መስተዋድዳን ቀለማት
በንግግርም ሆነ በጽሑፍ ጊዜ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁየንግግሩን/የጽሑፉን ሐሣብ የተሟላ እንዲሆን የሚያደርጉ ቀለማት አሉ፡፡ እነዚህም በግእዝ ቋንቋ ሰዋስው አገባብ ይባላሉ፡፡አገባባት በሶስት የሚከፈሉ ሲሆን ዐቢይ አገባብ፣ ንዑስ አገባብ፣ ደቂቅ አገባብይባላሉ፡፡ በግእዝ ሰዋስው ደቂቅ አገባብ የተባሉት በአማርኛ መስተዋድዳን የሚባሉት ናቸው፡፡ ለምሳሌያህል ከሶስቱም አገባባት የተውጣጡ ቃላት ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
አገባብ የአማርኛ ፍቺ አገባብ የአማርኛ ፍቺ
ዲበ፣ላዕለ፣መልዕልተ በ _ ላይ ዝንቱ/ዝ ይህ
ታሕተ፣መትሕተ በ _ ታች ዛቲ ይህች
ማዕከለ መካከል/በ _ መካከል እሉ እኝህ
ውስተ ውስጥ/በ _ ውስጥ እላ እኝህ
ቅድመ በፊት/በ _ ፊት ዘ፣እለ፣እንተ የ
ድኅረ በኋላ/በ _ ኋላ በይነ፣በእንተ፣እንበይነ ስለ
እስከ(እስከነ) እስከ በይነዝንቱ፣በእንተዝንቱ ስለዚህ
ኀበ ወደ/ዘንድ እምድኅረዝንቱ ከዚህ በኋላ
መንገለ ወደ እስመ / አምጣነ / አኮኑ ና
አምሳለ እንደ መጠነ ያህል
ከመ እንደ ዳዕሙ / ባህቱ ነገር ግን
ምስለ ጋር አላ እንጅ
እንበለ ያለ፣በቀር ወሚመ/አው ወይም
እም/እምነ ከ ናሁ እነሆ
እመ ቢ፣ባ፣ብ፣ሊ፣ከ ፣ኪ እፎ ንዴት
እንዘ እየ፣ሲ፣ሳ፣ስ ጌሠም ነገ
ሶበ/አመ በ _ ጊዜ ዮም/ይዕዜ ዛሬ
ጊዜ በጊዜ/በ _ ጊዜ ትማልም ትላንት
ምሳሌ ፦ በሚከተሉት ዐ/ነገሮች ውስጥ መስተዋድዳን ቀለማቱን አስተውሉ
ሀ , አመ ተሰቅለ ክርስቶስ መልዕልተ መስቀል ፀሐይ ጸልመ፡፡
ለ , ናሁ ተወልደ ዮም ቤዛ ኵሉ ዓለም በከመተነበየ ኢሳይያስ ነቢይ።
ሐ , ነግሠ ሞት እምነ አዳም እስከ ሙሴ
መ , አመ ይመጽዕ ወልድኪ ምስለ አእላፍ መላእክቲሁ።
ሠ , ሰአሊ ለነ ማርያም በቅድሜሁ።
ረ , ተዐውቀ ዝንቱ ብእሲ በኀበ ሊቃውንትአምጣነ ምሁር ውእቱ።
የመስተዋድዳን ዝርዝር በመራሕያን
መስተዋድዳን ቀለማት የሚዘረዘሩ እና የማይዘረዘሩ አሉ።ከማይዘረዘሩት ለምሳሌ እም፣እስከ
የሚዘረዘሩት መስተዋድዳን ግን በአሥሩ መራሕያን በአገናዛቢ ቅጽል አማካኝነት ይዘረዘራሉ።(ስለአገናዛቢ ቅጽል የስም ዝርዝር በመራሕያን የሚለውን ክፍል አስታውሱ።) በሚዘረዘሩበት ጊዜምአብዛኛዎቹ መድረሻቸውን ወደ ኀምስ ይለውጣሉ።
ምሳሌ ፦ 1, መንገለ
መንገሌሁ =ወደ እርሱ መንገሌከ =ወደ አንተ መንገሌየ=ወደ እኔ
መንገሌሆሙ=ወደ እነርሱ መንገሌክሙ =ወደ እናንተ መንገሌነ= ወደ እኛ
መንገሌሃ=ወደ እሷ መንገሌኪ =ወደ አንቺ
መንገሌሆን=ወደ እነርሱ መንገሌክን =ወደ እናንተ
2, ቅድመ
ቅድሜሁ =በፊቱ ቅድሜከ =በፊትህ ቅድሜየ =በፊቴ
