጊትና ውጣ ያለውን ውጣ ውረድ ይዘነጉታል ምክንያቱም ኑሯቸው ከሰማያውያን መላእክት ጋር ስለሆነ ነው፡፡ የመላእክትን ምሥጋና ለረጅም ጊዜ ሲያዩ ኖረው ወደ ቀደመ ህልውናቸው ሲመለሱ መላክእት  በየነገዳቸው ሆነው የሚቀርቡበትን ምሥጋናቸውንና ዝማሬአቸውን ማየቱንና መስማቱ ስለማይጠገባቸው አንድ አፍታም አይተው የመጡ አይመስላቸውም፡፡
Ø ተሰጥሞ ብርሃን
ተሰጥሞ ብርሃን ማለት በብርሃን ባህር ውስጥ መስጠም (መዋኘት) ማለት ነው፡፡ ይህም ብርሃን ፍፁም  ልዩ ነው፡፡ ይህ እነርሱ በዚህ ብርሃን ውስጥ እያሉ ሌላ ለዚህ መዓረግ ያልበቃ ሊያየው የማይቻለው ብርሃን ነው፡፡ ጨለማ የማይሰለጥንበት እንደዚህ ዓለም ብርሃን ዋዕይ የሌለው (የማያቃጠል) በጨረሩ ይህንን የማይበዘብዝ ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚያስችል ደስታ እስከሚሰማ ድረስ ልዩ መዓዛና ጣዕም ያለው ነው፡፡ እነዚህን ፀጋዎች የሚያውቁ የኖሩባቸው ቅዱሳን ናቸው እኛ ደግሞ ከመጻሕፍት ብቻ እንረዳቸዋለን፡፡ ይህም እግዚአብሔር ቅዱስ ጳውሎስን የጠራበትን መብረቅና የነገሩበትን ድምፅ ይመስላል፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ በስተቀር ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት ሁሉ የመብረቁን ብልጭታውን አላዩም ነጎድጓዱንም አልሰሙም፡፡ ሰዎች የሰሙት የጳውሎስን (የሳውልን) ድምፅ ብቻ ስለ ነበር ማንን ይናገራል እያሉ ግራ ተጋብተው እንደነበር ተጽፋል፡፡ የሐዋ.ሥ 9፥1-8
Ø ከዊነ እሳት
ከዊነ እሳት ማለት እሳት መሆን ማለት ሲሆን ይህም የመጨረሻው ማዕረግ ነው፡፡ ቅዱሳን ከዚህ ደረጃ ላይ ሲደርሱ ሰውነታቸው ለአጋንንት የሚያቃጥልና የሚያስቀርብ ይሆናል ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ እዚህ መዓርግ በመድረሱ ተህዋስንን ከሰውነቱ ሲያርፍ እሳት እንደገባ ጅማት እየተኮማተሩና እያረሩ ሲወድቁ ቅዱስ ኤፍሬም ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ማዕርግ የደረሱ ቅዱሳን ለነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ ይበሉ ስላሴን ያያሉ የጌትነቱ ብርሃን በህሊናቸው ይገለጽላቸዋል “ብፁዓን ንፁሐነ ልብ እስመ እውንቱ ይሬእይዎ ለእግዚሐብሔር ልበ ንፁሀን ብፁዓን ናቸው እግዚሐብሔርን ያዮታልና” ማቴ 5፥8 እግዚአብሔርን ከማየት የበለጠ ፀጋ ስለሌለ ከዚህ በኋላ ሌላ ፀጋና ክብር አይሹም፡፡ ምክንያቱም በባህሪይው የማይታይ እግዚአብሔርን ለባህሪያቸው በሚስማማ መልኩ እስከማየት በቅተዋልና ዮሐ1፥18 አባ ህርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ ምን አለ? “መንፈስ (ልቡናን) ንፁህ በማድረግ ነቢያት እግዚአብሔርን አይተውታልና” ቅዳ.ማርያም እንዲል ነቢያት እግዚሐብሔር በ1 እንድነቱና በሶስትነቱ ሲሰለስ ሲቀደስ አይተውታል ት.ኢሳ 6፥1 ላይ እንመልከት በአዲስ ኪዳንም ቅዱስ እስጢፋኖስ ለዚህ መዓረግ እንደበቃና ስላሴን እንደተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ የሐ.ሥራ 7፥55-57 እንዲሁም ስለዚህ ቅዱስ ሰው በዚሁ መጽሐፍ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልዕክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዮት” ይላል የሐ.ሥራ 6፥15
ከንፁህ ልቡና የደረሱ ቅዱሳን ሥጋዊ አኗኗርና አስተሳሰብ ፈጽሞ ይረሳቸዋል ይጠፋቸው ከዚህ ዓለም ነገር ፈጽመው የተለዮ ናቸው፡፡ የስላሴን ምስጢር ሲያደንቁ በረቂቅ ብርሃን ሲመላለሱ እንዲሁም የመላእክትን ምሥጋና ሲያዩ የሚኖሩ እንዴት የዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ማስቢያ ጊዜና ህሊና ይኖራቸዋል? የፀሐይን ብርሃን ያገኘ ሰው የጧፍ ወይንም የሻማ መብራት አይፈልግም፡፡ እነሱም የፀጋ ሁሉ መገኛና የማይጠፋ ብርሃን ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ደርሰዋልና በዚህ ዓለም ያለውን ነገር ማሰብ ጊዜና አእምሮ ፍላጎትም የላቸውም ለዚህ ዓለም አኗኗር ሞተዋልና ህይወታቸውም ከእግዚአብሔር ፀጋ እንኳንስ ምግባር ሰርቶ ከፀጋ ወገን አንዱን ላልቀመሰ ይቅርና ፀጋውን ይዘውት ላሉት ለራሳቸው ለቅዱሳንም ቢሆን በአንደበት አከናውኖ ለመናገር የሚያስቸግር እጹብ ድንቅ ነው፡፡ “ የእግዚአብሔር ባለ ደግነትና ጥበቡ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው!” ሮሜ 11፥23, 1 ቆ 2፥3-5 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳንን ለዚህ መዓርግ ፀጋ ያበቃ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
ምዕራፍ ሦስት
የቅዱሳን ቃል ኪዳን
3.1 ቃልኪዳን
     እግዚአብሔር ለቅዱሳን ፍጹም የሆነ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” መዝ 88፤3 በማለት እንደተናገረ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ያደረጋቸው ቃልኪዳኖች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህንም ቃል ኪዳናት እስከመጨረሻው ይጠብቅላቸዋል፡፡ “አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ ለሚወዱህና ትዕዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንህንና ምህረትህን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ” ነህ 1፤5 እንዲሁም በዘዳግም ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ አምላክ እንደሆነ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃልኪዳኑንና ምህረቱን እስከ ሺ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደሆነ እወቅ” ዘዳ 7፤9 በተጨማሪም በመጽሐፈ ነገስት ላይ ያለውን ተመልከት 1ነገ 8፤23 እነዚህ ጥቅሶች የሚያስረዱት ይህንን ነው፡፡ ለምሳሌ ከጥፋት ውሃ በኋላ እግዚአብሔር ኖህን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት” ዘፍ9፤1 አለው፡፡ ኖህ ግን “ብንበዛ ምን ዋጋ አለው ሰው ከማጥፋት ላያርፍ አንተም ከመቅጣት ላታርፍ ” ሲል መለሰ፡፡ በዚህ ጊዜ ነው እግዚአብሔር “እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር አቆማለሁ ከእናንት ጋርም ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፡፡ ከእናንተ ከመርከብ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች ለእንስሳትም ለምድር አራዊትም ሁሉ ይሆናል” ያለው በዚህ ለኖህ አምላክ በሰጠው የሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን እንስሳትም አራዊትም አዕዋፍም ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከዚህም የምንረዳው እግዚአብሔር በቅዱሳን ቃል ኪዳን እንደሚጠብቀን ነው፡፡
     ኢየሩሳሌም በአሶር ንጉስ በሰናክሬም ሠራዊት በተከበበች ጊዜ እግዚአብሔር ለቅዱስ ዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን አስቦ “እግዚአብሔር ስለ እኔም ስለባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ” ያለው በዚህም “የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ ከአሶርም ሰፈር መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ገደለ ማለዳም በተነሱ ጊዜ እነሆ ሁሉ በድኖች ነበሩ” ኢሳ 37፤33-36 ንጉስ ዳዊትም በዘመኑ ስለተሰጠው ቃል ኪዳን ሲገልጽ “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ… ከእኔም ጋር በሁሉ ነገር ቅንና ጽኑ የሆነውን የዘለአለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፡፡” ብሏል፡፡ 2 ሳሙ 23፤1-5 የዘላለም በማለትም በቅዱሳን ቃል ኪዳን እረፍተ ዘመን (የዘመን ግድግዳ) የማይገታው ዘለዓለማዊ መሆኑን የተናገረው ስለዚህም ነው “መታሰቢያችሁን የሚያደርገውን ቤተክርስቲያን የሚያድነውን በስማችሁ እንዲሁ ለተራቆተ የሚያለብሰውን የታመመ የሚጎበኘውን የተራበ የሚያበላውን የተጠማ የሚያጠጣውን ያዘነ የሚያረጋጋውን መመስገኛችሁን የፃፈውን ያፃፈውን ያነበበውን የስማውን ልጆቹን በስማችሁ የሰየመውን በበዓለ ንግሳችሁ ዝማሬ ያቀረበውን እምርላችኋለሁ፡፡ ” እንዳለ በየጊዜው የተነሱትን ቅዱሳን ቃል የሚገባላቸው፡፡
3.2 የቅዱሳን ክብር
     የቅዱሳን ክብር ከእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት “ነፍሴ (ሰውነቴ) በእግዚአብሔር ትከብራከች” መዝ 33፤2 ያለው በዚህ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ልጁ (በተዋህዶ አንድ አካል አንድ ባህርይ የሆነው ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ) በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ (ለቅዱሳን ሁሉ ለበጎ ነገር በኩር አብነት ይሆናቸው ዘንድ) አስቀድሞ ያውቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው ብሏል ሮሜ 8፤29-30 በመሆኑም የቅዱሳን ሁለንተናቸው የከበረ ነው፡፡
1.    ስማቸው
    የቅዱሳን ስም እንደማንኛውም ሰው ስም ተርታ አይደለም፡፡ የተለየ ክብርና ኃይል አለው፡፡ እግዚአብሔር አብርሀምን “ስምህንም አከብረዋለሁ” ያለው ለዚህ ነው ዘፍ 12፤12 ስለዚህ የቅዱሳንን ስም በክብር መጥራት ያስፈልጋል፡፡  በጣም የሚገርመው እንኳን እኛ የክብር ሁሉ ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔር “ሙሴ ሙሴ ሆይ” እያለ የቅዱሳኑን ስም በክብር ጠርቶታል “ሆይ” ማለት ቃለ አክብሮ ነውና፡፡ ይህም እርሱ አክብሮ አክብሩ ሲለን ነው፡፡
     የቅዱሳን ስም የከበረ በመሆኑ እግዚአብሔርን የምንማፀንበት ታላቅ መሳሪያ ነው ነቢዩ ኤልያስ የጣዖት ሀሰተኛነት የእግዘአብሔር እውነተኛነት እንዲገለጥ መስዋዕ ሰውቶ የተማፀነው በቅዱሳን ስም ነው፡፡ “አቤቱ የአብርሀምና የይስሀቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደሆንህ እኔም ባሪያህ እንደሆንሁ ይህንንም ሁሉ በቃልህ እንዳደረግሁ ዛሬ ይገለጥ” ነው ያለው፡፡ 1ኛ ነገ 8፤33 እግዚአብሔርም ወዳጁ ኤልያስ በወዳጆቹ በቅዱሳን ስም ያቀረበውን ልመና ተቀብሎ ፈፅሞለታል፡፡ በመሆኑም ጠበላት በስማቸው የሚጠሩ መካናት በስማቸው የሚፈልቁ ጠበላት በስማቸው የተሳሉ ስዕላት ሁሉ ክብርም ኃይልም አላቸው፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳን በመንፈስ (በረድኤት) ከእነዚህ ሁሉ ጋር አሉና፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ ምንም እንኳ በስጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ” ያለው ለዚህ ነው 1ኛቆሮ 5፤3-4 በቆላስያስ መልእክቱም “በሥጋ ምንም እንኳን ብርቅ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል” ብሏል፡፡ ቆላ 2፤5
      ስለዚህ የቅዱሳን የሆነ በቅዱሳን ስም የተጠራ ሁሉ ልዩ እንደሆነ ማስተዋል ይገባል፡፡ ለምሳሌ የማንኛውም ሰው ጥላና የቅዱሳን ጥላ አንድ አይደለም፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ለማስተማር ወደ አንድ ከተማ በሚገባበት ጊዜ ጥላው እንዲያርፍባቸው ህመምተኞችን ጧት ጧት በምዕራብ አቅጣጫ ከሰዓት ሲሆን ደግ በምስራቅ ያስቀኙአቸው ነበር፡፡ ታዲያ ጥላው ያረፈባቸው ሁሉ ይፈወሱ ነበር፡፡ የሐዋ 5፤15-16 ከዚህም ሌላ የቅዱሳን ልብስ የማንኛውም ሰውልብስ አንድ አይደለም ምክንያቱም ቅዱሳን ሲበቁ የነፍሳቸው ቅድስና ለስጋቸው  የስጋቸው ቅድስና ደግሞ ለጥምጣማቸው የጥምጥማቸ ለመጎናፀፊያቸው  ለቀምሳቸው ለምረከዛቸው ይተርፋልእና የነቢያት አለቃ ሙሴ እግዚአብሄር በአዘዘው መሰረት በያዘው በትር የኤርትራን ባህር ቢመታው  ለሁለት ተከፍሎለታል ዘጸ14፤21 የሌላሰው በትር ቢሆን ኖሮ ውሀው ‹‹እንቦጭ›› ይላል እንጂ የሚያመጣው ለውጥየለም ነብዩ እልያስም መጎናፀፍያውን ጠቅልሎ የዮርድያኖስን ወንዝ  ቢመታ ለሁለት ተከፍሎለታል 2ነገ 2፤8 የሌላሰው መጎናፅፍያ ብሆን ኖሮ በውሃ ይርሳል እንጂ የሚያመጣው  ለውጥ የለም  ባአዲስ ኪዳንም የታላቁ ሀዋርያ የቅዱስ ጳሎውስ የልብስ ቁራጭ አጋንንትን ያስወጣ በሽተኞችን ያፈውስ ነበር ‹‹እግዚኤብሄር በጳውሎስም እጅ የሚያስገርም ታምራትን ያደርግ ነበር  ስለዚህ ካአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውያን ይወስድ ነበር ድውያመኑም ይፈወሱ ነበር ክፍዎች መናፍስትም  ይወጡ ነበር በማለትም ወንጌላዊው ቅድስ ሉቃስ ፅፎለታል ሐዋ19፤11-12 ከዚህም ሁሉ የምንማረው የቅዱሳን የሆነው ሁሉ  ፈዋሽ መሆኑን ነው፡፡
    2 ሥዕላቸው
የቅዱሳን ስዕላች እናደማንኛውም ሰው ፎቶ አይደለም የሰው ፎቶ ከማስተዋሻነት ያለፈ አይደለም የቅድሳን ሥዕል  ግን ከዚህ በላይነው በረከታቸው እና እረዴታቸውን የሚያስተላልፍ መሳርያነው ከላይ እነደተጠቀሰው ነው በቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ በቅድስ ጳውሎስ የአካሉ ጨርቅ(ልብስ) ብዙ ታምራት እንደተደረገ እንደዚ የቅዱሳን የሆነ ሁሉ በረከት አለውና የቅዱሳንን ሥዕል የሚገባውን ክብር መሥጠት ይገባል፡፡ በመሆኑም በቅዱስ ሥዕላት ዐንቀፅ ጨ ይቻላል
 3 ዐጽማቻው
ቅዱሳን በዚህ ዓለም በሞት ከተለዮ በኋላ ዐጽማቸው በክብር ማሳረፍ ይገባል እንዱሁም እስከመጨረሻ ክብር መስጠት ይገባል ያእቆብ ልጆችን ከባረካቸው በኋላ‹‹ እኔ ወደወገኖቼ እሰበስባለው በኬታውዊ  በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶች ጋር ቅበሩኝ ያለው ለዚህ ነው ዘፍ 49.29 ልጅ ዮስፍም ወንድሞቹን እኔ እሞታለሁ እግዚአብሄር መጎብኘትን የጎበኛችሆል ከዚህም ምድር ያወጣችሆል ለአብርሀም እና ለይስሀቅ ለያእቆብም ልጅ ሞላላቸው ምድርም ያደርሳቹሀል እግዚአብሔር ሳያስባቹ ከእናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ አማላቸው ‹‹የሚለውም ምን የሚያመለክተን የቅዱሳን አፅም ክብር እንዳለው ነው ዘፍ 50.24-25፤1ኛ ነገ 13፡31
በመቃብር በክብር የሚያርፍ የቅዱሳን አፅም ቅዱስ ስለሆነ ተአምራት ሲያደርግ የኖራል ለዚህም ምስክሩ የነቢዩ ኤልሳዕ አጽሙ ነው ፡፡ ‹‹ ኤለሳዕ ሞተ ቀበሩትም ከሞአብም አደጋ ጣዮችም በየአመቱ ወደ ሀገሩ ያገቡ ነበር ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮች አዩ እሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ላይ ጣሉት የኤልሳንም አጥንት በነካ ጊዜ ድኖ በእግሩ ቆመ›› 2ኛ ነገ 13.20 ይህም የቅዱሳን አማላጅነት በአፀደ ነፍስም የሚቀጥል መሆኑን የሚያመለክት ነው
4. ስግደት
ስግደት ሁለት አይነት ነው
     1ኛ የባህሪ ስግደት
    2ኛ የጸጋ ስግደት
የባህሪ ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ ነው ምክንያቱም ክብር የባህሪው ነውና የጸጋ ስግደት የሚባለው ለቅዱሳን የሚቀርብ ነው ምክንያቱም በጸጋ እግዚአብሕር የሚያገኙት ነውና ለክዱሳን ስግደት እነደሚገባ ምስክሩ መፅሀፍ ቅዱስ ነው የንጉሱ አክአብ ባለሞል አብድዮ ‹‹ ጌታዬ›› እያለ ለነቢዩ ለኤልያስ ሰግዶል 1ኛ ነገ 18፡7 ንጉሱ አካዝያስ በመጨረሻ 50 ወታደሮች ጋር የላከው  የ50 አለቃ በኤልያስ ፊት እየሰገደ ‹‹ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ነፍሴና የእነዚህ የ 50 ባሪያዎችህ ነፍስ በፊትህ የከበረች ትሁን›› ብሎል ለነብዩ በመስገዱና የሚገባውን ክብር በመስጠቱ ልመናው ተሰምቶ እንደቀደሙት ከሰማይ በወረደ እሳት አልሞተም የወታደሮቹ ህይወት አድኖል 2ኛ ነገ 1፡13 የኢያሪኮ ሰዎችም ለነቢዩ ኤልሳዕ በግንባራቸው ተደፍተው ሰግደውለታል 2ኛ ነገ 4፡27-37 ሱናማዊቶም ስት በችግሮም በደስታዋም ጊዜ ሰግዳለታለች፡፡ 2ኛ ነገ 4፡27-37 በአዲስ ኪዳንም የወኅኒ ቤት ጠባቂ ለቅዱስ ጳውሎስና ለሲላስ እየተንቀጠቀጠ በግንባሩ ተደፍቶ ሰግዶላቸዋል፡፡ የሐ ስራ 16፡29
3.3 የቅዱሳን መታሰቢያ
 ቅዱሳን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከቤቱ ጀምሮ በጽላቱ፡በጸበሉ ይታሰባሉ፡፡ ቤቱ ጽላቱ ጸበሉ የእግዚአብሕር ሲሆን የጻድቁ የተክለ ሀይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጽላት ጸበል ይባላል፡፡በዚህ ሁሉ ስማቸው እየተጠራ እንዲታሰቡ ያደረገ እግዚአብሕር ነው፡፡ ለቢዩ ኢሳይያስ እንደተናገረው ‹‹ በቤቴ እና በቅጽሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣችሆለሁ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣችሆለሁ፡፡ ‹‹በማለት(ኢሳ 56፡5) በብሉይ ኪዳን በኢሳይያስ አንደበት የተናገረ እግዚአብሄር በአዲስ ኪዳንም ባለ ሽቶዋ ማርያም ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቶ በራሱ ላይ ባፈሰሰች ጊዜ‹‹ይህች ሴት መልካም ስራ ሰርታልኛለች …. እርሶ ይህን ሽቶ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገችው፡፡ እውነት እላችሆለሁ ይህ ወንጌል በአለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበኩበት እርሶ ያደረገችው ደግሞ ለእርሶ መታሰቢያ እንዲሆን የነገራል፡፡››ብሎል፡፡ማቲ 26፡7-13 ይህም የሚያስተምረው በስብከተ ወንጌል ውስጥ የቅዱሳን መታሰቢያ መኖሩ ነው፡፡ ስለሆነም ደማቸውን ያፈሰሱ ቅዱሳን ምን ያህል መታሰብ አለባቸው; የሚለውን በንጹህ ልቦና ማሰብ ይገባል ቅዱስ ጳውሎስ በአብራውያን መልእክቱ ከአቤል ጀምሮ ያሉትን ቅዱሳን በስማቸው እየጠራ ታሪካቸውን እየተረከ በማሰብ የስብከቱ አስኮል አድርጎቸዋል                                       
ምዕራፍ አራት
የቅዱሳን አማላጅነት

