Monday, December 31, 2018

ምክንያታዊነትን ለመጠየቅ የምንጠቀምበት መጠይቃዊ ቃል


Ø     ክፍለ ትምህርት
ምክንያታዊነትን ለመጠየቅ የምንጠቀምበት መጠይቃዊ ቃላት
,ለምንት ለምን why? 
=> ህየንተ ምንት ስለምን about what?
=> በእንተ ምንት ስለምን about what?
=> በምክንያተምንት በምንምክንያት?
 ጠያቂ
ð   ለምንት ትትሜሀር ልሳነ ግእዝ? የግእዝ ቋንቋ ለምን ትማራለህ?
ð   ለምንት የሐውር ሰብእ ኀበ ቤተ ክርስቲያን? ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለምን ይሔዳል?
ð   ለምንት መጻእከ/ ዮም? ዛሬ ለምንመጣህ/
ð   ለምንት ሖርከ/ ኀበ ጎንደር? ወደ ጎንደር ለምን ሔድክ/?
ð   ለምንት ይዜኀር ባዕል? ባለፀጋ ለምን ይኮራል?
ð   ለምንት ተፈጥረ ሰብእ? ሰው ለምን ተፈጠረ?
ð   በይነ ምንት ተኀዝን/? ስለምን ታዝናለህ/ኛለሽ?
ð   ህየንተ ምንት ተወልደ ክርስቶስ? ክርስቶስ ስለምን ተወለደ?
ð   በምክንያተ ምንት በከዩ ሕዝብ? ሕዝቦች ስለምን ምክንያት አለቀሱ?
 መላሽ
ð   ለአንብቦተ መጻሕፍት እትሜሀር። መጽሐፍ ለማንብ እማራለሁ።
ð   ለገቢረ ጸሎት የሐውር። ጸሎት ለማድረግ ይሔዳል።
ð   ለነጽሮተ ሕንጻ ዘፋሲለደስ። የፋሲለደስን ሕንጻ ለማየት።
ð   ለተምህሮ ግእዝ መጻእኩ። ግእዝ ለመማር መጣሁ።
ð   በእንተ በዝኀ ሐብቱ ይዜኀር። ሐብቱ ስለበዛ ይኮራል።
ð   ለሰብሖተ ፈጣሪ ተፈጥረ ሰብእ። ሰው ፈጣሪን ለማመስገን ተፈጠረ።
ð    በእንተ ሀገርየ አኀዝን። ስለሀገሬ አዝናለሁ። 
ð   ህየንተ ሰብእ ተወልደ ክርስቶስ። ክርስቶስ ስለሰው ተወለደ።
ð   በምክንያተ ሀገሮሙ በከዩ። ስለሀገራቸው ምክንያት አለቀሱ።
 የሚከተሉትን ቃላት በቃላችሁ ያዙ/አጥኑ
ð    ህየንተ/በእንተ ስለ --- ሰብእ ሰው
ð   ተዝኅረ ኮራ -------  ይዜኀር ይኮራል
ð   በከየ አለቀሰ -------  ባዕል ባለፀጋ
ð   በዝኀ በዛ ---------  ሐነጸ ሰራ
ð   ገብረ አደረገ ------- ሀገሮሙ አገራቸው
ð   ነጸረ አየ --------- ይኔጽር ያያል
ð   ሰብሐ አመሰገነ -----  ይሴብሕ ያመሰግናል
ከሁለት አንድ የሆነ አማራጭን ለመጠየቅ የሚያገለግል መጠይቃዊ ቃል
,  አይ የቱ/የትኛው which?
=> አየ የቱን/የትኛውን which?
=> አያት የቶቹ/የትኞቹ which?
=>አያተ የቶችን/የትኞቹን which?
ጠያቂ
=>
አይ ውእቱ ርእስከ/? ራስህ/ የትኛው ነው?
=> አይ ውእቱ የማናይ ዐይንከ/? ቀኙ ዐይንህ / የትኛው ነው?
=> ይኄይስ እምነ ጎንደር አዲስ አበባ? ከጎንደርና ከአዲስ አበባ የቱ ይሻላል
=> አይ የዐቢ እምነ ዐባይ ተከዜ? ከዐባይና ከተከዜ የቱ ይበልጣል
=> አይ ውእቱ ቤትከ/ ቤትህ/ የትኛው ነው
=> አይ ልሳን ዘይትናገር ዘንተ ነገረ? ይህንን ነገር የሚናገር የትኛው አንደበት ነው?
