Monday, January 28, 2019

ሥርዓተ ንባብ ዘልሣነ ግእዝ


ሥርዓተ ንባብ ዘልሣነ ግእዝ
የግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ የተወሰነ ሥርዓተ ንባብ አለው፡፡ይህ የንባብ ሥርዓቱ ከተፋለሰ ቋንቋው ለዛ ያጣል፡፡አንባቢውም ሆነ አድማጩ ምሥጢሩን ስለማይረዳው ቃሉ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ የግእዝ መጻሕፍትን ሁሉ ለማንበብ የግእዝ ቋንቋን ሥርዓተ ንባብ መማር ይጠበቅብናል፡፡በግእዝ ቋንቋ ትምህርት ውስጥ አንዱ እና ትልቁ ክፍል የንባብ ህግጋቱነው፡፡በግእዝ ቋንቋ ሶስት ዓይነት የንባብ ዓይነቶች አሉ፡፡ ይህም አከፋፈል በንባብ ጊዜ ከድምፅ አወጣጥ አንጻር ነው፡፡
ግእዝ ንባብ ይህ የንባብ ዓይነት ቃልን ከቃል እየለዩ የሚነበብበትየንባብ ዓይነት ሲሆን በአብነት ትምህርት ቤቶች የንባብ ትምህርት የመጀመሪያው የንባብ ደረጃ ነው፡፡ ፊደል የለየ ተማሪ የሚያነበው የመጀመሪያው የንባብ ዓይነት ነው፡፡ ሲነበብም ፊደልን ከፊደል እየለዩ በዝግታ ሳብ ሳብ እያለ የሚነበብ የንባብ ዓይነት ነው፡፡
ውርድ ንባብ ይህ ሁለተኛው የንባብ ደረጃ ግእዝ ንባብን አንብቦ የጨረሰ ተማሪ የሚያነበው ቀጣይ ደረጃ ሲሆን የኅዘን ዜማ መልክ ያለው የንባብ ዓይነት ነው፡፡ሲነበብም ቃላትን ከቃላት እየለዩ ነው፡፡የግእዝ ንባብ ጐተት ዝግ ይል የነበረውን ሳብ ሳብ በማድረግ ይነበባል፡፡ሳቢ እና ተሳቢው ተነሽ እና ወዳቂው አንቀጹ እና አንቀጽ አጐላማሹ በየአመሉ እየተለየ የሚነበብበት የንባብ ዓይነት ነው፡፡
ቁም ንባብ ከውርድ ቀጥሎ ሶስተኛው የንባብ ደረጃ ሲሆን ያለአንዳች ችግር ሕግጋተ ንባባትን ተነሽ ተጣዩን ወዳቂና ሰያፉን ጠንቅቆ በመለየት ጠበቅ ያዝ ለቀቅዘለግ ፈጠን እየተደረገ የሚነበብበት የንባብ ደረጃ ነው፡፡ ይህ የንባብ ዓይነት ዘወትር በቤተክርስቲያን በሊቃውንት ፊት ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነበቡበት የንባብ ዓይነት ነው፡፡
በግእዝ ቋንቋ ትምህርት ውስጥ የታወቁት የንባብ ዓይነቶች አራት ናቸው፡፡ እነርሱም፦
               ፩, ተነሽ                        , ወዳቂ
               ፪, ሰያፍ                        , ተጣይ

አንድን ቃል የአነባበብ ሥርዓቱን ለማወቅ የሚከተሉትን መለያዎች እንጠቀማለን
መድረሻ ቀለም
የሆሄያት ተጽዕኖ
ተነባቢ ቀለም
የቃሉ ባህርይ(ስም ወይም ግስ መሆኑ) በዚህ ክፍል ለአካሄድ እንዲያመቸን ከግስ ውጭ የሆኑትን ሁሉ ስም እንላቸዋለን
ተነሽ ንባብ