4.1 አማላጅነት፡-በግእዝ uu ተንበለ ለመነ አማለደ ከሚለው ግስ ተንበለ የሚለምን የሚጸልይ ማላጅ አማላጅ አቆላማጭ የሚል የግብር ስም ይወጣል፤፤ ስለዚህ አማላጅ ማለት በሁለት አካላት መካከል ገብቶ አንዱን ስለ ሌላው የሚለምን ማለት ነው፡፡
4.2 በምልጃ ወቅት የሚሳተፉ አካላት
    በምልጃ ወቅት የተለያ እኔ ባይ አካላት እንዳሉ ለመረዳት የሚያዳግት አየደለም ምክንያቱም ምልጃ አንዱ ስለ ሌላው የሚያቀርበው ልመና ነውና የሚለምን፣የሚለመንለት  የሚለመን ሶስት አካላት ይሳተፋሉ፡፡
 ሀ/ ተማላጅ የሚለመነው ይህ አካል የመፍረድ ስልጣን ያለው የፈቀደውን ያደርግ ዘንድ የሚቻለው አካል ነው፡፡ በነገረ ደህነት ለሚፈጸመው ምልጃ ተለማኙ እግዚአብሄር ብቻ ነው በሀይማኖት ትምህርት የጸሎት ሁሉ መድረሻ እግዚአብሄር ነው ተማላጁ እግዚአብሄር እነደ አማላጆች ብዙ አይደለም አንድ ነው አንድ እግዚአብሔር ስንልም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ ሶስቱ አካላት በአንድ ጌትነት በአንድ ስልጣን በአንድ ክብር በአንድ መለኮት በአንድ ፈቃድ በሰማይና በምድር የሚገኙ ፍጥረታትን ልመና  ተቀብለው የፈቃዳቸውንና የቸርነታቸውን ስራ ይሰራሉ፡፡
ለ/ አማላጅ/የሚለምነው ይህ ደግሞ ከተለማኙ ጋር በቅርብ የሚተዋወቅ እውነቱን ለማስረዳት የበቃ ይቅርታ ሊያሰጥ የታመነ ይልቁንም ከተለማኙ ባለሞልነትን ያገኘ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት ይህን ስራ የሚሰሩት በባህሪያቸው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሄር በጸጋ የከበሩ ቅዱሳን ናቸው፡፡ማማለድ ለፍጡራን የማስማሚያ የትህትና ስራ ነው፡፡ በመሆኑም ሁል ጊዜ ስለሀጣን እግዚአብሔር ፊት  ለምናሉ የሚማልዱለት ራሳቸውን/ህይወታቸውን/ ለሀጣን አሳልፈው እስከ መስጠት ድረስ ነው፡፡ ‹‹ሙሴም ወደ እግዚአብሄር ተመልሶ ወደ እነዚህ ህዝብ ታላቅ ሀጢያት ሰርተዋል ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት አድርገዋል አሁን ይህን ሀጢያታቸው ይቅር በላቸው አለዚያ ግን ከጻፍከው መጽሀፍ እባክህ ደምስሰኝ አለ››፡፡ ዘፍ 32፤31-32 እግዚአብሄር ስለ ሙሴ ልመና ለራሳቸውም ‹‹----እግዚአብሔር በህዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰሰበው ክፋት (ጥፋት) ራራ››፡፡ ዘፍ 32፤9-14 ይህንን ቅዱስ ዳዊት ‹‹እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሰፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ››በማለት ጠቅሳ  መዝ 105፤23 በአዲስ ኪዳንም ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑ ስለ ወንድሞቼ መዶቼ ስለሆኑ በሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ የተረገምሁ እንደሆን እጸልይ ነበርና ብላል››፡፡ሮሜ 91-3
    ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኙ የእግዚአብሔር ወዳጆች ባለሞሎች በመሆናቸው ልመናቸው ጸሎታቸው ተቀባይነት አለው፡፡አበ ብዙሀን አብርሀም ‹‹አቤቱ በፈሐትህ ሞገስን አግንቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ››በማለት ሥላሴን ለምኖ ተፈጽሞለታል፡፡ ዘፍ 18፤3 ነቢዩ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ስለነበረው ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር 1ኛ ሳሙ 2፤26 እና 3፤1-21
ሐ/ የሚማለድለት/የሚለመንለት ይህ ሶስተኛው አካል ሲሆን መበደሉንና ኀጢያት ማድረጉን በወቅቱ እግዚአብሔር ፊት በትሁት ስብና ልመናውን በማቅረብ ምልጃን የሚጠይቅ ምእመን(አማኝ) ነው፡፡እንዲሁም የሚለመንለት የራሱ የሆነ ድርሻ አለው ይኸውም በአማላጁ ጸሎት በማጁ ቸርነት አምኖ ከሚሰራው ሀጢያት በንሰሀ መመለስ አለበት ለዚህ ነው ህዝበ እስራኤል ኤርሚያስን የእግዚአብሄርን ቃል እንሰማለን አንተም አምላክህን ለምንልን ነው ያሉት ት.ኤ 42፤5-6 የሚማለድለት ሰው ለመመለስ ንሰሀ ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆነ ያማላጃችን ጸሎት በረከት አጥቶ በከንቱ የቀራል ማት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቸርነት የቅዱሳን አማላጅነት ንቆ በሀጢያቱ ሲጋፋ እግዚአብሄር ቅዱሳኑን ጸሎታቸውን እንዲያቆሙ (እንዳይለምኑ) ይነግራቸዋል ‹‹በእስራኤል ላይ እንዳይነግስ ለናቁት ለእስራኤል የምታለቅስለት እስከመቼ ነው›› 1ሳሙ 16፤1 ነብዩ ኤርሚያስንም ‹‹እንግዲህ አልሰማህም ስለዚህ ህዝብ አትጸልይ›› ኤር 7፤16-19 በተጨማሪም ‹‹ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ሊቆምም ልጄ ወደዚህ ህዝብ አያዘነብልም ከፊቴ ጣላቸው ይውጡ›› ት.ኤ 15፤7