ቅድሜሆሙ =በፊታቸው ቅድሜክሙ =በፊታችሁ ቅድሜነ=በፊታችን
ቅድሜሃ =በፊቷ ቅድሜኪ =በፊትሽ
ቅድሜሆን =በፊታቸው ቅድሜክን=በፊታችሁ
ከኀምስ ውጭም መድረሻቸውን ወደ ራብዕ እና ሳልስ በመቀየርየሚዘረዘሩ አሉ።
ምሳሌ ፦ 1, ከመ
ከማሁ = እንደ እርሱ ከማከ = እንደ አንተ ከማየ = እንደ እኔ
ከማሆሙ = እንደ እነርሱ ከማክሙ = እንደ እናንተ ከማነ = እንደ እኛ
ከማሃ = እንደ እርሷ ከማኪ = እንደ አንቺ
ከማሆ = እንደ እነርሱ ከማክን = እንደ እናንተ
2, ውስተ
ውስቴቱ = በውስጡ ውስቴትከ = በውስህ ውስቴትየ = በውስጤ
ውስቴቶሙ = በውስጣቸው ውስቴትክሙ = በውስጣችሁ ውስቴትነ =በውስጣችን
ውስቴታ = በውስጧ ውስቴትኪ = በውስጥሽ
ውስቴቶን = በውስጣቸው ውስቴትክን = በውስጣችሁ
ሰዋስወ ግእዝ
፪.፩. መራሕያን
መርሐ /መራ/ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን መሪዎች ፊታውራሪዎች የሚለውን ትርጉም ይይዛል። መራሕያን የሚባሉት በግእዝ ልሣን አስር ናቸው።
እነሱም ፦
አነ ………………………………እኔ
አንተ ……………………………አንተ
አንቲ ……………………………አንቺ
ውእቱ ……………………………እሱ
ይእቲ …………………………….እሷ
ንሕነ ……………………………..እኛ
አንትሙ ………………………….እናንተ /ለቅርብ ወንዶች/
አንትን ……………………………እናነተ /ለቅርብ ሴቶች/
ውእቶሙ /እሙንቱ/ …………….እነርሱ /ለሩቅ ወንዶች/
ውእቶን /እማንቱ/ …………………እነርሱ /ለሩቅ ሴቶች/
የመራሕያን አገልግሎት ሦስት ዓይነት ነው፡፡ ይኸዉም ፦
፩.፩. ተውላጠ ስም በመሆን
፩.፪. የመሆን ግስ /ነባር አንቀጽ/ በመሆንና
፩.፫. አመልካች ቅጽል በመሆን
፪.፩.፩. መራሕያን ምድብ ተውላጠ - ስሞች / pronouns /
መደብ ጾታ ነጠላ ቁጥር ብዙ ቁጥር
ሣልሳይ /ሦስተኛ መደብ/ ተባዕታይ ውእቱ ውእቶሙ /እሙንቱ/
አንስታይ ይእቲ ውእቶን /እማንቱ/
ካልኣይ /ኹለተኛ መደብ/ ተባዕታይ አንተ አንትሙ
አንስታይ አንቲ አንትን
ቀዳማይ /፩ኛ መደብ/ የወል አነ ንሕነ
በስም ፋንታ ተተክቶ የሚያገለግል ቃል ተውላጠ-ስም ይባላል። መራሕያን እንደ ተውላጠ-ስም ሲሆኑ በስም ፋንታ ተተክተው የሚነገሩ የርባታ መደቦች ናቸው። እነሱም የአካል፣ የስምና የስም አጸፋ እየሆኑ በወንድና በሴት፣ በሩቅና በቅርብ፣ በነጠላና በብዙ የሚነገረውን ርባታ ያሳያሉ። አስሩም መራሕያን በነጠላና በብዙ፣ በወንድና በሴት፣ በሩቅና በቅርብ ሲከፈሉ ሦስት መደብ ይሆናሉ።
ይኸዉም፦
፩. ቀዳማይ መደብ / 1st person/ አንደኛ መደብ፡ የወል ጾታ
አነ => እኔ = I
ንሕነ => እኛ = we
፪. ካልኣይ መደብ /2nd person/ ኹለተኛ መደብ፡