ተነሽ ንባብ የሚባለው እንደ ቁጣ ቃል የሚነገር ተፈላጊውን ቀለም አንስቶ አንዝሮ የሚነበብ ንባብ ነው፡፡ተነስተው የሚነበቡ ቃላትን ለመለየት የሚከተለውን ዘዴ እንጠቀማለን፡፡
, መድረሻ ቀለም ተነስተው ሊነበቡ የሚችሉ ቃላት በአምስቱ የሆሄ ስልት የጨረሱ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡እነዚህም፦
ግእዝ፣ካዕብ፣ሳልስ፣ራብዕ እና ሳብዕ ናቸው፡፡በእነዚህ ያልደረሰ ቃል ፈጽሞ ሊነሳ አይችልም፡፡
ምሳሌ፦በግእዝ ቆመ፣ገብረ፣ሐቀለ፣አንፈርዐፀ፣ሰበከ
በካዕብ፡ ቆሙ፣ገብሩ፣ሐቀሉ፣አንፈርዐፁ፣ሰበኩ
በሳልስ፡ ቁሚ፣ግበሪ፣ ሕቅሊ፣ስብኪ፣ቀድሲ
በሳብዕ፡ አሥመረቶ፣ንሴብሖ፣ይግብሮ
በግእዝ ወይም በሌሎቹ የጨረሰ ሁሉ ግን ተነስቶ ይነበባል ማለት አይደለም፡፡ለምሳሌ የሚከተሉትን ህገወጦች መመልከት እንችላለን፡፡ ህየ፣እወ፣ሠለስተ፣ክልዔተ፣አርባዕተ በግእዝ ቢጨርሱም ተነስተው አይነበቡም፡፡
አሐዱ፣ክልዔቱ፣ሠለስቱ፣አርባዕቱ በካዕብ ቢጨርሱም አይነሱም፡፡
, ተነባቢ ቀለም የተነሽ ቃላት ተነባቢ ቀለማቸው ቅድመ መድረሻቸው ነው፡፡ ቅድመ መድረሻቸው ቆጣ ነዘር ብሎ ይነበባሉ፡፡ ምሳሌ፡ አእመረ፣ወረደ፣ቀተለ፣ሐወጸ
, የቃል ክፍል በአብዛኛው ተነስተው የሚነበቡ ቃላት ግሶች ናቸው፡፡
ማስታወሻ፦ ሶስት ቀለም ያላቸው በግእዝ ጀምረው ቅድመ መድረሻቸው ሳድስ በሆኑ ግሶች ሳድስ ቀለሙ ተውጦ ይነበባል፡፡
ምሳሌ፦ ገብረ፣ፈርሐ፣መርሐ፣መጽዐ
ኅረየ ዐሥርተ ወክልዔተ አርድእተ
አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ
ንሴብሐከ እግዚኦ
ተጣይ ንባብ
ተጣይ ቀለማት ሲነበቡ እንደ ወዳቂ ቀለም ያዝ ለቀቅ በማድረግ ነው፡፡
, መድረሻ ቀለም ተጣይ ቃላት የሚጨርሱት በሳድስ ቀለም ብቻ ነው፡፡
ምሳሌ፦ ቅዱስ፣ ኅሩይ፣ መንሱት፣ መንበር፣ ሰዋስው፣ ልብ፣ ዮም፣ ጾም
, ተነባቢ ቀለም የተጣይ ቀለም ተነባቢ ቀለሙ ቅድመ መድረሻው ስለሆነ ይህን ቀለም ያዝ ቆየት በማድረግ ይነበባሉ፡፡
, የቃል ክፍል ተጣይ ቃላት በአብዛኛው ስሞች ናቸው፡፡ ከግስ የወጡ ዘሮች በአብዛኛው ተጥለው ይነበባሉ፡፡
ምሳሌ፦ ኀሩያን፣ ቡሩክ፣ ሲሳይ፣ መላእክት
ፃድቃን ወሰማዕት ጽኑዓን በሃይማኖት
ንጉሥ ወካህናት ክቡራን በኅበ እግዚአብሔር
ማስታወሻ፦ የተጣይ ቃላት ሳድስ ቀለማት ተከታትለው ሲመጡ ቅድመ መድረሻቸው ተውጦ ይነበባሉ፡፡
ምሳሌ፦ወርቅ፣ ፍቅር፣ ምድር፣ ምግብ፣ ዘርዕ፣ ቅድስት፣ ትስብእት
ወዳቂ ንባብ
ይህ የንባብ ዓይነት ተፈላጊውን ቀለም ያዝ ቆየት በማድረግ ይነበባል፡፡ ወዳቂ ንባብ ወዳቂ ዜማ ባለው ድምጸ ማኀዘኒ ይነበባል፡፡
, መድረሻ ቀለም የወዳቂ ቀለማት መድረሻ ቀለማት ሰባቱም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ምሳሌ፦ በግእዝ፦ ህየ፣ አሐደ፣ ክልዔተ