=> አየ ትጸልእ ወአየ ታፈቅር እምነስቴ መብልዕ? ከመብልና ከመጠጥ የትኛውን ትጠላለህ የትኛውንስ ትወዳለህ
=> አያት ውእቶሙ አብያጺከ? ጓደኞችህ የትኞቹ ናቸው?
=> አያት ወእቶሙ አዕይንቲከ? ዐይኖችህ የትኞቹ ናቸው
=> አያት ውእቶሙ አእጋሪከ? እግሮችህ የትኞቹ ናቸው?
=> በአይ ዘመን ይመጽእ ክርስቶስ? ክርስቶስ በየትኛው ዘመን ይመጣል?
=> በአይ ዕለት ተሰቅለ ክርስቶስ? ክርስቶስ በየትኛው ቀንተሰቀለ?
=> በአይ ዕለት ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን? ክርስቶስ በየትኛው ቀን ከሙታን መካከል ተነሣ?
 መላሽ 
=> ዝንቱ ውእቱ ርእስየ። ራሴ ይህ ነው።
=> ዝንቱ ውእቱ የማናይ ዐይንየ። ቀኙ ዐይኔ ይህ ነው።
=> አዲስ አበባ ይኄይስ። አዲስ አበባ ይሻላል።=> ዐባይ የዐቢ እምነ ተከዜ። ከተከዜ ዐባይ ይበልጣል።
=> ዝንቱ ውእቱ ቤትየ። ቤቴ ይህ ነው። 
=> ዝንቱ ልሳን ይትናገር ዘንተ ነገረ። ይህን ነገር ይህኛው አንደበት ይናገራል።
=> አነ አጸልዕ ስቴ ወባሕቱ አፈቅር መብልዐ። መጠጥ እጠላለሁ ነገር ግን መብል እወዳለሁ።
=> እሉ ውእቶሙ አብያጽየ። እነዚህ ጓደኞቼ ናቸው።
=> እሉ ውእቶሙ አዕይንትየ። እነዚህ ዐይኖቼ ናቸው።
=>እሉ ውእቶሙ አእጋርየ። እነዚህ እግሮቼ ናቸው።
=> በማእከላዊ ዘመን ይመጽእ ክርስቶስ። ክርስቶስ በመካከለኛው ዘመን ይመጣል።
=> በዕለተ ዐርብ ተሰቅለ ክርስቶስ። ክርስቶስ ዐርብ ቀን ተሰቀለ።
=> በዕለተ እሑድ ተንሥአ ክርስቶስ። ክርስቶስ እሑድ ቀን ተነሣ።
የዕለቱ ዋና ዋና ቃላት
=> ጸልአ ጠላ --------  ልሳን አንደበት
=> አፍቀረ ወደደ ------  ማእከላዊ መካከለኛ
=> ተንሥአ ተነሣ ------  አእጋር እግሮች
=> የማን ቀኝ -------- የዐቢ ይበልጣል
=>እሉ እነዚህ -------  ስቴ መጠጥ
=> ውእቶሙ ናቸው ----  መብልዕ መብል
የክፍለ ትምህርት መልመጃ
የሚከተሉትን ቃላት በተስማሚው ቦታ በማስገባት ባዶ ቦታውን አሟሉ። 
አንድ ቃል ሁለት ቦታ ሊገባ ይችላል።
- ማዕዜ ---------  አይቴ
- መኑ ----------   እፎ
- ምንት ---------  እለመኑ
- እስፍንቱ -------- እስፍንተ
-     እስከ ማእዜኑ ----  ለምንት
,______ አኀው ሀለውከ እኁየ
,______ ይከውነኒ ዝንቱ ነገር እንዘ ኢየአምር ብእሴ
,______ ሐዋርያተ ኀረየ ክርስቶስ
,______ ይትበሀል ስመ ዚአከ/
,______ አነብር ኀዘነ ውስተ ልብየ ይቤ ዳዊት በመዝሙሩ። 
,______ ነገር ይኄይሰነ አኀውየ
,______ ሖሩ ዮም ኀበ አሜሪካ
,______ ተወልደት ማርያም ቅድስት
,______ ውእቱ መካነ ህላዌከ/
,______ ትትሜሀሩ ልሳነ ግእዝ?