አንተ => በቁሙ = you
አንቲ => አንተ = you
አንትሙ => እናንተ = you (ለቅርብ ወንዶች)
አንትን => እናንተ = you (ለቅርብ ሴቶች)
፫. ሣልሳይ መደብ / 3rd person / ሦስተኛ መደብ፡
ውእቱ => እሱ = He
ይእቲ => እሷ = She
ውእቶሙ => እነሱ (እነዚያ) = They (ለሩቅ ወንዶች)
ውእቶን => እነሱ (እነዚያ) = They (ለሩቅ ሴቶች)
፩.፩. መራሕያን ምድብ ተውላጠ-ስሞች በዐረፍተ- ነገር
ተውላጠ-ስሞች ቀደሰ፣ ሖረ እና ሰገደ በሚሉት ቀዳማይ አንቀጾች ዐረፍተ- ነገር ሲመሠርቱ፦
ሀ. ቀደሰ / ቀዳማይ አንቀጽ፡ past tense/
አነ ቀደስኩ - እኔ አመሰገንሁ
አንተ ቀደስከ - አንተ አመሰገንህ
አንቲ ቀደስኪ - አንቺ አመሰገንሽ
ውእቱ ቀደሰ - እሱ አመሰገነ
ይእቲ ቀደሰት - እሷ አመሰገነች
ንሕነ ቀደስነ - እኛ አመሰገን
አንትሙ ቀደስክሙ - እናንተ አመሰገናችሁ
አንትን ቀደስክን - እናንተ አመሰገናችሁ (ለሴቶች)
ውእቶሙ ቀደሱ - እነሱ አመሰገኑ
ውእቶን ቀደሳ - እነሱ አመሰገኑ (ለሴቶች)
ማስታወሻ
• ውእቱ / ቀደሰ/ እና ይእቲ /ቀደሰት/ ከሚሉት ውጭ በሌሎች መራሕያን "ሰ" የሚለው ፊደል ወደ ሳድስ፣ ራብዕና ሳብዕ ይለወጣል፡፡
ለ. ሖረ = ሄደ /went/ ፣ ኀበ = ወደ
አነ ሖርኩ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር - እኔ ወደ እግዚአብሔር ቤት ኼድኩ።
አንተ ሖርከ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር - አንተ ወደ እግዚአብሔር ቤት ኼድክ።
አንቲ ሖርኪ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር - You went to church (house of God).
ውእቱ ሖረ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር - He went to church.
ይእቲ ሖረት ኀበ ቤተ እግዚአብሔር
ንሕነ ሖርነ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር
አንትሙ ሖርክሙ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር
አንትን ሖርክን ኀበ ቤተ እግዚአብሔር
ውእቶሙ ሖሩ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር
ውእቶን ሖራ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር
ሐ. ሰገደ = ሰገደ ፣ቅድመ = ፊት ለፊት
አነ ሰገድኩ ቅድመ ቤተ መቅደስ - በቤተ መቅደስ ፊት ሰገድሁ ።
አንተ ሰገድከ ቅድመ ቤተ መቅደስ - You fell on in front of church.