በካዕብ፦ ኵሉ፣ ብሔሩ፣ ዝንቱ፣ እሙንቱ፣ እማንቱ
በሳልስ፦ ቀታሊ፣ ገባሪ፣ ዛቲ፣ ኖላዊ፣ ነጋሢ፣ ዜናዊ
በራብዕ፦ ዜና፣ መና፣ ሠረገላ፣ ተድላ፣ መክራ፣ ሀገራ
በኅምስ፦ አይቴ፣ ምናኔ፣ ሥላሴ፣ ልምላሜ፣ ትካዜ
በሳድስ፦ ብቻ ነው(በሳድስ ወዳቂ ብቻ ነው)
በሳብዕ፦ ከበሮ፣ አእምሮ፣ እፎ፣ ተዋህዶ
, ተነባቢ ቀለም በወዳቂ ንባብ ጊዜ ተነባቢ ቀለሙ መድረሻ ቀለሙ ነው፡፡ተነባቢ ቀለሙን ያዝ ቆየት በማድረግ ይነበባል፡፡
, የቃል ክፍል ወድቀው የሚነበቡ በአብዛኛው ስሞች ናቸው፡፡ በዚህ ትምህርት ከግስ ውጭ ያሉትን ሁሉ በስም ስር መድበናቸዋል
ሰያፍ ንባብ
ይህ የንባብ ዓይነት ተፈላጊውን ቀለም እንደ ተነሽ ንባብ አስቆጥቶ አንዝሮ ይነበባል፡፡
, መድረሻ ቀለም ፦ሰያፍ ንባብ በሳድስ ብቻ ይጨርሳል፡፡
, ተነባቢ ቀለም ፦ተነባቢ ቀለሙ ቅድመ መድረሻው ነው፡፡
, የቃል ክፍል ተሰይፈው የሚነበቡ ስሞችም ግሶችም ናቸው፡፡
ምሳሌ፦ አእመረት፣ ቀተለት፣ ይወርድ፣ ይገብር፣ እቀትል፣ ቅትል፣ግበር፣ንላዕ
ኢሳያስ፣ ቶማስ፣ ገብርኤል፣ ጴጥሮስ፣ ዳንኤል፣ ቴዎፍሎስ
ገብርኤል ሰብሐ ኪያሃ
ንፁም ፆመ ወናፍቅር ቢጸነ
ማስታወሻ፦ ሰያፍ እና ተነሽ በአነባበብ አንድ ናቸው የሚለያዩት በመድረሻ ቀለማቸው ነው፡፡
ወዳቂ እና ተጣይ ሥርዓተ ንባባቸው አንድ ነው ቢባልም በተነባቢ ቀለም እና በመድረሻ ቀለም ይለያያሉ፡፡
የግሥ ስልት
በዚህ የትምህርት ደረጃ ለአጠናነፀ ይረዳን ዘንድ ግሶችን በአራት ክፍላት ከፍለን እንመለከታቸዋለን። ነገር ግን ሌሎች መጻህፍ ከዚህ በተለየ መልኩ ከፍለው ሊመለከቷቸው ይችላል።
, ገቢር ግሥ፡- ይህ የግሥ ዐይነት ቃላትንና ሐረጋትን መሳብ የሚችል የአድራጊ ድርጊት የሚገለጽበት የግሥ ዓይነት ነው። በዐረፍተ ነገር ውስጥ ሁልጊዜ ገቢር ስሞችን ይወስዳል።
ምሳሌ፡- ገብረ ሠራ ሰጠቀ ሰነጠቀ
ዘገበ ሰበሰበ ፈኀረ አጨ
ጼሐ ተረገ መሀረ አስተማረ
መርሐ መራ ለበወ አስተዋለ
ፆረ ተሸከመ አርኀወ ከፈተ
ዖደ ዞረ ወዘተ
ቃላትንና ሐረጋትን ሲስቡም በምሳሌ እንደሚከተለው እናያቸዋለን። አብርሃም ገብረ ግብረ ሠናየ
በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ
ቀርነ ነፍሐ ወከለልዎ ክሳዶ ወዘተ
, ተገብሮ ግሥ፡- ይህ የግሥ ዐይነት በገቢር ግሥ ላይ ባዕድ ፊደል በመነሻ በመጨመር የሚመሠረት ሲሆን የተደራጊ ድርጊትን ይገልጻል። ይህ የድሥ ዓይነት ገቢር ግሥን አትስብም።
ምሳሌ፡- ገብር ተገብሮ ገቢር ተገብሮ
ገብረ ተገብረ ቀተለ ተቀትለ
ዘገበ ተዘግበ ጸሐፈ ተጽሕፈ
ሰብሑ ተሰብሑ መሐሩ ተመሐሩ
ሤመ ተሤመ ወዘተ
ማስታወሻ፡- , የሚጀምር ግሥ ሁሉ ተገብሮ ግሥ አይደለም።ምሳሌ፡- ተንበለ/ለመነ፣ ተሞገሰ/ባለሟል ሆነ፣ ተምዐ/ተቆጣ፣ተመነየ/ተመኘ፣ ወዘተ
