ክርስቶስን ይዞ ሞት፣ ድንግል ማርያምን ይዞ እፍረት የለም።
ዓለም ያለ ድንግል ማርያም ምልጃ አትድንም።
Tuesday, December 18, 2018
ግእዝ
ግእዝ
የአብነት
ትምህርት
ቤቶች
ግዕዝ
ቤተ ክርስቲያን
ባለፈችበት
የረጅም
ዓመታት
ዕድሜ
ብቸኛ
የትምህርት
ማዕከል
ሆነው
የኖሩት
የአብነት
ትምህርት
ቤቶች
ናቸው፡፡
አባቶቻችን
ከፊደል
ጀምሮ
ዳዊት
ደግመው
ዜማውን፣
ቅኔውን፣
ትርጓሜውን
ወዘተ
…
ተምረው
ቤተክርስቲያንን
በማገልገል
ላለንበት
ዘመን
አድረሰውልናል፡፡
በእነዚህ
የአብነት
ትምህርት
ቤቶች
የሚሰጡትን የትምህርት
ዓይነቶች
በዝርዝር
እናያለን፡፡
የፊደል
ትምህርት
ፊደል
ጻፍ
ከሚለው
የግእዝ
ቋንቋ
የመጣ
ሲሆን
ጽሑፍ
ማለት
ነው፡፡
የፊደል
ስልት
በሕገ
ልቦና
ከነበሩ
አባቶች
መካከል
በሄኖክ
ዘመን
እንደተገለጸለት
ቤተክርስቲያን
ታስተምራለች፡፡
ፊደል
የምሥጢር
መመልከቻ፣
የጥበብ
ሁሉ
መነሻ፣
ወደ
እውቀት
መንገድ
ጠራጊ፣
የእውቀት
ሁሉ
ምንጭ
ነው፡፡
“
ኢተወልደ
መጽሐፍ
ዘእንበለ
ፊደል
”
እንዲል፤
ቤተክርስቲያን
የምትጠቀምበት
ፊደል
ትርጉም
አለው፡፡
ለምሳሌ፡
-
ሀ
-›
ብሂል
ሀልዎቱ
ለአብ
እምቅድመ
ዓለም፣
የአብ
አኗኗሩ
ከዓለም
በፊት
ነው፡፡
ለ
-›
ብሂል
ለብሰ
ሥጋ
እምድንግል፣
ክርስቶስ
ከድንግል
ሥጋን
ለበሰ
ሐ
-›
ብሂል
ሐመ
ወሞተ፣
ታመመ
ሞተ
ፊደላት
ራሳቸው
መልክዓ
ቁጥር
አላቸው
ብዛታቸው
7
ናቸው፡፡
ሀ
-
ግእዝ
-
አንደኛ
ሁ
-
ካዕብ
-
ሁለተኛ
ሂ
-
ሣልስ
-
ሦስተኛ
ሃ
-
ራብዕ
-
አራተኛ
ሄ
-
ኃምስ
-
አምስተኛ
ህ
-
ሳድስ
-
ስድስተኛ
ሆ
-
ሳብዕ
-
ሰባተኛ
ከፊደል
ትምህርት
ጋር
አቡጊዳ
የጽሕፈት
ትምህርት
አብሮ
ይጠናል፡፡
የንባብ
ትምህርት
ከፊደል
ቀጥሎ
የሚሰጥ
የአብነት
ትምህርት
ንባብ
ነው፡፡
የንባብ
ትምህርት
መለያ
ተብለው
የተወሰኑ
የቤተክርስቲያን
መጻሕፍት
አሉ፡፡
ለምሳሌ
መልዕክተ
ዮሐንስ፣
ወንጌላት፣
ድርሳናት፣
አርጋኖን፣
ውዳሴ
አምላክ፣
ስንክሳር፣
መጽሐፈ
አርድእት
በመጨረሻም
ዳዊት
ነው፡፡
የንባብ
ዓይነቶች
ሦስት
ናቸው
እነርሱም
ሀ
.
የግእዝ
ንባብ
(
ማጋዝ
)
፡
-
መጻሕፍትን
ሲያነብ
ፊደሎችን
በመቁጠር
ያነባል፡፡
ለንባብ
ዳዴ
እንደማለት
ነው፡፡
ለ
.
ውርድ
ንባብ
(
ንዑስ
)
፡
-
ይህ
ዜማ
ያለው
ነው፡፡
የኀዘን
መልክ
ያለው
ስለሆነ
ለምሳሌ
ያህል
የዕለተ
ስቅለት
ዲያቆኑ
የሚያነበው
ይህን
ንባብ
ነው፡፡
ሐ
.