4.3 ምልጃ ለምን አስፈለገ?
ለመሆኑ ምልጃ ለምን አስፈለገ?እግዚአብሄር ያለ ሶስተኛ ወገን ሲነግሩት ስለማይሰማ ነውን? አንዳንድ ሰዎች እኛ እግዚአብሄርን በቀጥታ ማነጋገር እንችላለን እርሱም ይሰማናል ስለዚህ ሶሰተኛ ወገን አማላጅ አያስፈልገንም ይላሉ በውኑ ምልጃ የሚሉ ወገኖች እግዚአብሄር አይሰማንም ብለው ይሆን ወይስ ስለሌላ?
ሀ/ የእግዚአብሔር ትእዛዝን ፈቃድ
 ምልጃ የእግዚአብሄር ትእዛዝ ነው ቅዱሳንም የእግዚአብሄር ስጦታዎች ናቸው ይህም ይታወቀው ዘንድ እግዚአብሄር አቤሜሌክን ወደ አብርሀም ልኮታል ‹‹አብርሀም ስለ አንተም ይጸልያል ትድናለህም›› ብሎታል ዘፍ 20፤7 የእዮብንም ወዳጆችንም ‹‹እንደ ባሪያዬ እዮብ ቅንን ነገር አልተናገራችሁምና በአንተና በሁለት ባለንን ጀሮችህ ላይ ነድዶል አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ እዬብ ዘንድ ሂዱ የሚቃጠለውንም መስዋእት ስለራሳችሁ አሳርጉ ባሪያዬን ኢዬብ ስለእናንተ ይጸልያል እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ ብሎቸዋል፡፡ ኢዩ 42፤7-8 እንግዲህ ከእነዚህ የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪኮች የምንረዳው ምልጃ ሰው የሰራው ፈጠራ ሳይሆን የእግዚአብሄር ትእዛዝና ፈቃድ መሆኑን ነው፡፡‹‹ እኛ ራሳችን በደንብ እንጸልያለንአማላጅ መፈለግ መንገድ ማብዛት ነው›› የሚሉ ሰዎች አካሄዳቸው ልብ ወለድና የድፍረት አካሄድን የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚጻረር ወይም የሚቃወምእንዲሁም መጽሀፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባል በሀዲስ ኪዳንም ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በእኛም የማስታረቅን ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሄር ስለ እኛ ስለሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን›› ብሎል 2ኛ ቆ5፤19-20 እንዲሁም በፊሊጲዩሳ መልእክቱ ‹‹ነገር ሁሉ በጸሎት እና በምልጃ ከምሥጋና ጋርእግዚአብሔርዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ አነዳች አትጨነቁ››ይላል ፊሊ 4፤6
ለ/ የእግዚአብሄር የምህረቱን ብዛት እንድናውቅ
እግዚአብሔር ከበደለ በሆላ የሚጸጸት አለ በተቃራኒም ደግሞ የማይጸልይ ልቡየሚደነድን ሰውም አለ ሰውም እንደበደለ በተሰማው ወቅት በደሉ በቆረቆረው ጊዜ እግዚአብሄርን ይለምናል ሲለምንም እግዚአብሄር እንዲምረው ነው የሚያሳስበው ከእርሱ የተሸሉትን የሚበልጡትንእግዚአብሔርፊት ባለሞልነት ያላቸውን ሰዎች በማሰብ ነው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብር ምህረት ተሰፍራ የምትለካ ስላልሆነች ደጋጎቹን ቅዱሳንን ባሰበ ጊዜ ብዙ ምህረቱ ስለሚፈስ ሀጥአንም ይቅር ይባላሉና እነ ሙሴ እነ ዳዊት ስለ እስራኤል ሲለምኑ በደጋጎቹ በኩል አድርገወ ነው ‹‹--------ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ ብለህ በራስህ የማልህላቸው ባሪያዎችህን አብርሀምና ይስሀቅን እስራኤልንም አስብ እግዚአብሔር በህዝቡ ላይ ሊያደርገው ስላሰበው ጥፋት (ክፋት) እራራ››፡፡ ዘጸ 32፤13-14 ተብሎ እንደተጻፈ ስለዚህ እኔ እበቃለሁ ነቢዩ ነኝ ሳይል የእግዚአብሄር ብዙኃ ምህረት በቅዱሳኑ መሆኑን አውቆ እነ አብርሀም ስማቸው በመጥራት አሳስብ እመብታችን ድንግል ማርያም በቅዱሳኑ በኩል ስለሚሆነው የእግዚአብሄር ምህረት ‹‹ለአባቶቻችን እንደተናገረው ለአብርሀም እና ለዘሩ ምህረቱን አስቦ እስራኤል ብላቴናውን ረድቶል›› ሉቃ 1፤55 በማለት እናታችን የእግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ መሆኑን ተናግራለች፡፡
ሐ/የእግዚአብሔር ባለሞሎች ለይተን እንድናውቅ በቃልኪዳናቸው እንድንጠቀም
እግዚአብሔር በወዳጆቹ ሁል ጊዜ ይደሰታል ስለዚህም የሚታሰቡበትን ቃል ኪዳን ይገባላቸዋል፡፡ ‹‹ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ ለባሪያም ለዳዊት ማልሁ›› መዝ 88፤3 እንዲል ከመረጣቸው ቅዱሳን ጋር እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶ መሀላም ገብቶል፡፡ ይህንን እውቀት እንድንጠቀምበት እግዚአብሔር ይፈልጋል ጠቢቡ ሰሎሞን ይህን ለዳዊት የተሰጠውን ቃል ኪዳን ማሳሰብ ‹‹-----አሁንም የእስራኤል አምላክ አብቱ አንተ በፊቴ እንደሄድህ ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው በፊቴ አታጣም ብለህ ተስፋ የሰጠኸውን ለአባት ለዳዊት ጠብቅ›› በማለት አስቦል 1ኛ ነገ 8፤25 ታዲያ እግዚአብሔር ምን አለ ስንል ‹‹ነገር ግን ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስለመረጥኁችሁ ስለ ኢየሩሳሌም አንድ ነገር እሰጣለሁ እንጂ መንግስቱን ሁሉ አልቀድም›› በማለት ለዳዊት የገባውን ቃል ጠብቆል 1ኛ ነገ 11፤13 ታዲያ ይህ ሁሉ የሆነው ጠቢቡ ሰሎሞን የቅዱስ ዳዊት ስም ስለማለደው (ስላማለደው) ነው፡፡
መ/ ስለ ትህትና
ጠህትና ራስን ዝቅ በማድረግ ራስን ታናሽ አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች ሁል ጊዜ እንኮን እግዚአብሔር ፊት በሰውም ፊት ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር ትእቢተኞችን ይቃወማል ትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣል›› 1ኛጴጥ 5፤5 ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ሰዎች መታወቅያቸው ትህትና ነው፡፡ ሮማውያን የመቶ አለቃ አብነት አርገን ብንጠቅስ ራሱን እግዚአብሄር ፊት መቆም እንደማይገባው ቆጥሮ የአይሁድን ሽማግሌዎችን ልኮ በሆላም ‹‹በቤቴ ጣሪያ በታች ልትገባ አይገባኝም››በማለቱ ተመሰገነ እንጂ አልተዋረደም ጌታችንም እንዲህ ነበር ‹‹እስራኤልስ እን£ን እንዲህ ያለ እምነት ታላቅ እምነት አላገኘሁም››ያለው ስለ ትህትናው አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ በማድረግ ያለ እኛ ጻድቅና ቅዱስ ማን አለ የሚሉ ራሳቸውን ቢመረምሩ መልካም ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ የትህትና እንጂ የትዕቢት መንፈስ አይደለምና ስለዚህ እግዚአብሄር በትህትና የሚቀርበውን ጸሎት ይቀበላልና በትሁት ስብእና ለቅዱሳን በገባው ቃል ኪዳን በኩል ብንለምነው የምንጠቀም እንጂ የምንጎዳ አይደለምና፡፡ 


