Saturday, May 25, 2019

ምን እንጸልይ?


ምን እንጸልይ?
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ርእስ ምን እንጸልይ?
1  ውዳሴ ማርያም
1.     የዘወትር ጸሎት
2.     የዕለ ውዳሴ ማርያም
3.     አንቀጸ ብርሃን
4.     ይዌድስዋ መላእክት
5.     አባታችን ሆይ
2.     መዝሙረ ዳዊት
መዝሙረ ዳዊት ሁሉም ጸሎት ነው፡፡ የየቀኑን መዝሙር ለመጸለይ አከፋፈሉ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
የሰኞ፦ መዝ. 1 – 30
የማክሰኞ፦ መዝ. 31 60
የረቡዕ፦ መዝ.   61 80
የሐሙስ፦ መዝ.  81 110
የዓርብ፦ መዝ.   111 130
የቅዳሜ፦ መዝ.  131 150 መኃል. መኃ. ዘሰሎሞን
የእሑድ፦ ጸሎተ ነቢያት
የየቀኑን ማድረስ ካልተቻለ
በየቀኑ አንድ፤ አንድ ንጉሥ (አሥር፤ አሥር መዝሙራትን) መጸለይ
 ልዩ ጸሎት  መዝ. 118(119)  1 176
አሥር አሥር መዝሙራትን ለማድረስ ካልተቻለ ጊዜ የሌለው ሰው ቢያንስ የሚከተሉትን መርጦ ቢጸልይ መልካም ነው::
መዝሙረ ዳዊት 6
መዝሙረ ዳዊት 12 (13)
መዝሙረ ዳዊት 19 (20)
መዝሙረ ዳዊት 22 (23)
መዝሙረ ዳዊት 24 (25)
መዝሙረ ዳዊት 26 (27)
መዝሙረ ዳዊት 37 (38)
መዝሙረ ዳዊት 50 (51)
መዝሙረ ዳዊት 69 (70)
መዝሙረ ዳዊት 85 (86)
መዝሙረ ዳዊት 90 (91)
መዝሙረ ዳዊት 120 (121)
መዝሙረ ዳዊት 135 (136)
መዝሙረ ዳዊት 140 (141)
መዝሙረ ዳዊት 144 (145)
3.     ጸሎተ ነቢያት
የእስራኤላውያን ምስጋና (ዘጸአት 15 1 19)
የሙሴ ጸሎት (ዘዳግም 32 1 43)
የሳሙኤል እናት የሐና ጸሎት (1 ሳሙ. 1 10)
የምናሴ ጸሎት (2 ዜና መዋ. 33 : 12 13)
የነቢዩ የኢሳይያስ ጸሎት (ኢሳ. 26 1 21)
የንጉሡ የሕዝቅያስ ጸሎት (ኢሳ. 38 10 20)
የነቢዩ የዳንኤል ጸሎት (ዳን. 9 4 19)
የነቢዩ የዮናስ ጸሎት (ዮና. 2 3 11)
ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ (የጸሎት መጻሕፍት)
የሦስቱ ልጆች መዝሙር (የጸሎት መጻሕፍት)
የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት (ዕንባ. 3 1 19)
የድንግል ማርያም ጸሎት (ሉቃ. 1 46 55)
የካህኑ የዘካርያስ ጸሎት (ሉቃ. 1 68 79)
የነቢዩ የስምዖን ጸሎት (ሉቃ. 2 29 32)
ከነዚህ ውስጥ የምናሴ ጸሎት፣ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ፣ የሦስቱ ልጆች መዝሙር የሚሉት የጸሎት መጻሕፍት ውስጥ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም፡፡
4.     ውዳሴ አምላክ
የቀን፤ የቀን ጸሎት ያለው ሲሆን የሚከተሉት የዳዊት መዝሙራት በየቀናቱ መጨረሻ ላይ ይገኛሉ፡፡
መዝሙረ ዳዊት 6
መዝሙረ ዳዊት 24 (25)
መዝሙረ ዳዊት 37 (38)