አንቲ ሰገድኪ ቅድመ ቤተ መቅደስ
ውእቱ ሰገደ ቅድመ ቤተ መቅደስ
ይእቲ ሰገደት ቅድመ ቤተ መቅደስ
ንሕነ ሰገድነ ቅድመ ቤተ መቅደስ
አንትሙ ሰገድክሙ ቅድመ ቤተ መቅደስ
አንትን ሰገድክን ቅድመ ቤተ መቅደስ
ውእቶሙ ሰገዱ ቅድመ ቤተ መቅደስ
ውእቶን ሰገዳ ቅድመ ቤተ መቅደስ
ማስታወሻ
የግሱ መጨረሻ ፊደል ‹ከ› ፣‹ቀ› ፣‹ገ› ን የመሰለ ከሆነ ከዚያው ላይ ፊደሉን በማጥበቅ (አነ ፣አንተ ፣አንቲ፣ አንትሙ፣ አንትን ሲሆኑ) ይነበባል። ምሳሌ ሰበከ ብሎ አነ ሰበኩ ይባላል (ኩ ጠብቃ ትነበባለች) እንጅ አነ ሰበክኩ አይባልም። አነ አጥመቁ ይላል እንጅ አነ አጥመቅኩ አይልም። ስለሆነም ማጥበቅ አለብን።
፪.፩.፪. መራሕያን እንደ ነባር አንቀጽ / verb to be/
ነባር አንቀጽ ሲባል ማሰሪያ ግስ ማለት ነው። መራሕያን በአንቀጽነታቸው እየተተረጎሙ ሲፈቱ ማሠሪያ ይሆናሉ። ይኸዉም፦
ውእቱ = ነው፣ ኾነ፣ ነበረ፣ ኖረ፣ ይኑር፣ ነሽ፣ ነኝ፣ ነኽ፣ ናችሁ፣ ነበራችሁ
ይእቲ = ናት፣ ነበረች
ውእቶሙ(እሙንቱ) = ናቸው፣ ሆኑ፣ ነበሩ፣ ኖሩ፣ ይኑሩ ( ለወንዶች)
ውእቶን(እማንቱ) = ናቸው፣ ነበሩ (ለሴቶች)
አንተ = ነህ፣ ሆንክ፣ ነበርክ፣ ኖርክ፣ ኑር
አንቲ = ነሽ፣ ኾንሽ፣ ነበርሽ፣ ኖርሽ፣ ኑሪ
አንትሙ(ተባዕት) = ናችኹ፣ ኾናችኹ፣ ነበራችኹ፣ ኖራችኹ፣ ኑሩ
አንትን(አንስት) = ናችኹ፣ ኾናችኹ፣ ነበራችኹ፣ ኖራችኹ፣ ኑሩ
ንሕነ = ነን፣ ኾንን፣ ነበርን፣ ኖርን፣ እንኑር
አነ = ነኝ፣ ኾንኩ፣ ነበርኩ፣ ኖርኩ፣ ልኑር
ምሳሌ፦
አነ ውእቱ ጒንደ ወይን = እኔ የወይን ግንድ ነኝ።
አነ ውእቱ ኖላዊ ኄር = እኔ ቸር ጠባቂ ነኝ።
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም= የአዳም /ለአዳም/ ተስፋው አንቺ ነሽ።
አንተ ውእቱ ዕጣን ኦ መድኃኒነ = መድኃኒታችን ሆይ አንተ ዕጣን ነህ።
ማርያም ይእቲ መሠረተ ሕይወት = ማርያም የሕይወታችን መሠረት ናት።
ናሆም ወሚልክያስ ነቢያት ውእቶሙ /እሙንቱ/ = ናሆምና ሚልክያስ ነቢያት ናቸው።
አስቴር ወሶስና ቅዱሳን ውእቶን /እማንቱ/ = አስቴርና ሶስና ቅዱሳን ናቸው።
ውእቱ ለዋጭ ተለዋጭ ባሕርይ ስላለው በተባዕትና በአንስት በብዙና በነጠላ አፈታት ይፈታል። እንዲህ ማለት በነባር አንቀጽነቱ የሚከተሉትን ትርጉም ሊያስገኝ ይችላል። በዐረፍተ- ነገር እየገባ ሲታይ የትኛውን ትርጉም እንደያዘ ዐመሉን ማስተዋል ያስፈልጋል።
ውእቱ = ነው፣ ናት፣ ናቸው /ተ/አ/፤
= ነኽ፣ ነሽ፣ ናችኹ /ተ/አ/ ፤
= ነኝ፣ ነን፣ ይኾናል
ሥርዓተ ዐረፍተ- ነገር በምሳሌ፦
• ቅድስት ይእቲ ኤልሳቤጥ = ኤልሳቤጥ ቅድስት ናት
• ኤልሳቤጥ ቅድስት ይእቲ