4.4 የቅዱሳን አማላጅነት በህይወተ ሥጋ
      ቅዱሳን በህይወተ ሥጋ ሳሉ እግዚአብሔር ስለ እርሱ ሲል ምህረት ይቅርታን ያደርጋል ምሳሌም የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል፡፡ አብርሀም ስለ ሰዶምና ገሞራ እግዚአብሄር በነገረው ጊዜ እንዳይጠፋ ምህረትን ለምኖ ነበር ‹‹ሀምሳ ጻድቅ በከተማው ውስጥ ቢገኝ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን ከተማይቱንስ በእርg ስለሚገኙ ሀምሳ ጻድቅ አትምርምን?›› ብሎ በለመነው ጊዜ ‹‹እግዚአብሔርም በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ  ሀምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለእነርሱ እምራለሁ›› ብሎታል ነገር ግን
በሰዶምና ገሞራ ሀምሳ ቀርቶ አስር ጻድቃን ስላልተገኙ ሀገሪቱ በእሳት ተቃጥላ ጠፍታለች ንጉሱ አቤሜሌክ ከነ መላ ቤተሰቡ ከእግዚአብሄር ቁጣ የዳነው በአብርሃም ጸሎት ከአቤሜሌክ ተጠብቃለች፡፡ዘፍ2017-18 ርብቃ በይስሀቅ አማላጅነት የልጆች እናት ሆናለች፡፡ዘፍ2519-26 ልበደንዳናው ፈርኦን እን£ ሙሴንና አሮንን አማልዱ ብሎ ëሎታቸው ተጠቅሞአል የጎዳው ወደ ክፋቱ መመለሱ ነው ë 8-10 እስራኤል ከምድረበዳሲÕ የሚበሉትንና የሚጠጡትንና የሚያገኙት በሙሴ አማላጅነት ነበር ë 1522-25 ë 171-7 አማሌቅን ድል የነሱት በሙሴ አማላጅነት ነበር ë 121-5 በአጠቃላይ የነቢያት አለቃ ሙሴ ስለ ህዝቡ ባመéበት ጊዜ እግዚያብሄር ‹‹እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ››እያለ ይመልስላት ነበር 1325-33 ወይም 141-19 እስራኤል ዘሥጋ
በባቢሎናውያን ምርኮ ስራ በወደቁ ጊዜ በአማላጅነታቸው ያዳናቸው ነቢዩ ኤርሚያስ ነው እግዚአብሄር አማላጅነቱን ስለተቀበለው ‹‹ጽሎታቸውን በፊቱ አቀርብ ዘንድ የላካችሁልኘኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ስላደረጋችሁት ክፉ ነገር  ትታችልና በዚህች ምድር ብትቀመጡ እሰራችኀለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም እተክላችኀለሁ እንጂ አልነቅላችሁም ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉስ አትፍሩ አድናችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ ይላል እግዚአብሔር›› .ኤር 21-11 እንዲሁም በአዲስ ኪዳን የጠብ ግርግዳ የፈረሰበት በመሆኑ ቅዱሳን ይበልጥ ወደ እግዚአብሄር የቀረቡት ነው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጥቶዋቸዋል ‹‹እውነት እላችለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድር የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል ››ማ.ቴ 16፤19 ማ.ቴ 18፤18 የሚሳናቸው ነገር የለም ብሎቸዋል እንዲሁም የምእመናንም ህይወትም በአደራ ሰጥቶችሆል ማቴ 17፤20 ዩሀ 21፤15-17
    ቅዱስ ጴጥሮስና ዩሀንስ በዘጠኝ ለሊት ወደ ቤተ መቅደስ በሚሄዱበት ሰአት በመቀቅደስ በር ላይ ወድቆ የነበረውን አንካሳ ሰው በአማላጅነታቸው ፈውሰውት እንደ አንበሳ እየዘለለ እግዚአብሄርን አመስግኖል የሐዋ ስራ 3፤1-10 በዲያቆኑ በፊሊጶስ የአማጅነት ስልጣንም እርኩሳን መናፍስት በቃላት ድምጽ እየጮሁ ከብዙ ሰዎች ይወጡ ነበር ብዙም ሽባዎችና አንካሶች ይፈወሱ ነበር የሀዋ 8፤7 ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በየስፍራው ሁሉ በአማጅነቱ ፈውሶታል ሀዋ 9፤32 በኢየሩሳልምም ‹‹ጦቢት ሆይ ተነሽ ብሎ ጦቢትን ከሞት አስነስቶል››የሀዋ 9፤36 ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ደግሞ በልስጥላን እግሩ የሰለለ ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ አንካሳ የሆነ ከቶም መሄድ የማያውቅ ሰው አግኝቶ በታላቅ ድምጽ ‹‹ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም›› ነማለት ፈውሶታል ሀዋ 14፤8 በፊሊጲዩስስ የሞርተኝነት መንፈስ የነበረባትን ሴት በጸሎት ፈውሶታል፡፡ሀዋ 16፤16
    በወንጌል ለቅዱሳን አማላጅነት አብነት የሚሆን ትምህርት አለ የቅርናሆም አለቃ የሚወደው ባሪያው በታመመ ጊዜ አማላጅ አድርጎ የአይሁድም ሽማግሌዎች ልኮቸዋል መድሀኒታችን ክርስቶስም እምነቱንና ትህትናውን አድንቆለት ልመናውን ፈጽሞለታል ሉቃ 7፤1-10 አንድ መኮንንም የሞተችበትን ልጁን እንዲያስነሳለት በለመነ ጊዜ ልመናውን ተቀብሎ ብቱ ድረስ በመግባት እጆን ይዞ አስነስቶታል ማቴ 9፤18-25 በጨረቃ እየተነሳበት ከእሳትና ከውሀ እየወደቀ ይሰቃይ የነበረው ልጅ አባትም ስለ ልጁ በለመነ ጊዜ ልመናውን ተቀብሎ መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈውሶታል ማቴ 17፤14፤18 ከዚህም የምንማረው ለኛም ቅዱሳን መንፈሳውያን አባቶቻችን በምድርም ሆነ በሰማይ በሚለምኑልን ጊዜ ሁሉ ነገር እንደሚደረግልን ነው፡፡
4.5  የቅዱሳን አማላጅነት ዐጸደ ነፍስ
   የቅዱሳን አማላጅነት በዐጸደ ሥጋ ምን እነደሚመስል ከብሉም ከሀዲስ ኪዳን እየጠቀስን ተመልክተናል በዚህ  ደግሞ ቅዱሳን ከዚህ አለም በሞተ ሥጋ ከተለዩ በሆላ በአጸደ ነፍስ ሆነው እንዴት እንደሚማልዱ ነው፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ በዚህ አለም የአማላጅነትን ሆነ ማናቸውም መንፈሳዊ ስራ ሲፈጽሙ የነበሩ ቅዱሳን ከሞቱ በሆላም ይህ ስራቸው እንደሚከተለው ይነግረናል ይህንን በተመለከተ በዩሀንስ ራእይ ‹‹ከሰማዕትም ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብጹአን ናቸው፡፡ መንፈስ ፡-አዎን ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ስራቸው ከተለቸዋል ይላል፡፡ብለህ ጻፍ የሚል ድምጽ ሰማሁ››፡፡ የሚል ይገኛል ረእይ 14፤13 ለዚህም ነው በአጸደ ሥጋ በነበረ ጊዜ ሙት ይነሳል ኤልሳስ ከሞተ በሆላ በአጸደ ነፍስ ሆኖ በመቃብር በሚገኝ አጽሙ ሙት ያስነሳው 2ነገ 13፤20 በምድር ባለ ድንኮን እንግዳ ይቀበል የነበረ አብርሀም በሰማይ ድንኮን ሆኖ አላዛርን በእንግድነት ተቀብሎታል ሉቃ16፤22
   ቅዱሳን በአጸደ ነፍስም ሆነው እንደሚለምኑና እንደሚጸልዩ ‹‹አምስተኛውንም ማህተም በፈታ ጊዜ ስለ እግዚአብሄር ቃልና ስለጠበቁት ምስክር የታረዱትን ሰዎች ነፍሳት ከመሰዊው በታች አየሁ፡፡በታላቅ ድምጽም እየጮሁ ቅዱስ እና እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከመቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከመቼ አትበቀልም አሉ፡፡ ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው እንደእነሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው ባሪያዎች ባልንጀሮቻቸውና ወንድሞቻቸው ቁጥር እስኪፈጸም ድረስ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው፡፡››የሚለው ታላቅ ምስክር ነው፡፡ ራዕይ 6፤9-11 ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሁለተኛ መልእክቱ ‹‹ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተ ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑም ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም፡፡ሁል ጊዜ በዚህ ማደሪያዬ ሳለሁ (በህይወተ ሥጋ)በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንደሚሆን አውቃለሁና ከመውጣቴም በሆላ (በአጸደ ነፍስ)እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ (እጸልያለሁ እለምናለሁ)፡፡››2ኛጴ 1፤13-15 ብሎል በመጽሀፈ ሄኖክም ‹‹በሰማይ የሚኖሩ ጻድቃን በአንድ ቃል ሆነው ተባብረው ያመሰግናሉ ለሰውም ፈጽመው ይለምናሉ››ሲል በአጸደ ነፍስ ያሉ ጻድቃን በዚህ ምድር ላሉ እንደሚጸልዩ ተናግረዋል፡፡ ሄኖክ 1፤9 ከዚህም ሌላ ከዚህ አለም ተለይተው የነበሩ ቅዱሳን ሙሴንና ኤልያስ በደብረ ታቦር በጌታ ግራና ቀኝ ተገልጠው ሲነጋገሩ መታየታቸው ተጨማሪ ምስክር ነው፡፡ማቴ 17፤2
4.6 ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል
      ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሀፈ መክብብ 9፤4 ላይ ‹‹ያልሞተ ውሻ ካልሞተ አንበሳ ይሻላል›› ሲል ምን ማለቱ ነው
     ይህን ሀይለ ቃል ለመረዳት በመጀመሪያ የምሳልን አመሳሰል ዘይብና ምንነት መረዳት ያስፈልጋል ምሳል የነገርን ፊት ለመግለጠና አንድን ሀሳብ ሰሚው በሚረዳው መንገድ ለመግለጽ አስረጂው የሚጠቀምበት ስልት ከሚመስልለት ነገር ጋር ቐሚ ዌም ዘላቂ የሆነው ግንኙነት ያለውአይደለም ምሳልውም ራሱ ነገሩ ከሆነ ምሳልነቱ ይቀራል አንድ ነገር ለተለያዩ ነገሮች ሳይቀር ሊያገለግል እንደሚችል መረዳት ይገባል ለምሳሌ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ተራራ ዝግባ ድንጋ ወዘተ ለተለያዩ ነገሮች ምሳሌ ሆነው ለአስረጂነት ቀርበዋል ወደነገራችን ስንመለስ ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሀፈ መክብብ ላይ ጠቀሰውን እንዲረዳን ዝቅ ብለን ስንመለከተው‹‹ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከህያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው ህያዋን እንዲሞቱ ውቃሉና ሙታን ግን አንዳች አያውቁም መታሰቢያቸውም ተነስቶልና ከዚያ በሆላ ዋጋ የላቸውም›› ነው የሚለውመ.መክ 9፤4-5፡፡
    በመጽሀፍ ቅዱስ ውሻምሳል ሆኖ በብዙ መልኩ ተጠቅሶል ግታችን በወንግል‹‹እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳያነክሱአችሁ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ›› ብሎል ማቴ 7፤6 ውሾች ያላቸው መናፍቃንን ነው በለእየ ዩሀንስ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደማይገቡ ተጠቅሶል ዩሀ ራ2፤15 እና 22፤15 ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከውሾች (ከመናፍቃን) ተጠበቁ›› ብሎል ፊሊጲ 3፤2 ቅዱስ ጴጥሮስም ከክህደት ወደ እምነት ከመጡ በሆላ ተመልሰው ወደ ክህደት የሚመለሱትን ሰዎች በውሾች መስሎቸዋል 2ኛ ጴጥ 2፤22 በልላ መልኩ ደግሞ በወንግል ጌታችን ከነአናዊቶን ሴት ‹‹የውሾችን ምግብ ለቡችሎቻቸው መስጠት አይገባም ብሎታል እሶም መልሳ ቡችሎችም የጌቶችቸውን ፍርፋሪ ይመገባሉ በማት ስለ ትህትናዋ ጌታችን ልመናዋን ሰምቶ ልጆን አድኖላታል ፡፡ ማቴ 15፤21፤25 ከዚህ የምንማረው እንደዚች ሴት ስለ ሀጢያታቸው የሚጸጸቱ ከልባቸው ሰዎች ራሳቸውን ንቀውና ተጸይፈው ‹‹አዎ ውሻ ነኝ››እንደሚሉ ነው ይህ በሰውምእግዚአብሔርዘንድ የሚያስመሰግን ታላቐ ትህትና ነው ከሞተ አንበሳ ይሻላሉ የተባሉት ውሾች እነዚህ ናቸው፡፡ እነዚህም አንዴ ከተመለሱ በሆላ ወደ ሆላ አይሉም ውሻው ለጌታው እስከ መጨረሻው ታማኝ እንደሆነ እነርሱም አስከ እለተ ሞታቸው ለጌታቸው ለእግዚአብህር ታማኝ ናቸው፡፡
    አንበሳ ደግሞ ብርቱና ሀያል ስለሆነ የነገስታት ምሳሌ ነው፡፡ምሳ330፤30 ለዚህ ነው ከይሁዳ ወገን ስለሚወለዱ ነገስታት ‹‹ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው የተባለው ዘፍ 49፤9 ይሄ ለጊዜው ለዳዊት ሲሆን ፍጻሜው ግን ለኢየሱስ ክርስቶስ ነው በመሆኑ ሰብአ ሰገል ‹‹የተወለደው የይሁድ ንጉስ ወዴት ነው››ብለው ጠይቀዋል ማቴ 2፤27 ትንቢቱም ‹‹አንቺ ቤተልሄም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለአለም የሆነ (ለዘመኑ ጥንት ፍጻም የልለው) በእስራእልም ላይ ገዢ(ንጉስ) የሚሆን ይወጣል›› ተብሎ በነቢዩ በሚኪያስ ተነግሮል ሚኪ5፤2 ቅዱስ ዩሀንስም በራእዩ ‹‹ከሊቃናቱ አንዱ አታልቅስ ከይሁዳ አንዱ የሆነውአንበሳ ዕርሱም በዳዊት ስር መጽሀፉን የዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማህተም የፈታ ዘንድ ድል ነስቶል አለኝ›› ብሎል ራዕ 5፤5 በልላ በኩል ደግሞ ሰይጣን በነጣቂነቱንበአንበሳ ተመስሎል ለዚህ ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹በመጠን ኑሩ ንቁ ባለጋራችሁ ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚገሳ አንበሳ የዞራልና›› 1ኛጴጥ 5፤8
    እንግዲህ በነጣቂ አንበሳ የተመሰለ ዲያቢሎስ አድሮባቸው በሀጢያት በበደል የኖሩ ዐና ንሰሀ ሳይገቡ የሞቱ ሰዎች የሞተ አንበሳ ይባላሉ ምክንያቱም በህይወት በኖሩበት ዘመን ለሀጢትና ለበደል ለክህደትና ለክፋት አንበሶች ነበሩና ሰው ስለክፉ በአውሬ መመሰሉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ነው መጥምቀ መለኮት ይጻፍት ፈሪሳውያንንና ሰዱቃውያንን ‹‹እናንተ የእፉኝት ልጆች›› ብሎቸዋል ሉቃ13፤32 ሀሳዊ መሲህ (ሀሰተኛው መሲህ) አውሬ ተብሎል ራዕ 13፤1 እንግዲህ ጠቅለል ባለ መልኩ ‹‹ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና›› ማለት በህይወት እያሉ ስለ ኃጢያታቸው የሚጸጸቱ ንሰሀ የሚገቡ ትንሳኤን ልቦናን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች ሳይጸጸቱ ንሰሀ ሳይገቡ ከሞቱ ሰዎች ይሻላሉ ማለት ነው፡፡
4.7 ሕያዋንና ሙታን
   ህያዋን የሚባሉት ሀይማኖትን የዘው ምግባር ሰርተው ያረፉ ቅዱሳን ናቸው ጌታችን በወንጌል ‹‹ትንሳእና ህይወት እን ነኝ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኮ ሕያው ይሆናል ህያው የሆነ የሚያምንብኝ ሁሉ ለዘለአለም አይሞትም››ዩሀ 11፤25-26 ብሎል ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ክርስቶስ ከሙታን ተነስቶ ወደፊት ዕነዳይሞት ሞትም ወደፊት እንዳይዘው እናውቃለንና መሞትም አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለሀጢያት ሞቶላና በህይወጠ መኖርን ግን ለእግዚአብሄር ይኖራል እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለሀጢያት እንደሞታችሁ ግን ለጌታችሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ሆናችሁ ለእግዚአብሄር ህያዋን እንደሆናችሁ ቁጠሩ››ብሎል ሮሜ 8፤9,11
  ሙታን የሚባሉት ደግሞ ኃጠአን ናቸው ከኃጢአት አእስካልተመለሱ  ድረስ በህይወትም እያሉ ሙታን ይባላሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተከተሉት መካከል አነዱ ‹‹ጌታ ሆይ አስቀድሜ ልሂድና አባትን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ›› ቢለው ኃጢያታቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዎቸው››ብሎታል ማት8፤21 በዚህም በንሰሃ ተመልሰው ወደ ጉባኤ ያልመጡትን እርሱን ያልተከተሉትን በቁማቸው ሙታን ብሎቸዋል ይኸውም ሙታን አእምሮ ሙታን ልቦና ሲላቸው ነው ከዚህ አለም ከተለዩ በሆላ ሞተ ነፍስ ስለሚጠብቃቸው ሙታን ይባላሉ ‹‹ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኩሳንም የነፍስ ገዳዮችም የአስማተኞችም ጣኦትም የሚያመልኩ የሀሰተኞችም ሁሉ እድላችው በዲንና በእሳት በሚያቃጥል ባህር ነው ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው፡፡››አነዲል ራእ 21፤8
   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳ ህያዋን ሀጠአን ደግሞ ሙታን እንደሚባሉ ጠቅሶ ሲናገር ‹‹አእን የአብርሀም አምላክ የይስወቅ አምላክ የያዕቆብ አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሄር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን የህያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አይደለም ፡፡››ብሎል ማቴ22፤31-32 ስለዚህ በመጽሀፈ መክብብ‹‹ሙታን ግን አንዳች አያወቁም መታሰቢያቸውም ተረስቶልና ከዚያ በሆላ ዋጋ የላቸውም›› የተባሉት ሀጥአን ናቸው ይህንን በተመለከተ ነቢየ እግዚአብሄር ዳዊት ‹‹መታሰቢያቸውን ጠፋ ከምድር ዘንድ ጠፋ የእግዚአብሄር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው ብሎል መዝ 33፤16ስለ ቅዱሳን ግን ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ነው›› መዝ 111፤6‹‹የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣችሆለሁ የማይጠፋም የዘለአለም ስም እሰጣችሆለ፡፡››ተብሎል ት. ኢሳ 56፤5
4.8 ማጠቃለያ
  የሰው ልጅ ቅዱሳንን ቢያከብር ስማቸውን ቢጠራ መታሰቢያቸውን ቢያምህረትና በረከትን ያገኛል ባያከብር ግን መርገምን ይሸከማል፡፡ለዚህም ነው እግዚአብሄር አብርሀምን ‹‹እባርክሀለሁ ስምህን አከብረዋለሁለበረከትም ይሁን የሚባርኩህንም እባርካለሁ የሚረግሙህንም ረግማለሁ››ዘፍ 12፤2-3 በተጨማሪም እግዚአብሄር አማላክ አብርሀምን ‹‹በሰዶም ከተማ አስር ጻድቃን ባገኝ ስለ አስሩ ጣድቃን ስል ከተማዩትን እምራለሁ›› ብሎታል ዘፍ 18፤32 ህም እግዚአብሄር ስለ ጻድቃን ብሎ እንደሚምር ትልቅ ትምህርት ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምም በሶራውያን በተከበበች ጊዜ ‹‹ስለ እኔም ስለባሪያይም ስለ ዳዊት ስል የህቺን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ››ብሎል ኢሳ 36፤33-35 ጠቢቡ ሰሎሞንም ደግሞ ‹‹ስለ ባሪያዬ ዳዊት እና ስለ ኢየሩሳልም ስል ለልጅህ አንድ ነገር እሰጥሀለሁ አእንጂ መንግስትህን ሁሉ አልቀድም›› ብሎታል 1ኛ ነገስት 11፤13 ነቢየ እግዚአብሄር ዳዊትም እግዚአብሄር ስለ ባለሞሉ ሙሴ ብሎ እስራእልን እንዴት እንደመራቸው ሲናገር ‹‹እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሴ በመቅሰፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ›› ብሎል መዝ 105፤23 የግብጻዊው የጲጢፋራ ብት ስለዮሴፍ በውጪማ በግቢም በበረከት ተሞልቶል፡፡ ዘፍ 39፤1-6 የሰራፕታዊ ሴት ስለ ነቢዩ ስለ  ኤልያስ ተባርኮል 1ኛ ነገ 4፤1-7 ሱናማዊቶ ስት ስለ ኤልሳስ ቤቶ ተባርኮላታል፡፡ 2ተኛ ነገ 4፤1-7 ለዚህም ነው ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ዋጋ ያገኛል-----እውነት እውነት እላችሆለሁ በደቀ መዝሙሬ ስም ቀዝቃዛ ውሀ የሚያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም›› ብሎል ማቴ 10፤42