ቁም
ንባብ
(
ዐቢይ
)
፡
-
ይህ
ንባብ
ተነሽ፣
ሰያፍ፣
ወዳቂ፣
ተጣይ
ብሎ
የሚያመለክት
ሲሆን
ያለምልክት
ማንኛውም
መጽሐፍ
ማንበብ
እንዲችል
የሚያስችል
የንባብ
ክፍል
ነው፡፡
የሃይማኖት
ትምህርት
ኢትዮጵያዊያን
ከሃይማኖት
ውጪ
ሆነው
አያውቁም
በስድ
ንባብ፣
በግጥም
መልክ፣
በጥያቄና
መልስ
መልክ
ይጠና
ነበር፡፡
ለምሳሌ
፩
ሥነ
ፍጥረት፡
-
22
ቱን
ሥነፍጥረት
፪
አሥርቱ
ቃላተ
ኦሪት፡
-
እግዚአብሔር
ለሰው
ልጆች
የሰጠውን
የመጀመሪያ
ሕግ
፫
ስድስቱ
ቃላተ
ወንጌል፡
-
የኦሪትን
ሕግ
የሚያጸኑ
እምነትን
ፍጹም
የሚያደርጉ
፬
አዕማደ
ምሥጢር፡
-
የቤተክርስቲያን
የእምነት
ምሶሶ
ሆነው
የምእመናንን
ልብ
በኑፋቄ
በክሕደት
እንዳይናወጹ
አጽንተው
የሚይዙ
ናቸው፡፡
እነዚህም፡
-
ምሥጢረ
ሥላሴ፣
ምሥጢረ
ሥጋዌ፣
ምሥጢረ
ጥምቀት፣
ምሥጢረ
ቁርባን፣
ምሥጢረ
ትንሳኤ
ሙታን
ናቸው፡፡
፭
ምግባረ
ሠናይ
ትምህርት፡
-
ይህ
የሲራክና
የሰሎሞን
ምሳሌ
ላይ
ያሉ
ምክሮችን
በመጠቀም
በግብረ
ገብነት
እንዲያድጉ
የሚያደርግ
ነው፡፡
የቃል
ትምህርት
የቃል
ትምህርት
ማለት
መጽሐፍ
ተመልክተውም
ሆነ
ሳይመለከቱ
መምህሩ
በቃል
የሚናገሩትን
ተማሪው
በመቀበል
በቃል
ብቻ
የሚጠና
ትምህርት
ነው፡፡
በቃል
ትምህርት
ከሚጠኑት
መካከል፡
-
ጸሎት
ዘወትር፡
-
በስመ
አብ
ወወልድ
ወመንፈስ
ቅዱስ
አሐዱ
አምላክ
የሚለው
የጸሎት
መጀመሪያ
ነው፡፡
ነአኩተከ
እግዚኦ
ወንሴብሐከ፡
-
ይህ
ትምህርት
ልዩ
ምስጋና
የያዘ
ነው፡፡
አቡነ
ዘበሰማያት፡
-
ጌታችን
ኢየሱስ
ክርስቶስ
ያስተማረው
ነው፡፡
በሰላመ
ቅዱስ
ገብርኤል
መለአክ፡
-
ቅዱስ
ገብርኤል
ለእመቤታችን
የተናገረው
ቃል
ነው፤
ከሉቃስ
ወንጌል
ላይ
የተውጣጣ
ነው፡፡
ጸሎተ
ሃይማኖት፡
-
ይህ
ጸሎት
318
ሊቃውንት
በጉባኤ
ኒቂያ
አርዮስን
ካወገዙ
በኋላ
የደነገጉት
ጸሎት
ነው፡፡
ቅዱስ
ቅዱስ
ቅዱስ
እግዚአብሔር፡
-
ይህ
ጸሎት
የሥላሴን
ሦስትነትና
አንድነት
የምንመሰክርበት
ሲሆን
በኢሳ
6
፡
3
ተጽፎ
እናገኘዋለን፡፡
ስብሐት
ለአብ፡
-
ይህ
እግዚአብሔርን
በጸሎት
የምናመሰግንበትና
ከምግብ
በኋላ
የምንጸልየው
ጸሎት
ነው፡፡
ሰላም
ለኪ፡
-
የእመቤታችን
የድንግል
ማርያምን
ምስጋናና
አማላጅነት
የሚያስቀምጥ
ጸሎት
ነው፡፡
ጸሎተ
እግዝእትነ
ማርያም፡
-
ይህን
ጸሎት
የደረሰችው
እመቤታችን
ድንግል
ማርያም
ናት፤
ሉቃ
1
፡
-46-53
፡፡
ውዳሴ
ማርያም፡
-
የቅድስት
ድንግል
ማርያም
ምስጋና
ማለት
ነው፡፡
የዚህ
ጸሎት
ደራሲ
ሶሪያዊው
ሊቅ
ቅዱስ
ኤፍሬም
ነው፡፡
በመጀመሪያ
በግጥም
መልክ
የተደረሰ
ሲሆን
ሲተረጎም
ግን
ግጥምነቱን
አጥቷል፡፡
ቅዱስ
ያሬድ
ለዜማ
ማሸጋገሪያ
ይሆን
ዘንድ
በ
64
ሰአሊ
ለነ
ቅድስት
ከፋፍሎታል፡፡
እመቤታችን
ድንግል
ማርያም
በዚህች
ምድር
የኖረችበት
ዕድሜ
ነው፡፡
አንቀጸ
ብርሃን፡
-
የብርሃን
በር
ማለት
ሲሆን
ደራሲው
ቅዱስ
ያሬድ
ነው፡፡
ቁጥሩም
12
ነው፡፡
መልክዓ
መልክ፡
-
የቃሉ
ትርጉም
የአንዱን
ቅዱስ
ከራስ
ጠጉሩ
እስከ
እግር
ጥፍሩ
እንዲሁም
ንዋየ
ውስጡን
በመዘርዘር
የሚቀርብ
ምስጋና
ማለት
ነው፤
ድርሰትነቱም
የኢትዮጵያውያን
ነው፡፡
የዜማ
ትምህርት
የዜማ
ቃል
ትምህርት
መጀመሪያ
ውዳሴ
ማርያም፣
መስተጋብዕ፣
አርባእት
አርያም፣
ሠለስት፣
ክሥተት፣
መወድስ፣
እንዲሁም
ስብሐተ
ነግህ
በአጠቃላይ
የዜማ
ቃል
ትምህርቶች
ናቸው፡፡
የቅዱስ
ያሬድ
የዜማ
ዓይነቶች
3
ናቸው
እነርሱም
ግዕዝ፣
ዕዝል፣
አራራይ
ሲሆኑ
በቅዱስ
ያሬድ
የተደረሱ
መጻሕፍት
አምስት
ሲሆኑ
እነርሱም
የሚከተሉት
ናቸው፡፡
ምዕራፍ፡
-
ማረፊያ
ማለት
ነው፡፡
በዜማ
ቤት
በመላ
ሰላም
ለኪ
ብሎ
ጀምሮ
የጾም
ምዕራፍ
እስኪፈጸም
ድረስ
ያለውን
ነው፡፡
ድጓ፡
-
ረቂቅ
ማለት
ነው፡፡
የዓመቱ
ሙሉ
መዝሙራት
ተወጣጥተው
ተሰብስበው
ይገኙበታል፡፡
በአራት
ክፍሎች
የተከፈለም
ሲሆን
ዮሐንስ፣
አስተምህሮ፣
ጾመ
ድጓ፣
ፋሲካ
ይባላሉ፡፡
ጾመ
ድጓ፡
-
ይህ
ክፍል
የሚዘመረው
በዓቢይ
ጾም
ብቻ
ነው፡፡
‹‹
ይትባሃል
››
በዚህ
ጊዜ
ይህ
ይባላል
እንደማለት
ነው፡፡
ዝማሬ፡
-
ዘመረ
ከሚለው
የግእዝ
ግስ
የወጣ
ሲሆን
አመሰገነ
ማለት
ነው፡፡
ቅዱስ
ያሬድ
ይህን
ድርሰት
አምባ
ከተባለ
ቦታ
ደርሶት
3
ዓመት
አስተምሮታል፡፡
መዋሥዕት፡
-
ለሙታን
የሚደረግ
የፍትኃት
ጸሎት
ነው፡፡
ይህ
ዜማ
በዓመት
አንድ
ጊዜ