መዝሙረ ዳዊት 50 (51)
መዝሙረ ዳዊት 69 (70)
መዝሙረ ዳዊት 85 (86)
መዝሙረ ዳዊት 120 (121)
5.       ወንጌል ዘዮሐንስ
ወንጌለ ዮሐንስ ሃያ አንድ ምዕራፎች አሉት፡፡ በሳምንት ለመጨረስ ሦስት፤ ሦስት ምዕራፍ በሦስት ቀን ለመጨረስ ሰባት፤ ሰባት ምዕራፍ ካልተቻለም በየቀኑ አንድ፤ አንድ ምዕራፍ ብቻ ይጸለያል፡፡
6. ሌሎች ጸሎታት
አርጋኖን- የቀን፤ የቀን ጸሎት ያለው ሲሆን የእመቤታችንን ምስጋናና ልመና የያዘ ጸሎት ነው፡፡
ሰይፈ መለኮት፣ሰይፈ ሥላሴ፣የመስቀል አጥር ጸሎት (የየዕለቱ)፣ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል ወገብርኤል (ወሩፋኤል) 
መልክአ መልክእ- መልክአ መድኃኔ ዓለም፤ መልክአ ሥላሴ፤ መልክአ ኢየሱስ፤ መልክአ ማርያም፣ የቅዱሳን መልክአ መልክ፣ . . .
በመጨረሻም አርባ አንድ ኪርያ ላይሶንና እግዚኦታ (ከስግደት ጋር)

እንደ ዓይነተኛ ምሳሌ አንድ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያለ ምእመን የሚያደርሰው ጸሎት
1.     ጧት
1.     የዘወትር ጸሎት
2.     የዕለቱ ውዳሴ ማርያም
3.     ይዌድስዋ መላእክት
4.     ውዳሴ አምላክ የዕለቱን
5.     አርባ አንድ ኪርያ ላይሶንና እግዚኦታ (ከስግደት ጋር) ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ (በ5ቱ ቅንዋተ መስቀል) በእንተ ማርያም መሀረነ ክርስቶስ
6.     አባታችን ሆይ
2.     ማታ
1.     አንቀጸ ብርሃን
2.     የዮሐንስ ወንጌል (አንድ ወይም ሦስት ምዕራፍ)
3.     መዝሙረ ዳዊት (አንድ ወይም 3(ሦስት) መዝሙራት)
4.     አባታችን ሆይ
አንዱ የጸሎት ዓይነት ሲያልቅ ወደሌላው ከመሸጋገር በፊት በአባታችን ሆይ ይዘጋል፡፡
እንደ ጊዜያችን ሁኔታ የጧትና የማታውን ጸሎት ስግደቱንም ጭምር ማሸጋሸግ ይቻላል፡፡
 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል አሜን


ከምግብ በፊት እና በኋላ ምን ብለን እንጸልይ?
ከመመገባችን በፊት ይህንን አባቶቻችን ከመዝሙረ ዳዊት አውጣጥተው ያደረሱትን ጸሎት እናድርስ።
«ለፍጥረታቱ ሁሉ መልካሙን የምትሠጥ አምላካችን እግዚአብሔር አንተ ምስጉን ነህ ስምህም የተመሰገነ ነው። እኛም ስለ ፍጹም ሥጦታህ ፈጽመን እናመሰግንሃለን። የፍጥረት ሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል። አንተ ለሁሉ በጊዜው ምግቡን ትሠጠዋለህና ቀኝህንም ትዘረጋለህ ሁሉንም ታጠግባለህ። አሁንም ልዩ የሆነች ቀኝህን ዘርጋ ይህንን የሠጠኸንን ምግብና መጠጥም ባርክ ለሥጋችንና ለነፍሳችን ኃይልና ብርታት ይሆነን ዘንድ አንተ ቸር ታማኝ መጋቢ ነህና ለዘለዓለሙ አሜን አባታችን ሆይ»
(
«እግዚአብሔ አምላክነ ዘትሁብ ሠናያቲከ ለኩሉ ፍጥረት እኩት አንተ ወስቡሕ ስምከ ወንህነኒ ነአኩተከ ወንሴብሐከ በእንተ ፍጹም ጸጋከ ዓይነ ኩሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ እስመ አንተ ትሁብ ሲሳየ ለኩሎ በጊዜሁ ትሰፍህ የማነከ ወታጸግብ ኩሎ ወይእዜኒ ስፋሕ የማነከ ቅድስተ ወባርክ ዘንተ መብልዓ ወመስቴ ዘአስተዳለውከነ ከመ ይኩነነ ኃይለ ወጽንዓ ጋነ ወነፍስነ እስመ አንተ ኄር ወምእመን መጋቤ ለዓለመ ዓለም አሜን አቡነ ዘበሰማያት»)
ከዚያም እንደየ መዓርጉ ማዕዱን የባረከው ሰው ለሌሎች ቆርሶ «በእንተ ማርያም በእንተ ኢየሱስ» እያለ ይሠጣል። ቀሳውስት ደግሞ  «በረከተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ» እያሉ ሲሰጡ ሰዉ  «ይምጻእ ኀቤየ መንፈስ ቅዱስ» እያለ ይቀበላል። ይህም ጌታችን በኤማሁስ አብረውት ሊበሉ ለተቀመጡት አርድእት እንደሰጣቸው በማየት የተሠራ ሥርዓት ነው።
የመዓድ ጸሎት ትልቁ ጠቀሜታ ሰው ምንም ለጸሎት ጊዜ የለኝም ቢል እንኩዋን ለምግብ ጊዜ አጣሁ ልል ስለማይችል በበላ/በተመገበ ቁጥር እንዲጸልይ ያደርገዋል። በቀን ሦስት ጊዜ የሚበላ ሰው ቢያንስ በቀን ሦስቴ ይጸልያል። አቅሙ ቢችልና ለሥጋውም ሆነ ለነፍሱ ጤና ካልሰጋ በስተቀር አንድ ሰው በቀን ሰባት ጊዜ ቢበላ ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠነቀቀ ማለት ነው። ጥቅሙን ለማስረዳ ይህንን አመጣነው እንጂ ይህ እንኩዋን ለመብላት መጸለይ ሳይሆን
ለመጸለይ መብላት ይሆናል። ከበላን/ከተመገብን በኋላ ስብሐት እንላለን። በምንም ምክንያት ለመብላት ጊዜ እስካለን ድረስ ስብሐት ለማለትም ጊዜ መሥጠት አለብን።
የበላነውን የጤና እንዲያደርግልንና እንዲስማማን እንዳያሳጧን ላጡትም እንዲያድላቸው ማመስገን ይገባል። አንዳንድ ሰዎች «ምግቡ ከተረፈ ስብሐት አንልም ምክንያቱም ስብሐት ብለንበት ለውሻ ሊሠጥ ይችላል የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ይላል።» ይላሉ። ይህ ሃሳብ ግን ብዙ የማያስኬድና አንዳንዴም ለስንፍና ምክንያት ይሆናል።
አንደኛ ስብሐት ከማለታችን በፊት ገና መብላት ስንጀምር ምግቡን በመባረካችን ምግቡ ከመነሻው የተባረከ ነው። ሌላው ስብሐት የምንለው በመብላታችን ፈጣሪን ለማመስገን ነው እንጂ ባለማስተረፋችን አይደለም። የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ የሚለውም ቃል ውሾችን ስላለመመገብ የተነገረ አይደለም።
በደመ ነፍስ የሚኖሩት ምንም የማያውቁት እንስሳትስ ካለ እኛ ማን አላቸው?
ውሾች እኛ ያስተረፍነውን ሊበሉ አይገባም ማለት ከወንጌሉም ሃሳብ ጋር «ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ» ይላልና {ማቴ. 1527} እንዲያውም ከቅዱሳኑ የተማርነው ለውሾች ያስተረፍነውን መከልከል ሳይሆን ያልቀመስነውንም ከላዩ አንስተ መሥጠት እንዳለብን ነው።  ርኅርኅተ ኅሊና እመቤታችን ለውሻ የሰጠችው
እሷ እንኳን ሳትቀምሰው አጉድላ አልነበር?  ጻድቅ ለእንስሳው ነፍስ ይራራል ይልስ የለ?