Ÿ=\w

c<^ò
 በልላ በኩል ደግሞ የንጉሱ የአካዝያስ ወታደሮች ነቢዩ ኤልያስን ባለማክበራቸው እሳት ከሰማይ ወርዶ አቃጥሎ ገሎቸዋል 2ኛ ነገ 1፤9-12 የቤቴል ወጣቶች ነቢዩ ኤልሳዕን ባለማክበራቸው ተረግመው በዱር አውሬ ተበልተዋል 2ኛ ነገ 2፤23 ግያዝም ነቢዩ ኤልሳዕን በመዋሸቱ ተረግሞ በለምጽ ነድዶል 2ኛ ነገ 1፤9-2 የሶሪያ ሰራዊት ደግሞ ታውረዋል 2ኛ ነገ 6፤18 በአዲስ ኪዳንም ሐናንያንና ሲጳራን ቅዱስ ጴጥሮስን በመዋሸታቸው ተቀስፈው ሞተዋል የሐዋ 5፤1-11 ኤልማስ የተባለውም ጠንከቆይም የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት በማጣመሙ ታውሮል የሐዋ 13፤4-12 እንግዲህ መምረጥከመርገም ይልቅ በረከትን መምረጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን በረከት አይለየን አምን፡፡          
ምዕራፍ አምስት
ቅዱሳን መላእክት
5.1የመላእክት ተፈጥሮ
 ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሯቸው በውል አይታወቅም ማለትም የተፈጠሩት በገቢርም በነቢብም አይደለም እንዲ ካለመኖር ወደ መኖር በሐልዮ(በሀሳብ) ነው የተፈጠሩት ነገር ግን ነቢየ ልዑል ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ መላእክት መንፈስ (ነፍስ) አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል አደረገ ›› በማለት መዝ 103÷4 ላይ እንደተናገረው እንደ እሳት ፈጣኖች እንደ ነፋስ ፈጣኖች አድርጎ ፈጠራቸው ለማለት ነው፡፡ ይሕም አገልግሎታችውን የሚመለከት ነው፡፡እሳትን ነፋስ ለመላእክት አገልግሎት ኃያልነት ረቂቅነት ፈቃድ ፈጻሚነት ምሳሌ ነው፡፡ ሊተቀሱም እንኳን ለእነርሱ ሕጸጽና ድክመት በመላእክት ሌለ ነው፡፡የተፈጠሩትም በመጀመሪያው ቀን በዕለተ እሁድ ነው ይኽንንም ቅዱስ ኢጲፋንዮስ አክሲማሮስ በተባለው መጽሐፉ ‹‹እግዚአብሔር መላእክትን በዕለተ እሁድ ፈጥሮ በሶስቱ ሰማያት(በኢዮር፤በራማ፤በኤረር) በከተማ ዐሥር በነገድ ደግሞ 100 አድርጎ አሰፈራቸው፡፡ ብሎ ተናግሯል፡፡ ቅዱሳን መላእክት በነገድ መቶ እንደሆኑ ጌታችን በወንጌል ‹‹ምን ይመስላችኋል ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነረሱም አንዱ ቢባዝን ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሔዶም የባዘነውን አይፈልግምን›› በማለት ለምሳሌ አስተምሯል ማቴ18÷12 በሳጥናኤል ዲያበሎስ ፈንታ ከዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ጋር መቶኛ ነገድ ተብሎ ተቀጥሮ የነበረ ኋላም የባዘነ አነድም ነው፡፡ ከተሞቻቸው ዐሥር እንደሆኑም በምሳሌ ሊያስተምር ‹‹ ወይም ዐሥር ድሮም የላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት መብራት አብራታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት ብሏል፡፡ሉቃ15÷8
5.2 የመላእክት አለቆች አሰፋፈራቸው
ከሰባቱ ሰማያት መካከል ሶስቱ ኢዮር ራማ ኤረር የተባሉት ሰማያት ዓለመ መላእክት
ይባላሉ በነዚሕ ሰማያት እግዚአብሔር መላእክትን በመቶ ነገድ በአስር ከተማ ከፍሎ አሰፈራቸው አለቆችንም  ሾመላቸው፡፡
.አንደኛውን ሰማይ ኢዮር በአራት ከተማ ከፍሎታል፡፡

