AsterEyo Mary
AsterEyo does appear, revealing that it is. It āšiteri’āye appeared, appeared from the Semitic verb derived from it. Our Lord and Savior Jesus Christ 's promise of an agreement in accordance with the flesh exposed ( times ) , the unity of šošitinetumi Exposure time since the birthday celebration to call the end of the full- year AsterEyo as is known. Our Lady's Easter break an updated AsterEyo in It is said to be the " mystery Mariam " because it is respected .
ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።
ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ
ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።
ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው ። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።
የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት።
ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው አግችተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል። በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።
ሰአሊ ለነ ቅድስት
የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን። አሜን።
አስተርእዮ ቃሉ የግእዝ ቃል ሲኾን መታየት
መገለጥ ማለት ነው፡፡ ገሃድ የሚለው ቃልም በጾምነቱ ሌላ ትንታኔ ሲኖረው ትርጕሙ ያው መገለጥ ማለት ነው፡፡ በግሪክ
‹‹ኤጲፋኒ›› ይሉታል፡፡ የእኛም ሊቃውንት ቃሉን በቀጥታ በመውሰድ ‹‹ኤጲፋኒያ›› እያሉ በዜማ መጻሕፍቶቻቸው ይጠሩታል፡፡
ትርጕሙም ከላይ ከጠቀስናቸው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አስተርእዮ የሚለው ቃል ‹‹አስተርአየ›› ከሚለው ግሥ ራሱን ችሎ
ሳይለወጥ በአምስቱ አዕማድ የሚፈታ ብቸኛ ግሥ ነው፡፡ ይህም ማለት፡- አስተርአየ፤ ታየ፤ ተያየ፤ አሳየ፤ አስተያየ፤ አየ ተብሎ
ይፈታል ማለት ነው፡፡
ዘመነ አስተርእዮ ሲያጥር ከጥር ፲፩ ቀን እስከ ጥር ፴፤ ሲረዝም ደግሞ ከጥር ፲፩ ቀን እስከ መጋቢት
፫ ቀን ይኾናል፡፡ በዚህም መሠረት ቀናቱ ሲያጥር ፳፤ ሲረዝም ፶፫ ይኾናሉ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ለሐዋርያት ሕጽበተ እግር
ካደረገበት ቀን (ከጸሎተ ሐሙስ) እስከ ጰራቅሊጦስ ቢቈጠር ቀናቱ ፶፫ ስለሚኾኑ የእነዚህ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ዮሐንስ በጥምቀት
ዕለት ለልዕልና (ጌታ ሰውን ምን ያህል እንዳከበረው) ለማሳየት እጁን ከጌታችን ራስ በላይ ከፍ እንዳደረገ ጌታችንም ለትሕትና
እጁን ከሐዋርያት እግር በታች ዝቅ አድርጎ እግራቸውን አጥቧቸዋልና ነው፡፡
ጥምቀት የሕጽበት አምሳል ሲኾን፣ ሕጽበት (መታጠብ) ደግሞ በንባብ አንድ ኾኖ ሁለት ምሥጢራት አሉት፡፡
የመጀመሪያው፡- ምእመናን የእንግዳ እግር እንዲያጥቡ ጌታችን ትምህርት ማስተማሩ ሲኾን፣ ሁለተኛውም ለሐዋርያት ጥምቀታቸው መኾኑ
ነው፡፡ ሐዋርያት በጸሎተ ሐሙስ ቢጠመቁም መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት የጰራቅሊጦስ ዕለት ነውና፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ስለ
ቅዱሳን ሐዋርያት ጥምቀት ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያን እንደ ጠየቀውና ጥምቀታቸው ሕጽበተ እግር መኾኑን እንደ መለሰለት፡፡
በሌላ በኩል ከዘመነ ልደት እስከ ጥምቀት ተወልደ፤ ተሠገወ (ሰው ኾነ) ይባላል እንጂ አስተርአየ
(ተገለጠ) አይባልም፡፡ ከጥምቀት በኋላ ግን አብሮ፣ ተባብሮ ተጠምቀ፤ ተወልደ፤ ተሠገወ፤ አስተርአየ ይባላል፡፡ ከጥምቀት በፊት
አስተርእዮ ለመባሉ በሦስት ነገሮች ነው፡፡ የመጀመሪያው፡- የማይታየው ረቂቅ አምላክ በበረት ተወልዶ፣ በጨርቅ ተጠቅልሎ ቢታይ፤
እንደ ሕፃን ሲያለቅስ ቢሰማም ሰው ዅሉ ሠላሳ ዓመት ሲሞላው ሙሉ ሰው ይኾናል እንደሚባለው፣ አምላክ ነኝ ብሎ በአንድ ቀን
ሳያድግ በጥቂቱ ማደጉንና ስደት እንደ ውርደት ኾኖ እንዳይቈጠር ለሰዎች ስደትን ባርኮ (ጀምሮ) ለመስጠት፤ ሄሮድስም ሊገድለው
ይፈልገው ስለ ነበር ወቅቱ የሚሰደድበት እንጂ የሚታይበት ስላልነበረ ነው፡፡
ሁለተኛው፡- ሰው በተፈጥሮም ኾነ በትምህርት አዋቂ ቢኾን ለሚመለከተው ሥራና ደረጃ እስከ ተወሰነ ጊዜ
ይህ ሕፃን ለእንዲህ ያለ ማዕረግ ይኾናል አይባልም፤ ተንከባክባችሁ አሳድጉት ይባላል እንጂ፡፡ ሕፃኑ አዋቂ ነው አይባልም፤
ያውቃል ተብሎም ለትልቅ ደረጃ አይበቃም፡፡ በየትኛውም ሓላፊነት ላይ አይሰጥም፤ ራሱን በመግዛት ይጠበቃል እንጂ፡፡ ጌታችንም በመንፈስም
በሥጋም ባለ ሥልጣን ቢኾንም ፍጹም ሰው ኾኗልና አምላክ ነኝ፤ ዅሉን በዕለቱ ልፈጽም ሳይል በየጥቂቱ ማደጉን እናያለን፡፡
የሰውን ሥርዓት ከኀጢአት በቀር ለመፈጸም
በየጥቂቱ አደገ፡፡ ‹‹በበሕቅ ልሕቀ›› እንዲል፡፡ ሰው ዅሉ ፴ ዓመት ሲኾነው
ሕግጋትን ለመወከል፣ ለመወሰን እስከ ፴ ዓመት መታገሡም ስለዚሁ ነው፡፡ ከሠላሳ ዓመት በኋላ ሰው ቢመቸው ይወፍራል፤ ቢከፋው
ይከሳል እንጂ ቁመት አይጨምርም አይቀንስም፡፡ ጌታችን ሰው ሙሉ፣ አእምሮው የተስተካከለለት ጐልማሳ በሚኾንበት ዕድሜ በ፴ ዓመት
በግልጽ በመታየቱ ወቅቱ ‹‹ዘመነ አስተርእዮ›› ተብሏል፡፡
ሦስተኛው፡- በ፴ ዓመት እርሱ ሊጠመቅበት ሳይኾን የመጀመሪያ መንፈሳዊ ሕግና ሥርዓት መሠረት የኾኑ
ጥምቀትንና ጾምን ሠርቶ በመሳየትና መመሪያ አድርጎ ለምእመናን በመስጠት እሱ ሙሉ ሰው ኾኖ ተገልጾ የቃሉን ትምህርት ለመስማት፤
የእጁን ተአምራት ለማየት ይከተለው ለነበረው አምስት ገበያ ያህል ሕዝብ ትምህርት፣ ተአምራት ያደረገበት፤ ሥራዬ ብሎ
የመጣበት መንፈሳዊ ሕግና ሥርዓት የፈጸመበት ዘመን በመኾኑ ነው፡፡ የታየውም ወልድ ብቻ አይደለም፤ አብ ‹‹ይህ የምወደው ልጄ
ነው›› ሲል፤ መንፈስ ቅዱስም በእርግብ አምሳል ሲወርድ ረቂቁ አምላክ የታየበት፤ የሥላሴ የአንድነትና ሦስትነት ምሥጢር
የተገለጠበት ዕለት ስለ ኾነ ይህ ወቅት ዘመነ አስተርእዮ ተብሏል፡፡
በአስተርእዮ ሌሎች በዓላትም ይጠሩበታል፡፡
ለምሳሌ ድንግል ማርያም ጥር ፳፩ ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት ለጻድቃን እና ለመላእክት
በሰማይና በምድር የተሰጣት ጸጋ፣ ክብር የተገለጸበት ዕለት ስለኾነ በዓሉ ‹‹አስተርእዮ ማርያም›› ይባላል፡፡ የኢትዮጵያ
ሊቃውንት በዚህ ቃል ሐሳባቸውን ያስተባብራሉ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ አምላክ በሥጋ ከድንግል መወለዱንና በዚህ አካለ መጠንም ለዓለም
መገለጡን አስተርእዮ ብሎ ሲናገር፤ አባ ጽጌ ብርሃን ደግሞ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ ‹‹እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት ለቢሶ ሥጋኪ ሥጋ ዚአነ፤ አመ አስተርአየ በምድር ወተአምረ ለነ፤ ንዌድሰኪ እንዘ ንብል ምክሐ ዘመድነ፤ ዮም በፍሥሓ ለማርያም እምነ፤ አስተርእዮ በሰማይ ኮነ፡፡ – የትንቢት አበባ እግዚአብሔር የእኛ ሥጋ የኾነውን የአንቺንሥጋ ለብሶ ለእኛ እንዲታወቅ በምድር እንደ ተገለጠ፤ የወገናችን መመኪያ ድንግል ሆይ፣ ‹ዛሬ ለእናታችን ለማርያም በሰማይ ፍጹም በደስታ መገለጥ ኾነ› እያልን እናመሰግንሻለን፤›› ሲል
ገልጾታል፡፡ ነቢዩ ዳዊትም፡- ‹‹በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ፤ በነቢያት ይወለዳል ሲባል የሰማነው በበረት ተጥሎ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግዕዘ ሕፃናት ሲያለቅስ ሰማነው፡፡ በዮርዳኖስ ሲጠመቅአየነው፤›› በማለት የአምላካችንን መገለጥ
ተናግሯል /መዝ.፵፯፥፮/፡፡