በቀዳም
ሥዑር
ዕለት
በፍትሐት
መልክ
ይዘመራል፡፡
አቋቋም፡
-
የመቆም
ሥነ
-
ሥርዓት
የአቋቋምን
ልክ
መልክ
የሚናገር
ትምህርት
ማለት
ነው፡፡
ማኅሌት፡
-
ኀለየ
ዘመረ
ከሚለው
ግሥ
የወጣ
ሲሆን
የምስጋና
መዝሙር
ማለት
ነው፡፡
በዕለተ
እሑድ
በወርና
በዓመት
በዓላት
የሚደረግ
አገልግሎት
ማኅሌት
ይባላል፡፡
ቅዳሴ፡
-
የቅዳሴ
መጻሕፍት
በየጊዜው
የተደረሱ
ሲሆን
ዜማውን
ግን
የደረሰው
ቅዱስ
ያሬድ
ነው፡፡
በቅዳሴ
ውስጥ
ግብረ
ዲቁና፣
ሰዓታት፣
መዝገበ
ቅዳሴ
(14
የቅዳሴ
ዓይነቶች
)
በጠቅላላ
ይገኙበታል፡፡
የግእዝ
ትምህርት
የግእዝ
ትምህርት
የቤተክርስቲያን
የመግባቢያ
ቋንቋ
ነውና
ተማሪው
ግስን
ከነ
አገባቡ
የነጠላ
ድርብ
ግስ
መርኃያንን
የግስ
እርባታን
ቁጥርን
ይህን
በደንብ
በቃሉ
ያጠናል፡፡
ቅኔ
ቅኔ
ማለት
የምስጋና
ግጥም
ማለት
ነው፡፡
የቅኔ
ደራሲ
ቅዱስ
ያሬድ
እንደሆነ
ሊቃውንት
ይስማማሉ፡፡
ድጓውም
የተደረሰው
በቅኔ
ነው፡፡
የቅኔ
ዓይነቶች
ከጉባኤ
ቃና፣
መወድስ፣
እጣነ
ሞገር
የመሳሰሉት
ናቸው፡፡
የመጻሕፍት
ትርጓሜ
ለቤተክርስቲያን
አገልግሎት
የሚውሉ
ብዙ
መጻሕፍት
ሊቃውንት
ሲተረጉሙ
የትርጓሜ
ስልት
አብሮ
ወደ
አገራችን
ገብቷል፡፡
ሦስት
ዓይነት
የትርጓሜ
ዓይነቶች
አሉ፡፡
እነርሱም፡
-
፩
የአንድም
ትርጓሜ
፪
የነጠላ
ትርጓሜ
፫
የምሥጢር
ትርጓሜ
ናቸው፡፡
በመጻሕፍት
ትርጓሜ
ቤት
የሚገኙ
ጉባኤያት
-
መጻሕፍተ
ብሉያት፡
-
ይህንን
የብሉይ
መጽሐፍ
ያወቀ
መጋቤ
ብሉይ
ይባላል፡፡
W
መጻሕፍተ
ሐዲሳት፡
-
በጉባኤ
መልክ
በ
3
ይከፈላል፡፡
ወንጌል፣
የጳውሎስ
መልእክት፣
ሌሎች
አጠቃላይ
እነዚህ
እያንዳንዳቸው
በዓመት
ሁለት
ጊዜ
ይዘለቃሉ፡፡
እነዚህን
ተምረው
ያጠናቀቁ
መጋቤ
ሐዲስ
ይባላሉ፡፡
W
መጻሕፍተ
ሊቃውንት፡
-
የሚባሉት
ፍትሐ
ነገሥት፣
ቄርሎስ፣
ዮሐንስ
አፈወርቅ፣
ሃይማኖተ
አበው፣
መጻሕፍተ
ቅዳሴያት
ሌሎችም
ወዘተ
…
ናቸው፡፡
W
መጻሕፍተ
መነኮሳት፡
-
ለብቻው
አንድ
ጉባኤ
ተብሎ
ይጠራል፡፡
ከመጸሐፈ
ሐዊ
እና
ከስንክሳር
የተውጣጣ
የቅዱሳንን
ሕይወት
የሚያሳይ
ነው፡፡
በውስጡ
አረጋዊ
መንፈሳዊ፣
ማር
ይስሐቅ
ፊልክሲስዩስ
.
