Wednesday, December 4, 2019

አቡነ ዘበሰማያት ጸሎት

በእንተ ጸሎት


አንትሙሰ ሶበ ትጼልዩ ከመዝ በሉ
አብዝታችሁ አትጸልዩ ብሎ ነበርና አጭር ጸሎት ጩኸችሁ አትጸልዩ ብሎ ነበርና የሕሊና ጸሎት ሲቆሙ ሲቀመጡ ሲተኙ ሲነሱ የሚጸልትን ጸሎት አስተማራቸው፡፡

አቡነ

በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ አቡነ በሉኝ አለ አምላክነ እግዚእነ መምህርነ በሉኝ አላለም፡፡ ቀድሞ ነቢያት ከግብርናተ ዲያብሎስ አልወጣንም ሲሉ አምላክነ እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ እኛ ግን ከግብርናተ ዲያቢሎስ ነጻ ወጥተናልና አባት ሆይ በሉኝ አለ፡፡ መምህር ደቀ መዝሙሩን ሲወድ ያበላዋል ያጠጣዋል የልቡን ምሥጢር ያጫውተዋል እንጂ ርስቱን አያወርሰውም፡፡ እርስቱን የሚወርስ ልጁ ነው፡፡ እርሱ ግን የማታልፈውን ርስት መንግስተ ሰማያት ያወርሰናልና አቡነ በሉኝ ብሏል፡፡ አባት ለልጁ እንደሚራራ የሚራራ መሆኑን ለመግለጽ

ዘበሰማያት


ዘበሰማያት(በሰማይ የምትኖር) አለ ከምድራዊ አባት ሲለይ በምድር ላይ ብዙ አባቶች አሉን፡፡ ለአብነትም ወላጅ አባት የቀለም አባት የቆብ አባት የምንላቸው ምድራዊያን አባቶች ናቸው እርሱ ግን ሰማያዊ ነውን ከዚህ ሲለይ ምድራዊ አባት ሲወልድ በግዘፍ ነው ሲያሳድግም በግዘፍ ነው በኋላ ኃላፊ ጠፊ ርስቱን ያወርሳል፡፡  ኋላ ሞትን ያስከትላል፡፡ እርሱ ግን ሲወልደን በረቂቅ ሲያሳድገንም በረቂቅ ነው፡፡ኋላም የማታልፍ መንግስቱን ርስታችንን መንግስተ ሰማያትን ያወርሰናል፡፡ ኋላ እንደመላእክት ሕያውነት ያስከትልልናልና፡፡ ጌታ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን ስለ ልዕልናው በሰማይ አለ ይባላልና፡፡ የክብሩ የልዕልናውን ለመግለጽ ጸሎቱም በሰቂለ ኅሊና ይሁን ሲል እንዲህ አለ፡፡

ይትቀደስ ስምከ

ስምህ ይቀደስ ሲል ምን ማለቱ ነው?  ስመ ወላዲ፣ ስመ ተወላዲ፣ ስመ ሠራፂ ይለይልን በሉ ስል ነው ስሜ መሐሪና ይቅር ባይ ነው ያልኸው ይድናልን በሉኝ እንደ መላእክት ቅዱስ ቅዱ ቅዱስ ብለን አመሰግነንህ ቅድስናህን ተስፈን እንድኖር አድርገን በሉኝ ሲል ነው ቅድስናህን ተሳትፈን እንድኖር አድርገን በሉኝ ሲል ነው

ትምጻእ መንግሥትከ

መንግሥትህ ትመጣ
መንግሥትህ ትምጣ ሲል ምን ማለቱ ነው ከወዲያ ያለች ከወዲህ የሌለች ሆና ከወዲያ የሌለች ሁና ከወዲህ ወዲያ የምትሄድ ሆና አይደለም፡፡ መንግሥተ ሰማይ ትምጣልን በሉኝ ስል ነው፡፡ መንግሥተ ሰማይ ትገልጥልን ቢሉኝ ስል ነው፡፡ልጅነት ትስጠን በሉኝ ሲል ነው

ወይኩን ፍቃድከ በከመ በሰማይ

ፈቃድህ በምድርም ትሁን ማለቱ መላእክት በሰማይ ሊያመሰግኑህ ፈቃድህ እንደሆነ እኛም እናመሰግናለህ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን ኋላ ሞቱን ተነስተን ልናመሰግን ፈቃድህ እንደሆነ ዛሬም በሕይወት ሥጋ ሳለን እንመሰግንህ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፡፡

ከማሁ በምድር ሲሳይነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም

የዕለት ዕንጀራችንን ዛሬ ስጠን
የዕለት ዕንጀራ የተባለ ምንድን ነው?
አንደኛ የዕለት ምግብ (ለፍጹማን) ሁለተኛ የመት ልብስ ያመት ምግብ (ለሰብአ ዓለም) ሦስተኛ ሥጋህን ደምህን፣ ንሰሐን፣ ትምህርትን አስቦ ጸሎታችንን ስጠን  እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን


ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንህነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ

የበደሉንን ይቅር እንደምንል ይቅር በለን
ይቅር እንድምንል ሲል ምን ማለቱ ነው? የበደለንን ይቅር እንል ዘንድ ይህማ ማስተካከል አይሆንም ቢሉ አይሆንም ሰው ይቅር ማለቱ እግዚአብሔር ይቅር ይለኛል ሲል ነው፡፡ ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትል የሰማዩ አባታችሁ እናንተ ደግሞ ይቅር ይላችኋልና ይቅር ይላችሁ ዘንድ ይቅር በሉ ማለት ነው ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ አባታችም ኃጢአታችን ይቅር አይላችሁም ይላቸዋልና ለትምህርቱ መነሻ ነው፡፡አንድም ይቅር ማለቱ ራሱ ያላንተ ፈቃድ አይሆንም ስል ነው፡፡ ሰው የያለ እግዚአብሔር ፍቃድ ይቅር ይል ዘንድ አይቻለውና

ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት እስመ ዚአከ ይእቲ መንግስት

ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈታን አታግባን መንግስተ ሰማያት ያንተ ናትና
አቤቱ ወደ ክህደት ወደ ኃጢአት ወደ መከራ ወደ ገሃነም አታግባን፡፡ ከመከራ ከገሃነም ከኃጢአት ከክህደት አድነን እንጂ መንግስተ ሰማያት ያንተ ናትና መንግስተ ሰማያት ገንዘብህ ናትና

ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም አሜን

 ከሃሊነት ጌትነት ለዘለዓለሙ ገንዘብህ ናትና አሜን በእውነት

በዚህ አጭር የኅሊና ጸሎት ላይ ምን ምን አለበት?

፭ ነገሮች አሉበት እነሱም
፩. ሃይማኖት- በዓይን ያላዩትን በእጅ ያልዳሰሱትን ያለይቱን እግዚአብሔርን አባታችን ማለት ሃይማኖት(እምነት)እንጂ
፪. ተስፋ- መንግሥትህ ትመጣ ማለት
፫. ፍቅር - ለኛ ብሎ አንዱ ለአንዱ መጸለይ
፬. ትኅትና - ቅዱሳን ከበቁ በኋላ በደላችንን ይቅር በለን ማለት
፭. ጸሎት - መላው (ጠቅላላ ይዘቱ)

Special website https://github.com/geezorg/ebooks/commit/afc0d4e7dcb57a309b4e4f0bb8f6199fb2241152

የፍለጋ ውጤቶች

ስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments: