Monday, December 31, 2018

የልሳነ ግእዝ ተከታታይ ትምህርት


መጠይቃውያን ቃላት
, መኑ ማን Who?
መነ ማንን who?
እለ መኑ እነ ማን ?
ጥያቄ
ምሳሌ  
መኑ ውእቱ ስምከ? ስምህ ማነው?
መኑ ይትበሀል ስምከ ስምህማን ይባላል?
መኑ ይትበሀል ስምኪ ስምሽ ማን ይባላል?
መኑ ወለደከ/ ማን ወለደህ/
መኑ ፈጠረከ/ ማን ፈጠረህ/
መኑ ይትበሀል አቡከ/ አባትህ/ ማንይባላል
መኑ ትትበሀል እምከ/ እናትትህ/ ማን ትባላለች
መኑ መጽአ ናሁ አሁን ማን መጣ
መኑ ሖረ ናሁ አሁን ማን ሄደ
መኑ ወእቱ ስምክሙ/ክን ስማችሁ ማን ነው
እለ መኑ ወእቶሙ እሉ አርድእት አነዚህ ተማሪዎች እነ ማን ናቸው?
መነ ተኀሥሥ/ ማንን ትፈልጋለህ/ትፈልጊያለሽ
መነ ታፈቅር/ ማንን ትወዳለህ/ትወጃለሽ
መልስ  
ዳዊት ውእቱ ስምየ ስሜ ዳዊት ነው።
ዳዊት ይትበሀል ስምየ። ስሜ ዳዊት ይባል።
ሔዋን ይትበሀል ስምየ። ስሜ ሔዋን ይባላል። 
አቡየ ወእምየ ወለዱኒ። አባትና እናቴ ወለዱኝ። 
እግዚአብሔር ፈጠረኒ። እግዚአብሔር ፈጠረኝ።
ያሬድ ይትበሀል አቡየ። አባቴ ያሬድ ይባላል። 
ቅድስት ትትበሀል እምየ። እናቴ ቅድስት ትባላለች።
መምህር መጽአ ናሁ። አሁን መምህር መጣ። 
ነቢዩ ሖረ ናሁ። ነቢዩ አሁን ሄደ። 
ደረጀ ወሐብታሙ ውእቱ ስምነ። ስማችን ደረጀና 
ሐብታሙ ነው።
እለ አብርሃም ውእቶሙ። እነ አብርሃም ናቸው።
አነ አኀሥሥ አቤልሀ። እኔ አቤልን እፈልጋለሁ። 
አነ አፈቅር አስቴርሀ። እኔ አስቴርን እወዳለሁ።
, እፎ እንዴት How
እፎ እፎ እንዴት እንዴት ምንኛ
ጥያቄ 
ምሳሌ
እፎ ኀደርክሙ እንዴት አደራችሁ።
እፎ ወዐልክሙ እንዴት ዋላችሁ።
እፎ ወዐልከ/ እንዴት ዋልክ /ሽ።
እፎ ወእቱ ሕይወት ሕይወት እንዴት ነው።
እፎ ውእቱ ግብርሥራ እንዴት ነው።
እፎ ውእቱ ህላዌከ/ኑሮህ እንዴት ነው።
እፎ እፎ ተዋነይከ ብየእንዴ እንዴት ተጫወትክብኝ
እፎ ይኩን ዝንቱ ነገርይህ ነገ እንዴት ይሁን።
መልስ 
ይትባረክእግዚአብሔር እግዚአብሔር ይመስገን።
ጥቀ ሠናይ ወእቱ በጣም ጥሩ ነው።
ምንተኑመ ኢይብል ምን አይልም።
ጸልዮ ኀበ እግዚአብሔር ይኄይሰኒ ወደ እግዚአብሔር 
መጸለይ ይሻለኛል።
ጥቀ ሠናይ ውእቱ በጣም ነው።
ይኩን በከመ ፈቀድከ እንደ ወደድክ ይሁን 
ምልማድ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትርጉም የሚመሳሰሉትን ""ስር ያሉትን 
""ስር ካሉት ጋር አዛምድ/
 "
" ........ " "
 , ጸለየ ........ , ፍጹመ
, ቡራኬ ........ , አደመ
, ተውኔት ........ , ሕይውና
, ምንተኑመ ........ , ተንበለ
, ሰቆቃው ........ , ትረጓሜ
, ጥቀ ........ , ወይሌ 
, ዐቃቢ ........ , ወሚመ
, ሠነየ ........ , ማኅሌት
, ህላዌ ........ , ስባሔ
, ፍካሬ ........ , ኖላዊ
ምልማድ
የሚከተሉት ጥያቄዎች በማንበብ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጥ/
__
, ___ወዐልክሙ አንትሙ አርድእት
, መኑ , መነ , እፎ , እለመኑ
__
, መነ ታፈቅሪ ___ትጸልዒ አንቲ ብእሲት
, መኑ , መነ , እፎ , አልቦቱ ሚጠት
__
,____ወእቶሙ ዘቀደሱ ቅዳሴ ዮም
, መኑ , እፎ , ምንተኑ , እለመኑ