udØ“›?M ð”{ pÆe T>”›?M

c<^ò

pÆe T>›?M

›Ò°´ƒ

Ÿ=\u?M

c<^ôM

ŠÃLƒ


›=
Ä
`

 



                     


ኪሩብ
                                                                   






 እግዚአብሔር በኢዮር ዐርባውን ነገደ መላእክት አሰፈራቸው እነርሱም ለዐራት ከፍሎ አራት አለቆች ሾመላቸው ኢዮርንም እንደ ፎቅ ቤት አድርጎ ለዐራት ከተማ ከፈላት፡፡
-‹‹ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ በእጁም ከመሰዊያው በጉጠት የወሰደው ፍም ነበር››ት.ኢሳ 6÷6 እኔ የእግዚአብሔርን ሰራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ ኢሳ5÷14 መጻ.ሔኖ10÷2-6 ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል ዳን12÷1 እንዲሁም ት.ሳን 10÷21 ይሁዳ ቁ9(1-9)
ሁለተኛውን ሰማይ ራማን በሦስት ከተማ ከፍሎታል፡፡

 pÆe Ñw`›?M

pÆe c<^ôM

pÆe \ó›?M

YMדƒƒ

S“w`ƒ

›`vw


    ^
T








  
እግዚአብሔር በራማ ሰላሳውን ነገደ መላእክት አሰፈራቸው እነርሱንም ለሦስት ከፍሎ ሦስት አለቆችን ሾመላቸው ራማንም እንደ ፎቅ ቤት አድርጎ በሦስት ከተማ ከፈላት አስሩን ነገድ አርባብ አላቸው አለቃቸውም ቅዱስ ገበርኤል ነው፡፡ መጽ.ሔኖ 10÷6-7 ሁለተኛም ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን መናብርት አላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩኤል ነው፡፡ መጽ.ኄኖክ 10÷7 የመኳንንት አለቃ ስዳካኤል ሲሆን እነዚህ መላእክት የሰውን ሁሉ አጥንት ሥጋ ሰብስበው ለትንሣኤ የሚያበቁ መላእክት ናቸው፡፡ማቴ 24÷31-32
ሦስተኛው ሰማይ ኤረር በሦስት ከተማ ከፍሎታል፡፡

kÆe ›“”›?M

pÆe cL›?M

pÆe cÇ”›?M

መላእክት

ሊቃናት

መኳንንት



 