የሕግ
ትምህርት
ሕግ
ማለት
ሐገገ
ሕግ
ሠራ
ከሚለው
ግስ
የወጣ
ሲሆን
መወሰን
መግታት
ማለት
ነው፡፡
የሕግ
መጻሕፍት
የሚባሉት
ኦሪታዊ
ህግ፣
ቀለሜንጦስ
ሕግ፣
ሲኖዶስ፣
ቀኖና
አቡሊድስ፣
ዲዲስቅልያ፣
ፈውሰ
መንፈሳዊ፣
ፍትሐ
ነገሥት
ወዘተ
…
ናቸው፡፡
የቁጥር
ትምህርት
የዘመን
አቆጣጠር
በተመለከተ
በልዩ
ስልት
ልዩ
ስፍረ
ሰዓት
መኖሩ
ነው፡፡
የዘመን
አቆጣጠርን
በተመለከተ
መጻሕፍት
ተጽፈዋል፡፡
እነርሱም፡
-
አቡሻክር፣
መርሐ
ወር፣
ባሕረ
ሐሳብ
ናቸው፡፡
አጠቃላይ
በአብነት
ትምህርት
ቤት
ውስጥ
የሚሰጡትን
የትምህርት
ዓይነቶች
አይተናል፡፡
በአሁን
ጊዜ
ግን
ያለው
ነባራዊ
ሁኔታ
እንደሚያሳየው
ደግሞ
ረጅም
ዓመታት
የአብነት
ትምህርት
ቤቶች
ከመማር
ይልቅ
በአጭር
ጊዜ
ዘመናዊ
ትምህርት
ተምሮ
የተሻለ
ሥጋዊ
ኑሮ
መምራት
የሚያስችል
በመሆኑ
በገጠር
የሚኖሩ
ካህናትና
ሊቃውንተ
ቤተክርስቲያን
የሚደረግላቸው
ድጋፍ
አነስተኛ
በመሆኑ
ወደ
ከተማ
እየተሰደዱ
ነው፡፡
አብነት
ትምህርት
ቤቶች
በተማሪና
በአስተማሪ
እጦት
ቁጥራቸው
እየተመናመኑ
መምጣታቸው
እውነት
ነው፡፡
እነዚህ
የአብነት
ትምህርት
ቤቶች
ከከተማ
በጣም
ርቀው
በገጠር
አካባቢዎች
መገኘታቸው
አስታዋሽ
እንዲያጡ
ዓይነተኛ
ምክንያት
ነው፡፡
በዚህ
ሁኔታ
የሚቀጥል
ከሆነ
ለነገይቱ
ቤተክርስቲያን
ተረካቢ
ካህናት
የማግኘቱ
ጉዳይ
አስጊ
ይመስላል፡፡
እነዚህን
ትምህርት
ቤቶች
ማጠናከር
ለነገ
የሚባልም
ጉዳይ
አይደለም፡፡
በዚህም
ሰንበት
ትምህርት
ቤቶች
በማጠናከር
ሕፃናትና
ወጣቶችን
በማስተማር
ለአብነት
ትምህርት
ቤቶች
ድጋፍ
እንዲያደርጉ
መምህራንንና
ተማሪዎችን
እንዲንከባከቡ
ማድረግ
ተገቢ
ነው፡፡
በከተማ
ያሉ
ሰንበት
ትምህርት
ቤቶች
በአደረጃጀታቸው
ውስጥ
የአብነት
ትምህርት
ቤቶችን
ዋነኛ
ክፍል
በማድረግ
ብዙ
ካህናትን
በማፍራት
ከፍተኛ
የትውልድ
አደራ
አለባቸው፡፡
በገጠር
አካባቢዎች
የሚገኙትንም
በጸሎት
በገንዘብ
በማቴሪያልም
መርዳት
ማገዝ
ይገባል፡፡
ሰንበት
ትምህርት
ቤታችን
ውሉደ
ብርሃን
ይህን
በማሰብ
የአብነት
ትምህርትን
ጥቅም
በመገንዘብ
በክፍል
ደረጃ
በማዋቀርና
አስተማሪ
በመቅጠር
ከሁለት
ዓመት
በፊት
የአብነት
ትምህርት
መስጠት
ጀምሯል፡፡
ትምህርቱ
በሁለት
ተከፍሎ
ለሕፃናትና
ለወጣቶች
የሚሰጥ
ሲሆን
ወደ
65
የሚሆኑ
ተማሪዎች
በመማር
ላይ
ይገኛሉ፡፡
የሚሰጡት
የትምህርት
ዓይነቶች፡
-
Ø
የቃል
ትምህርት
Ø
የንባብ
ትምህርት
Ø
የዜማ
ትምህርት
ናቸው፡፡
ትምህርቱ
የሚሰጥበት
ሰዓት፡
-
ለሕፃናት
ሰኞ፣
ረቡዕ፣
ዓርብ
ከ
11
ሰዓት
እስከ
ምሽቱ
1
ሰዓት
ለወጣቶች
ሰኞ፣
ረቡዕ፣
ዓርብ
ከ
ምሽቱ
1
ሰዓት
እስከ
ምሽቱ
3
ሰዓት
ማክሰኞ፣
ሐሙስ፣
ቅዳሜ
እሑድ
ከ
ምሽቱ
2
ሰዓት
እስከ
ምሽቱ
3
ሰዓት
“
የተወደዳችሁ
ምእመናን
የእኛነታችን
መለያ
የሆነውን
የቤተክርስቲያን
ሃብት
የሆነውን
የአብነት
ትምህርት
እንወቅ
እንማር
”
መፅሐፍ
Newer Post
Older Post
Home