• ነቢይ ውእቱ ሕዝቅኤል
• ሕዝቅኤል ነቢይ ውእቱ
ውእቱ ለሚለው አሉታው አኮ /አይደለም/ ነው
ለምሳሌ፦ አኮ ነቢይ ሕዝቅኤል
ተጨማሪ ምሳሌዎች:
አነ ውእቱ ፍኖተ ጽድቅ = እኔ የእውነት መንገድ ነኝ
አንተ ውእቱ ቤዛ ኵሉ ዓለም = አንተ የዓለም ሁሉ ቤዛ ነህ
ጳዉሎስ ወጴጥሮስ መምህራን ውእቶሙ
ሰሎሜ ወኤልሳቤጥ ቅዱሳት ውእቶን
አበዊነ መሀሩነ ልሳነክሙ ወቃለ እግዚአብሔር
በግእዝ የተለያዩ ንባባት አሉ። እነዚህን ለይቶ ለማወቅ እና ጥሩ አንባቢ ለመኾን ወሳኙ መንገድ ከመምህራኑ እግር ሥር ቊጭ ብሎ ደረጃ በደረጃ በድምፅ መማር ነው። ነገር ግን በድምፅ ለመማር ዕድሉ ለሌለው በጽሑፍ ምልክቶችን በመጠቀም ማለማመድ ይቻል እንደኾነ ለመሞከር ያኽል የተዘጋጁ ጥቂት መልመጃዎችን እናቀርባለን። በቅድሚያ ግን ንባባቱን በምሳሌ ጭምር እንወቃቸው።
ንባብ፦
1. ተነሽ = ባብዛኛው የቃሉን ቅድመ-መድረሻ ቀለም ይዞ ተኵሶ (እንደ ቁጣ ቢጤ) ማንበብ ነው
2. ወዳቂ = የቃሉን መድረሻ ቀለም ይዞ አልዝዞ (እንደማላዘን ቢጤ) ማንበብ ነው
3. ተጣይ = ኹሉንም ቀለማት እኩል ማንበብ ነው
4. ተናባቢ = ኹለት ወይም ከዚያ በላይ ቃላትን እንዳንድ ቃል ባንድ ትንፋሽ ማንበብ ነው
5. ሰያፍ = እንደተነሽ ነው ("ቅድመ-መድረሻ" የሚለው ቀርቶ)
6. ማጥበቅ = ቀለሙን አጥብቆ ማንበብ
7. ማላላት = አላልቶ ማንበብ
8. አጎበር = ተነሽ፣ ሰያፍ፣ ተጣይ ንባባትን እንደ ሂ፣ ኒ፣ ሰ፣ ኬ ፣ አ ያሉ ሲከተሏቸው አጎበር ይባላል
ምሳሌ፦
1. ተነሽ፦ ሖረ፣ ቀተለ፣ ባረከ፣ አእመረ፣
2. ወዳቂ፦ ዘ፣ ቀዲሙ፣ ብእሲ፣ ደብተራ፣ ጽጌ፣ ዝ፣ ከበሮ
3. ተጣይ፦ ማርያም፣ ትምህርት፣ መምህር፣
4. ሰያፍ፦ ገብርኤል፣ ኢሳይያስ፣ ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ
5. ተናባቢ፦ ቤተ-ክርስቲያን፣ ሥርዐተ-ቤተ-ክርስቲያን፣ ዕበየ-ክብረ-ስብሐት
6. የሚጠብቅ፦ ሰብሐ (ፍቺው "አመሰገነ" ሲኾን "ብ" ይጠብቃል፤ ይነሣማል)
7. የሚላላ፦ ሠብሐ (ፍችው "ሠባ፣ ወፈረ" ሲኾን ደግሞ "ብ" ይላላል፤ "ሠ"ይነሣል)
8. አጎበር፦ አነኒ፣ አብርሃምሃ (እንደ ወዳቂ)፤ ቀዲሙሰ፣ ይእዜሰ (እንደ ተነሽ)
እነዚህን ንባባት ጠንቅቆ ማወቅ ማናቸውንም በግእዝ የተደረሱ ጽሑፎች በትክክል ለመረዳት አስፈላጊ ከመኾኑ ጋር፤ በቅኔ ቤት እና በዜማ ቤት እንዲኹም በትርጓሜ መጻሕፍት ጉባኤ ለሚቀጥለውም ትምርት መሠረት ነው። ስለኾነም "ሀ" ተብሎ በ"ቊጥር" የሚጀመረውይህ መሠረታዊ የንባብ ትምህርት እስከ"ድጋም" የሚደርሰው የሚከተሉትን ሦስት ደረጃዎች አልፎ ነው፦
1. ግእዝ
2. ወርድ
3. ዐቢይ (ቊም)