, የሚጀምር ግሥ ተገብሮ የሚሆነው ተን አስወግደን የቀረው ገቢር ግሥ የሚሆን ከሆነ ብቻ ነው።
, ነባር አንቀጽ- እነዚህ የግሥ ዓይነቶች ከገቢርም ሆነ ከተገብሮ ግሦች ለየት ያሉ ናቸው። ቁጥራቸውም እንደ ገቢርና ተገብሮ ግሦች ብዙ አይደሉም።
ምሳሌ፡- , ውእቱ--- ነው፣ ነበረ፣አለ፣ ኖረ
, --- አለ፣ ኖረ፣ ነበረ
, አኮ--- አይደለም፣
, አልቦ--- የለም፣ አልኖረም፣ አልነበረም
እነዚህ ከገቢርና ከተገብሮ ግሦች የሚለዩበትና የሚመሳሰሉበት ሁኔታ አለ።
የሚለያዩበት፡- 1, መድረሻ ፊደሉ ካእብና ሳብዕ መሆኑ
2,
በካልዓይ፣ በዘንድና በትዕዛዝ አንቀጽ አለመገኘታቸው
3,
ከንዑስ አንቀጽ እስከ ቦዝ አንቀጽ ድረስ ያሉትን እርባታዎች አለማካተቱ
የሚያመሳስላቸው፡- 1, ማሰሪያ አንቀጽ መሆን መቻላቸው
2,
በአሥሩ መራሕያን መዘርዘራቸው
, ግዑዝ ግሥ፡- ይህ የግሥ ዓይነት ደግሞ በቅርጸ ቀለማቱ ገቢር ግሥን ሲመስል ገቢር ቃላትን ባለመሳቡ ተገብሮ ግሦችን ይመስላል። ስለሆነም ይህንን የግሥ አይነት ተን በመጨመር ወደ ተገብሮ ግሥ መቀየር አይቻልም። ይህም የሆነው በራሱ የተገብሮ ግሥ ፀባይ ስላለው ነው። ብዙ መጻሕፍት ግዑዝ ግሥን በተገብሮ ግሦች ውስጥ ያካትቱታል።
ምሳሌ፡- ኖመ--- አንቀላፋ፣ተኛ ሞተ--- ሞተ
ቆመ--- ቆመ ፆመ--- ፆመ
ሖረ--- ሄደ ደግደገ--- ከሳ
ሰከበ--- ተኛ ጎየ--- ሸሸ ወዘተ
መራኁት(የግሥ መነሻዎች)
መራኁት የሚለው ቃል መርኆ የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። ይኸውምአርኀወ = ከፈተካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው። ስለዚህ መርኆ ማለት መክፈቻ ማለት ሲሆን መራኁት መክፈቻዎች ማለት ነው። መራኁት የተባሉትም የግሥ መነሻ ፊደላት ናቸው። በግእዝ ሰዋስው ግሦች የሚነሱት በአምስት ፊደላት ብቻ ነው። አነዚህም መራኁት ይባላሉ። አነርሱም ግእዝ፣ ራብዕ፣ ኃምስ፣ ሳድስና ሳብዕ ናቸው። የግእዝ ግሥ ሁሉ በእነዚህ ይጀምራል እንጅ በካዕብና በሣልስ አይጀምርም።
ምሳሌ፡- በግእዝ__ ቀተለ፣ ሰከበ፣ ሰጠቀ፣ አፍቀረ፣ አርኀወ፣ መርሐ፣ አኀዘ፣ ጎንደየ፣ ኈለቈ
በራብዕ__ ባረከ፣ ሳቀየ፣ ማህረከ፣ ጻህየየ፣ ፃዕደወ፣
በኃምስ__ ሴመ፣ ሤጠ፣ ኄሰ፣ ኤለ፣ ጼሐ፣ሴሰየ፣ ዴገነ፣ ጌገየ፣ ሌለየ፣ ቄቅሐ
በሳድስ__ ብህለ፣ ርእየ፣ ጥዕየ፣ ውኅዘ
በሳብዕ__ ጦመረ፣ ኖመ፣ ሖረ፣ ሎለወ፣ ቆመ፣ ኖለወ፣ ጾመ፣ ኆሠሠ
ማስታወሻ፡ 1, ግሦች ሁሉ መነሻቸው ይለያይ እንጅ መድረሻቸው ሁልጊዜ ግእዝ ቀለም ነው። እንበለ ይቤ
2,
የግሥ ሆህያት ብዛት ቢበዛ ከሰባት አይበልጥም ቢያንስ ከሁለት አይወርድም።
ምሳሌ፡- ዔለ፣ ሤጠ፣ ሁለት ሆህያት