እግዚአብሔር በኤረር ሰላሳውን ነገደ መላእክት አሰፈራቸው እነርሱንም ለሦስት ከፍሎ ሦስት አለቆች ሾመላቸው ኤረርንም ከፍሎ እንደ ፎቅ ቤት አድርጎ በሦስት ከማ ከፈላት ዐሥሩን ነገደ መላእክት አለቃቸውም አናንኤል ይባላል፡፡እነዚህ መላእክት ከሰማይ በታች ከመድር ሁሉ በላይ የለውን ሁሉ ፀሐይና ጨረቃንም ጭምር የሚጠብቁ ናቸው፡፡ ኩፋ 2÷6-8 በአጠቃላይ እግዚአብሔር አምላክ መላእክትን በነገድ መቶ አድርጎ በአስር ከተማ በሦስቱ ከተማ ሦስቱ ሰማያት አድርጎ አሰፈራቸው መጽ.ኄኖ 2÷27 ኤፌ3÷10 ቆላሲ1÷16 1ኛ ጴጥ3÷22-23
5.3 የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት
 ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለተልእኮ የሚፋጠኑ ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምህረትን እና ቸርነትን ወደ ሰው ልጆች የመጣሉ ‹‹ዳንኤል ሆኖ ጥበብን እና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መደጥቻለሁ ›› የሚለው የቅዱስ ገብርኤል ቃል የሚያረጋግጥልን ይህንን ነው፡፡ት.ዳን9÷22 የሰወችን ልመና መባም ወደ እግዚአብሔር የሳርጋሉ፡፡ ለዚህም መስጢሩ ‹‹ ጸሎትህን ምጽዋትህን በእግዚአብሔር ፊት አረገ›› የሚለው የእግዚአብሔ መልአክ ቃል ነው፡፡ የሐዋ.ሥራ9÷4 ትልቁ ተግባራቸው እግዚአብሔር ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ›› እያሉ በአንድነት እና በሦስትነት ጸንቶ የሚኖር እግዚአብሔር የመሰግኑታል››ት.ኢሳ6÷3
1.ያድኑናል
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት‹‹ የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙርያ ይሰፍራል የድናቸውማል ››መዝ33÷7 በማለት እንድታናግረው እስራኤል ዘሥጋን ከፈርኦን ና ከሰራዊቱ ዘጻ14÷19 አናንያን አዛርያስን ሚሳኤልን ከእቶን እሳት ትን.ዳን 3÷25 ኒዩ ዳንኤልን ከአናብስት አፍ ት.ዳን6÷27 ቅዱሳን ሐዋርያትን ከወይኒ ቤት  አድኗል፡፡የሐዋ.ሥራ5÷19 ለዚህም ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ጌታ መልአኩን ልኮ ከጴጥሮስ እጅና የአይሁድ ህዝብ የጠብቃት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን አወቅሁ፡፡ ›› ያለው፡፡የሐዋ.12÷11 ያዕቆብ‹‹ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ  ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ  እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ አዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴናዎች ይባርክ ››በማለት የቅዱሳን መላእክትን አዳኝነት የተናገረው ዘፍ3፡15-16
2 ይረዱናል
እግዚአብሔር የሰውን ድካም ስለሚያውቅ ቅዱሳን መላእክት እንዲረዱት ፈቃዱ ነው፡፡የሚረዱንም በነፍስም በሥጋም እንድንድን ነው ይኸንን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ ‘’ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?’’ በማለት የተናገረው ዕብ 1፤14 በትንቢተ ዳንኤልም ‹‹የፋርስ መንግስት አለቃ ግን አንድ ቀን ተnnመኝ እነሆም ከዋንኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፡፡››የሚል ተጽፎአል፡፡ ት.ዳን 10፤21 ነብዩ ዳንኤል በጾም ወራት መልአከ እግዚአብሔር በተገለጠበት ጊዜ የሆነውን ሲገልጽ ‹‹ኃይልም አልቀረልኝም ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ ኃይልም አጣሁ …..ደግሞ ሰው የሚመስል ዳሰሰኝ አበረታኝ››ብላ;ል ፡፡ት ዳን 10፤8-18 በአዲስ ኪዳንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸሎት አብነት በሆነ ጊዜ በጌቴሰማኒ ዐጸድ የሚንበረታው መልአክ ታይቶታል ሉቃ22፤43 ይኸም ለሥጋ ለባሽ ሁሉ የሚያበረታ መልአክ እንደሚያስፈልገው ያመለክታል፡፡
3 ያማልዱናል
ህዝበ እስራኤል በባቢሎን እጅ ወድቀው በምርከ ሰባ ዘመን በተገዙ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ስለ እነርሱ‹‹አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እነዚህን ሰባ ዘመን የተቆጣኻቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳ ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው ?››ሲል ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹እኔ በታላቅ ቅናት ለኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ እኔ ጥቂት ብቻ ተቆጥቼ ሳለሁ እነርሱ ክፋትን ስላገዙት ባልተቸገሩት አህዛብ ላይ እጅግ ተቆጥቻለሁ፡፡….ወደ ኢየሩሳሌም በምህረት ተመልሻለሁ ቤቴ ይሰራባታል››በማለት በሚያጽናና ቃል መልሶታል፡፡ ዘካ 1፤12-17
4 ጸሎታችንን ያሳርጉልናል
ቀርለኔዎስ የነበረውን ጸሎትና ምጽዋት ቅድመ እግዚአብሔር  የነበረው መልአክ ‹‹ጸሎትህንና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ››እንዳለ የነበረው ፡፡የሐዋ 10፤1-4 በዩሀንስ ራዕይም ‹‹ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኩለ ሰአት የሚያህል በሰማይ ዝምታ ሆነ በእግዚአብሔርም ፊት የቆሙትን ሰባቱን መልአክት አየሁ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው፡፡ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዘ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣው ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ ››የሚል ተጽፋል ራዕ 8፤1-4 ከዚህም ሌላ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ባየው ራዕይ ከምድር እስከ ሰማይ በተዘረጋው መሰላል ላይ ቅዱሳን መላእክት  ወደ ሰማይ ሲወጡት ወደ ምድር ሲወርዱ ታይተዋል፡፡ዘፍ 28፤12 ይህም የምድራውያን ጸሎት የማሳርጋቸውንና የእግዚአብሔርን ቸርነት ምህረት የማውረዳቸውን ነገር የሚናገረው ነው፡፡ በአዲስ ኪዳንም መግቢያ ላይ ለነበረው ጻድቅ ካህን ዘካርያስ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ ‹‹ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሀልና አትፍራ››ማለቱ የኽንን የማይጠናከር ነው ሉቃ 1፤13 ምክንያቱም የሰው ልጅ ሳሎ የሚያሳርጉት ቅዱሳን መራእክት በመሆናቸው ቅድመ እግዚአብሔር የደረሰውን  ያልደረሰውን ያውቃሉ ማኑሄና ሚስቱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መስዋት ባቀለቡ ጊዜ  መልአኩ በመስዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐርጎል ይህም ጸሎታቸውንና መስዋዕታቸውን እንዳሳረገላቸው የሚያመለክት ነው መሳ 13፤20
5 ይዋጉልናል
የሰው  ልጅ ጦርነት በሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከአጋንንት ጋር ነው፡፡ገላ 6፤12 ስለ ሙሴ በሥጋ ከዲያቢሎስ ጋር ተከራክሮ በተግሳጹ እንደ ትቢያ ተበተነው የእግዚአብሔር መልአክ ነው፡፡ለእኛም ከዲያቢሎስና ከሰራዊቱ ጋር ተዋግተው ድል የሚነሱልን ቅዱሳን መራእክት ናቸው ምክንያቱም ጥንት ድል የነሱት እነሱ ናቸውና ‹‹በሰማይም ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውም ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእነሱ ጋር ተጣሉ ››ራእ 12፤7 በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉስ በሰናክሬም በተከበበች ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ሕዝቅያስንና ሕዝቡን ለመርዳት ከአሶርያውያን ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺ(185000)ገድሎ በማሸነፍ አድኖአቸዋል ተ.ኢሳ 37፤36 ስለዚህ ለነፍሳችንም ሆነ ለሥጋችን እንደሚዋጉልን  እንደሚያሸንፉልን እናምናለን፡፡
6 ይጠብቁናል
ቅዱሳን መላእክት በመንገዳችሁ ሁሉ ይጠብቁናል ለዚህም ነቢየ ልዑል ዳዊት ‹‹ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም መናፍስትም ወደ ቤትህ አይገባም በመንገድ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክትን ሁሉ አንተ ያዝዛችዋል እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሀል ››ያለው መዝ 90፤10-12 በኦራት ዘጸአት ላይ ‹‹በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ይገባ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰግዳለሁ በፊቱ ተጠንቀቁ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጥያት ብትሰሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት ፡፡››የሚል ተጽፎል ዘዳ 23፤20 ጌታችን በወንጌል ላይ እያንዳንዳችን ጠባቂ መልአክ እንዳለን ተናግሮል ነቢዩ ኤልሳ በሶርያ ንጉስ ሠራዊት በፈረስ በሰረገላ በተከበበ ጊዜ የእሳት አጥር ሆነው ዙርያ በፈረሶችና ሰረገሎች ሞልተውት የተጠበቁት ቅዱሳን መላእክት ናቸው  2ነገ 26፤14-18 ጻድቅ ሎጥም የሰዶም ሰዎች ቤቱን ከበው ባስጨነቁት ጊዜ  የጠበቁት ቅዱሳን መላእክት ናቸው ፡፡ዘፍ 19፤1-28 ስለ ቅዱሳን መላእክት ነቢዩ ዳንኤል ‹‹በአገልጋዬም ላይ በራሴ ዐየሁ እነሆ አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ወረደ ብሎል ተ.ዳ 4፤13
7 ይካሰሱልናል
አንዳንድ ሰው በመአልትና በለሊት የሚጠብቁት መላእክት አሉት፡፡እነርሱም የአንዳንዱን ሰው ህይወት በክፉ ነገር ከመጠበቅ አልፎ ገን ለጎን ስለሚጠብቁት ሰው ህይወቱን በእግዚአብሔር ፊት ይከስሱታል በባ;ለማልነት በእግዚአብሔር ፊት እውነተኛ ፍርድ ይጠይቁለታል ለዚህም ነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹‹ከእነዚህም ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኃለሁና››ያለው፡፡ማቴ18፤10 በትንቢተ ዘካርያስ እንደተፃፈው  ሰይጣን ካህኑን ኢያሱ ለመክሰስ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ ለካህኑ ለኢያሱ ተከራክሮ ሰይጣንን አሳፍሮ ያስፈረደለት የእግዚአብሔር መላእክት ነው ተ.ዘካ3፤1-10
8 ያጽናኑናል
የሰው ልጅ የሚጽነው ‹‹እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል ››በተባለው መሰረት እስከ መጨረሻው መጽናት ሲችል ነው፡፡ማቴ24፤13 ምክንያቱም ማዕበሉ ቀላል አይደለም በመሆኑም መከራው ፈጽሞ ተስፋ እንዳያስቆርጠንና ወደ ክርክር እንዳናወራ ኃያላን የሆኑ ቅዱሳን መላእክት ጸንተን እንድንቆም ይረዱናል ይኸንን በተመለከተ ‹‹ነግር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ በዚህም ነግር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጽናኝ የለም ››የሚል ተጽፎአል ት.ዳን 10፤21
9ይቆሙልናል
ቅዱሳን መላእክት ከእኛ ከሥጋውያን በላይ የሀነ መከራ ሲመጣ ሲያጋትምን ስለኛ ይቆሙልናል የኽውም መከራ ፈፅሞ እንዳያጠፉት ነው ለዚህ ነው ታላቁ ነቢይ ዳንኤል በዚያ ዘመን ስለህዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ መልአክ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ››በማለት ለካህኑ ዘካርያስ ነግሮታል ፡፡ሉቃ1፤19
10 በንስሐችን ደስ ይላቸዋል
እኛ በንስሐ ከኃጥያት ወደ ጽድቅ ስንመለስ ከበደል ስንርቅ ከጨለማ ወደ ብርሃን ስንወጣ ከሞት ወደ ህይወት ስንሸጋገር ደስ ይላቸዋል ምክንያቱም በእኛ የንስሃ ጉዞ ውስጥ የእነሱ ተራዳኢነት አለ፡፡ ለምሳሌ ጌታችን ፈጣሪያችን መድኃኒዓለም በወንጌል ሲያስተምር ‹‹ዐስር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት መብራት አብርታ ቤትዋን ጠርጋ እስታገኝ ድረስ የማትፈልግ ማን ናት?ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጎረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ የጠፋውን ድሪም ዐግኝቻለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላችዋለች እላችኀለሁ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጥያተኛ በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ደስታ ይሆናል ››ያለው ለዚህ ነው፡፡ሉቃ15፤8-10 ጌታችን የጠፋውን አዳም ለመፈለግ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሶ ነፍስን ነስቶ በተወለደ ጊዜም እግዚአብሔርን አመስግነዋል ‹‹ክብር በእግዚአብሔር  በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፍቃድ›› በሚል መዝሙር ደስታቸውን ገልጠዋል፡፡ሉቃ2፤13-14
11 ይመግቡናል   
ኤልዛቤል ነቢዩ ኤልያስን  ልትገድለው በዛተችበት ጊዜ ወደ ምድረበዳ ተሰደደ፡፡ ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠ ‹‹ይበቃኛል አሁን ም አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ››ብሎ እንደሚሞት ለመነ በክትክታውም ዛፍ ባታች ተጋደመ እንቅፍፍም አንቀላፋ እነሆም መልአክም ዳሰሰው ‹‹ተነስተህ ብላም ጠጣም ተመልሰህም ተኛ የእግዚአብሔር መልአአክም ዳግሞ ሁለተኛ ጊዜ መጥቶ ዳሰሰውና ‹‹የምትሔድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነስተህ ብላ››አለው ተነስተም በላ ጠጣም በዚያም ምግብ እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና ሌሊት ሄደ፡፡ 1ኛነገ 19፤1-8
12 ያጽናኑናል