አስተስነአለ= አስተስነአለ ባለሰባት ሆህያት
በግእዝ ቋንቋ ትምህርት የግሦችን ዝርዝር ለመማር ስንጀምር ግሦች በዝርዝር ወቅት የሚያሳዩትን ፀባይ መሠረት በማድረግ ከዚህ እንደሚከተለው እንከፍላቸዋለን።
, አርእስት ግሥ
, ሠራዊት ግሥ
, ስረይ ግሥ
አርእስት ግሥ
አርእስት የሚለው ቃል ችእስ የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን ትችጉሙም አለቆች ማለት ነው። የግሥ አለቆች ወይም መሪዎች የተባሉትም እስከድረስ ያለውን የግእዝ ግሥ ሁሉ የራሱን የአረባብ ስልት ጠብቆ የእነርሱን የአረባብ ባህርይ ተከትሎ ስለሚሄድ ነው። አርእስት ግሥ ቁጥራቸው ስምንት ሲሆን እነዚህም የሚከተሉት ናቸው።
, ቀተለ--- ገደለ , ባረከ--- አመሰገነ
, ገብረ--- ሠራ , ዴገነ--- ተከተለ
, ቀደሰ--- አመሰገነ , ክህለ--- ቻለ
, ተንበለ--- ለመነ , ጦመረ--- ጻፈ

የአርእስት መለያወች
እነዚህ ከላይ የተገለጹት የግሥ አለቆች አንዳአው ከአንዳቸው የሚለዩበት የራሳቸው የሆነ ባህርይ አላቸው። እነዚህንም መለያወች ከዚህ በታች እመንደሚከተለው ከፍለን እናያቸዋለን።
1,
የሆሄ ብዛት
2,
የሆሄ ቅርጽ
3, ሥርዓተ ንባብ / መጥበቅ መላላት/
በዚህም መሠረት የግሥ አለቆች ባህሪያቸውን እንደሚከተለው እናያለን።
, ቀተለ፡-
ሦስት ሆሄያት ብቻ አሉት
ሦስቱም ሆሄያት ግእዝ ብቻ የሆኑ በግእዝ የተነሳ
ላልቶ ይነበባል
, ቀደሰ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆሄያት ያሉት
በግእዝ የተነሳ / መካከሉ ግእዝም ሳድስም ይሆናል/
ጠብቆ የሚነበብ
, ገብረ፡-
ሦስት ሆሄያት ብቻ ያሉት
መካከሉ ሳድስ የሆነ በግእዝ የሚነሳ
ላልቶ የሚነበብ
, ተንበለ;-
አራትና ከአራት በላይ ሆህያት ያሉት
መነሻው ግእዝ መካከሉ ሳድስና ግእዝ የሆነ
ላልቶ የሚነበብ
, ባረከ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆህያት ያሉት
በራብዕ የተነሳ / መካከሉ ግእዝ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል/
ላልቶ የሚነበብ
, ዴገነ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆሄያት ያሉት
በኃምስ የተነሳ / መካከሉ ግእዝ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል/
ላልቶ የሚነበብ
, ክህለ፡-
ሦስት ሆሄያት ብቻ ያሉት
መነሻው ሳድስ የሆነ / ድኅረ መነሻው ሁልጊዜም ሰድስ ነው/
ላልቶ የሚነበብ
, ጦመረ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆሄያት ያሉት
በሳብዕ የተነሳ
ላልቶ የሚነበብ