የሰው ልጅ በመከራ ምክንያት ፈጽሞ እንዳያዝንና ተስፋ እንዳይቆርጥ ቅዱሳን መላእክት ያጽናኑናል ሐዘኑን ወደ ደስታ ለቅሶውን ወደ ሳቅ ይለውጡለታል የእስማኤል እናት ግብፅአዊተ;  አጋር በቤርሳቤህ ምድረ በዳ ሰው የሚያጽናና ማንም በሌለበት ውሃዋ አልቆባት ልጆም ለሞት ተቃርቦ በትቀበዘበዘ ሰአት መልአከ እግዝአብሔር‹‹አጋር ሆይ ምን ሆንሽ እግዘዚአብሔር የብላቴናውን ድምጽ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ ተነሺ ብላቴናውንም አንሺ እጅሽንም በእርሱ አጽናኚው ትልቅ ህዝብ አደርገዋለሁና ››እያለ አጽናናት እግዝአብሔርም ዐይንዋን በከፈተላት ጊዜ የውኃ ጉድጎድ አየች ሄዳም አቁማዳዋን በውኃ ሞላች ብላቴናውንም አጠጣች ዘፍ 21፤14-26 በአዲስ ኪዳንም በክርስተስ መከራና ሞት አዝነው የነበሩ ሴተችን ያጽናኑ መላእክት ናቸው ‹‹መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው እናንተስ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንዳትሹ አውቃለሁና እንደተናገረው ተነስቶአልና በዚህም የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ ››ማርያምም እያለቀሰች ቆማ ሳለ ዝቅ ብላ ወደ መቃብሩ ስትመለከት ‹‹ሁለት መላእክት ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶ በነበረው አንዱ በራስጌ ጌላውም በእግር ተቀምጠው ዐየች ፡፡እርሱም አንቺ ሴት ስለ ምን ተለቅሻለሽ አላት ››ዩሐ20፤11-13 ማቴ28፤5-6 ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ባረገበት እለት በሐዘን ተውጠው ትኩር ብለው ሰማይ ሰማዩን ሲያዩ ያጽናኑአቸው ቅዱሳን መላእክት ናቸው ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ የለበሱ (መላእክት በሰው አምሳል ይገለጣሉና)በአጠገባቸው ቆመው እናንተ የገሊላ ሰዎች ወይ ወደሰማይ እንዳንዳችሁ ለምን ቆማችሁ የናዝሬቱ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እንደወጣ እንደዚሁ ይመጣል አላቸው ዩሐ1፤9-12 ከዛን ሐዋርያትም ተጽናንተው ከተራራው ወረዱ
5.4 ባህርያዊ ሥልጣናቸውና ክብራቸው
በባሕርያቸው ረቂቃንና ፈጣኖች የሆኑ ቅዱሳን መላእክት ባሕርያቸውን የሚገልጽ ሥልጣንና ክብር ተሰተ;ቸዋል ለአብነት ያክል ጥቂቶቹን እንመልከት
1 ኃያላን ናቸው
ቅዱሳን መላእክት የተሰጣቸው ኃይልና ሥልጣን ታላቅ ነው ከዚህም የተነሳ ፍጥረት በፊታቸው ይለዳል ነብዩ ዳንኤል መልአከ እግዚአብሔር በተገለጠለት ጊዜ ‹‹ዐይኔን አነሳሁ እነሆ በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው ዐየሁ አካሉም እንደ  ቢረሌ ይመስል ነበር ፊቱም እንደመብረቅ ይመስል ነበር አይኖቹ እንደመሚገባ  ለበሉ ፋና ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ የቃሉም ድምጽ እንደ ብዙ ህዝብ ድምጽ ነበር እኔም ዳንኤል ብቻይን ራእዩን ዐየሁ  ከእኔ ጋር የነበሩ ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም ነገር ግን ጽኑ መንቀጥቀጥ ወደ ቀባቸው ሊሸሽጉም ሸሹ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ ኃይልም አልቀረልኝም  ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ ኃይልም አጣሁ የቃሉንም ድምጽ ሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግንባሬ ተደፋሁ ››ብሎል ዳን 10፤5-9 በአዲስ ኪዳንም  የሆነውን ቅዱስ ማቴዎስ ሲናገር ‹‹በሰንበትም መጨረሻ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛዬቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባለሉ በላይ ተቀመጠ፡፡መልአኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር ጠባቆችም እርሱን ከመፍራት የተነሳ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ ››ብሎል ማቴ28፤1-4
2 በፍርድ ቀን ተሳትፎ አላቸው
ጌታችን በማቴዮስ ወንጌል ላይ የዳግም ምጽአቱን ጉዳዩ ሲናገር ‹‹መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው አጫሾችም መላእክት ናቸው እንግዱህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል የሰው ልጅ (ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ )መላእክቱን ይልካል ከመንግስቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን  ይለቅማሉ ወደ እቶን እሳትም የጥሎቸዋል በዚያ ጥርስ ማፋጨት  ይሆናል ››ማቴ13፤39-43‹‹የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ስራው ያስረክባሉ ››ማቴ 25፤31‹‹መላእክቱም ከታልቅ መለከት ድምጽ ጋር ይልካቸዋል ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻ ከዐራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን የሰበስባሉ ››ማቴ 24፤31 የጌታችን አገልጋይ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ እራሱ በትእዛዝ በመላእክ አለቃም ድምጽ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ የወርዳልነ››ብሎል1ኛተሰ4፤16
3 ተአምራት ያደርጋሉ
ተአምር ማለት በሰው ዘንድ ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ ነገር ግን ሆኖ የሚታይ ማለት ነው፡፡በጥቅሉ ድንቅ ነገር ማለት ነው ለማኑሄና ለሚስቱ ተገልጦ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ ያበሰራቸው የእግዚአብሔር መልአክ በገሃድ በፊታቸው ልዩ ልዩ ተአምራትን አድርጎል ማኑሄና ሚስቱ ይመለከቱ ነበር መሳ 13፤19 ለምሳሌ ሰለስቱ ደቂቅ ወደ እሳት በተጣሉ ጊዜ መልአኩም አብረአቸው ወደ እይቃጠሉ ማድረጉ ተአምር ነው ነብዩ ዳንኤል ወደ አናብስት ጉድጎድ በተጣለና አፉ በተዘጋበት ጊዜ መልአኩ የአናብስቱን አፍ መዝጋቱ ተአምር ነው ት.ዳን 6፤22 በአዲስ ኪዳንም ቅዱስ ጴጥሮስ በሰትሰለት ታስሮ ወደ ወህኒ ቤት በተወረወረ ጊዜ መልአኩ ወደ እስር ቤት በመግባት ጨለማውን ብርሃን አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስ ከእንቅልፉ ቀስቅሶ ከወህኒው በተአምራት እንዳወጣው ተጽፎአል ሐዋ 12፤6-15
4 ዓመጸኞችን ይቀጣሉ
ቅዱሳን መላእክት ክፎዎችን የመቅጣት ሣልጣን አላቸው የሰዶም ሰዎች የጻድቁን የሎጥን ቤት ከበው ባስጨነቁት ጊዜ ከልጅ እስከ አዋቂ ሁሉንም አሳውረዋቸው ከተማዋን በጠቅላላ አቃጥለዋል ዘፍ 19፤1-20 ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉስ በሰናክሬም ሠራዊት በተከበበች ጊዜ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ ከአሦራውያን ሰፈርም መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ››ተብሎ ተጽፎአል ፡፡በአዲስ ኪዳን በዘመነ ሐዋርያት ደግሞ ሄሮድስ የተባለው ንጉስ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ በትእቢት ድምጹን ከፍ አድርጎ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ‹‹ይህ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው የሰው አይደለም ››ብለው በማይገባ ምሥጋና አመሰገኑት በዚህም ጊዜ በአምልኮተ እግዚአብሔር የቀና መልአክ እግዚአብሔር በሰይፍ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ የሐ12፤20-23
5 የጸጋ ጌትነት አላቸው
ጌትነት የባህርይ ገንዘቡ የሆነ ልዑል እግዚአብሔር የኃይሉ መገለጫ የሆኑት ቅዱሳን መላእክትን በጸጋ ጌትነት አክብሮአቸዋል በሊቀ ነቢያት ሙሴ የተተካው እያሱ ወልደ ነዌ የመልአክ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በተገለጠበት ጊዜ ‹‹ጌታዬ ለባርያው የሚነግረው ምንድን ነው ››ያለው ለዚሁ ነው ኢያ 5፤14 ኢያሱ በእግዚአብሔር ‹‹በሕይወትክ እድሜ ሁሉ ማንም አይnnምህም ከሙሴ ጋር እንደሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም አልተውኽም ››የተባለ ቅዱስ ሰው ነው ኢያ1፤5 ታላቁ ነቢይ ዳንኤልም በጾም ወራት የእግዚአብሔር መልአክ በተገለጠበት ጊዜ ‹‹ጌታዬ ሆይ ከራእዩ የተነሳ ሕመሜ መጣብኝ ኃይልም አጣሁ ይህ የጌታዩ የጌታዬ ባርያ ከጌታዬ ጋር ይናገር ዘንድ እንዴት ይቻላል?አሁንም ኃይልን አጣሁ እስትንፋስም አልቀረልኝም››አልሁት እርሱም ዳሰሰኝ አበረታንም‹‹እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ አትፍራ ሰላም ለአንተ ይሁን በርታ ጽና ››አለኝ በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና ‹‹አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር አልሁ››ብላ;ል ዳን 10፤16-20 ፃቁ ሎጥም ቅዱሳን መላእክት ሊታደጉት በመጡ ጊዜ‹‹ጌቶቼ ሆይ ወደ ባርያችሁ ቤት አቅኑ ››እለ ተማፅና;ቸዋል፡፡ዘፍ 19፤2
6 ስግደት ይገባቸዋል
ስግደት ሁለት ዓይነት ነው፡፡አንደኛው የባህርይ ሲሆን ይህ የሚፈጸው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ምክንያቱም ክብር የባሕርዩ ገንዘብ ነውና፡፡ሁለተኛው  ደግሞ የጸጋ ስግደት ነው ይህም በጸጋ እግዚአብሔር ለከበሩ ለቅዱሳን የሚፈጸም ነው፡፡ በመሆኑም ለቅዱሳን መስገድ የእግዚአብሔር ጸጋ ማክበር ነው፡፡
ፃድቁ ሎጥ ሁለቱ መላእክት (ቅዱስ ሚካኤል እና ቅዱስ ገብርኤል) ሊታደጉት በመጡ ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ ሰግዶላቸዋል ፡፡ዘፍ19፤1 ኤያሱ ወልደ ነዌ በኢያሪስ አጠገብ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር መልአክ በግንባሩ ተደፍቶ ሰግዶል ኢያ5፤14 ነቢዩ ዳንኤል በጾም ወራት ለተገለጠለት መልአክ በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በግንባሩ ተደፍቶ ሰግዶለታል ፡፡መፍራቱም የአክብሮትና የፍቅር ነው፡፡ት.ዳን10፤9
በዩሐንስ ራእይ ላይ እንደተጻፈው ወነወጌላዊ ቅዱስ ዩሐንስ ለእግዚአብሔር መልአክ በሰገደ መልአኩ ግን ‹‹እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ከአንተም ጋር የእየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባርያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ ብሎታል፡፡ቅዱስ ዩሐንስም የሰገደው ለቅዱሳን መላእክት ስግደት እንደሚገባ አውቆ ነው ፡፡መልአኩ ደግሞ ‹‹አትስገድልኝ ያለው ትህትናን እንዲህ መፈጸም ስለሚገባ ነው፡፡ራእ19፤10ቅዱስ ዩሐንስ ወንጌላዊ የእግዚአብሔርን መልአክ ‹‹አትስገድልኝ ››ካለው በኃላ መልሶ ሰግዶለታል  ይኸውም መልአኩ ‹‹አትስገድልኝ›› ማለቱ ለትህትና መሆኑን ስለሚያውቅ ነው መልአኩም የጀመረውን የትህትና ስራ ቀጥሎበት መልሶ‹‹እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ከአንተ ጋር ከወንድመችህም ከነቢያት ጋር አብሬ ባርያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ ››ብሎታል ራእ22፤8-9፡፡ በአጠቃላይ ሁለቱም የፈጸሙጽ የትህትና ሥራ ነው ይህም የሚገባ ነው፡፡‹‹ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል ››ምሳ 29፤23‹‹እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያቃወማል ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ››ያዕ 4፤6 አንድም የእግዚአብሔር መልአክ  ከአንዴም ሁለት ጊዜ ቅዱስ ዩሐንስ ተሰጥቶት የነበረው ክብር እጅግ ታላቅ ስለነበር ነው፡፡ደግሞም ቅዱሳን መላእክት ደስ የሚያሰኛቸው ጌታቸው እግዚአብሔር ያከበረውን ማክበር ነው፡፡
5.5 ማጠቃልያ
ቅዱሳን መላእክት ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው በእግዚአብሔርም ፊት በባለሞልነት የሚቆሙ ናቸው፡፡ሉቃ1፤19 የእግዚአብሔርን ኃይል ለመግለጥ የሚላኩ ናቸው፡፡ኢያ5፤13-15 የእግዚአብሔርን ምህረትና ይቅርታ ለሰው ልጅ ትሩፋትና ማንኛውም በጎ ስራ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡ ናቸው የሐዋ 10፤3 ዕብ1፤14 ከዚህም ሁሉ ጋር በክርስትና ታሪክ ውሰጥ የእግዚአብሔር ምስጢር ተካፋዮች እና የቤተክርስትያን አገልጋዮች ናቸው፡፡በመጀመርያ አምላክ ሰው ሊሆን ነው የምስራችን(ብስራትን)የተናገረ የእግዚአብሔር መልአክ ነው፡፡ሉቃ1፤26-39 በተወለደም ጊዜ ‹‹የዓለም መድኃኒት ተወለደ››ብሎ ለእረኞች የሰበከው መልአክ ነው ሉቃ2፤8-14 የሕፃኑን መሲህ ሕይወት ለማጥፋት እነ ሄሮድስ ያጠመዱትን ወጥመድ በመግለጥ ድንግል እመቤታችንና ጠባቂዋ ጻድቁ አረጋዊ ዬሴፍ ወደ ምድረ ግብፅ እንዲሸሹ ያደረጉ ቅዱሳን መላእክት ናቸው፡፡ማቴ2፤13 ክርስቶስ ወዶ ባደረገው                                               በዲያቢለስ ተፈትኖ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል ባደረገ ጊዜ የድል አድራጊነቱ ምልክት የሆኑት መልአክት ወጥተው አገልግለውታል፡፡ማቴ4፤12 የማስተማር ጊዜውን ፈጽሞ ለሰው ልጆች መስዋትን ለመሆን ወደ መስቀል በሚወጣበት ጊዜ ሊፈረድበት ለተቀመጠው ለጲላጦስ እንግዳ የሆነ አስደንጋጭ ነገር ነግሮታል ‹‹እኔ ከፈለኩ ካንተ ፊት እንዳልቆም ለማድረግ የሚችሉ መልአክትን ማዘዝ እችላለሁ››እንዲል፡፡ዩሐ19፤36 በመስቀል ተሰቅሎ ከሞተ በኆላ በመቃብሩ ዙርያ የተገኙ የትንሳኤንም የምስራች ለሰው የሰሙ መላእክት ናቸው ፡፡ማቴ28፤1 ማር16፤5 ሉቃ24፤4 ዩሐ20፤11 ጌታ የማዳን ስራውን ፈስራውን ፈጽሞ ወደ ሰማያዊ ክብሩ በተመለሠበት እለት ዕለት አንጋጠው ሰማይ ሰማይ እያዩ ያለቅሱ የነበሩ ሐዋርያትን አጽናንተው ዳግም ምጽአቱን ነግረዋቸዋል፡፡የሐዋ 1፤10 የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተቀብለው የክርስቶስን ትንሳኤ ለመመለስ ይፋጠኑ የነበሩ ሐዋርያትን ወኅኒ ቤት ከፍተው እግረ ሙቅ ፈትተው በማውጣት አይዞአችሁ በማለት  የነበሩ መላእክት ናቸው፡፡ሐዋ 5፤19 12፤2፡፡ሰማዕታት የዓላውያን ነገስታትን ግርማ እንዳይፈሩ የሚያበረታቱ ጻድቃን ግርማ ሌሊትን ድምጽ አራዊትን ጸብአ አጋንንትን እንዳያስቀቁ  የሚያደርጉ መላእክት ናቸው፡፡በመጨረሻም በፍርድ ቀን ጌታን ተከትለው ይመጣሉ፡፡የእግዚአብሔርም ምርጦች ከዐራቱን ማዕዘናት ይሰበሰባሉ ፡፡ማቴ24፤31
       ስለዚህ ሁሉ ነገር የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት የእግዚአብሔርን አምልኮት ለምትመሰክር ቤተክርስትያን ኃይል ድጋፍ ስለሆነ ቤተክርስትያናችን ቅዱሳን መላእክት ታከብራቸዋለች በአማላጅነታቸውም ትማጸናለች፡፡ድርሳናቸውን በመጻፍ ከፈጣሪያቸው እየተላኩ ያደረጉትን ተአምራት ሁሉ መዝግባ በማንበብና በመጸለይ ለቅዱሳን መላእክት ያላትን አክብሮት ትገልጣለች በዓላትን በቀኖናዋ ወስና ‹‹ዛሬ በዓለ ሚካኤል ነው ዛሬ በዓለ ገብርኤል ነው››እያለች በዓላቸውን ታከብራለች ዝክር               ትዘክራለች በስማቸው መታሰቢያ ቤተክርስትያን ትሰራለች ፡፡ልጆችዋን ገብረ ሚካኤል ወለተ ሚካኤል እያለች በስማቸው ትሰይማለች ቤተክርስትያን የምእመናን ህይወትን የቅዱሳን መላእክትን አገልግሎት የተሰናሰለ ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን